Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
/ 3 4 7
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
እግዚአብሔር ይነሳ! (የቀጠለ)
የመዳን ተስፋን እናረጋግጣለን ፡፡ መተላለፋቸውን ይቅር ባለበት እና በዚያች ጨለማ ከተማ ላይ በሚፈርድ ፍርዱ ፣ እግዚአብሔር ለጠፉት እና ዓመፀኛ ለሆኑ የሰው ልጆች ያለውን ጥልቅ ፍቅር እና ነዋሪዎች በፊቱ ራሳቸውን ዝቅ ካደረጉ እጅግ በጣም ክፉ ከሆነችው ከተማ ላይ እንኳን ፍርዱን ማቀቡን እንመለከታለን ፡፡ እግዚአብሔር በሺዎች የሚቆጠሩ የተሞሉትን ነነዌን በመጽሐፍ ቅዱስ ጊዜ ካዳነ ፣ ያው እግዚአብሔር በአስር ሚሊዮኖች የተሞላችውን ኒው ዮርክን ወይም በደርዘን የሚቆጠሩ ሚሊዮኖች የሞሏትን ሜክሲኮ ሲቲን እንደሚያድን በእርግጠኝነት መናገር እንችላለን! ምሳሌው መጽሐፍ ቅዱሳዊ እና አሳማኝ ነው፤ ልባቸው ለተሰበረ ፣ ለተጸጸቱ እና ለሚመለሱ ሁሉን ቻይ የሆነው እግዚአብሔር ለጩኸታቸው ምላሽ ይሰጣል (መዝ. 34.18) ፡፡ በማረጋገጫ ክፍለ ጊዜ ፣ ጌታን በመፈለግ እና በመለመን ወቅት ለእያንዳንዳችን ጌታ የተናገረንን በጸሎት እና በምስክርነት ለእግዚአብሔር እናረጋግጣለን ፡፡ ለእኛ ቤዛ እንድንሆን አንድያ ልጁን የላከውን የእግዚአብሔርን ዘ ላለማዊ ፍቅር እናረጋግጣለን (ዮሐ. 3.16) ፣ እናም በስሙ የተጠሩ ሕዝቦቹ ራሳቸውን ዝቅ ሲያደርጉ ፣ ሲጸልዩ ፣ ፊቱን ሲሹ ፣ እናም እራሳቸውን ከሚያስቡበት መንገድ፣ ከሚመኙት እና በራስ ከመመካት ክፉ መንገዳቸው ንስሃ ይግቡ (2 ዜና 7.14)። እግዚአብሔር በሚሰቃዩበት ፣ በተሰበሩበት እና በሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ ወደ እርሱ ለሚጮኹት ሕዝቡ ምላሽ ይሰጣል (ዘዳ. 26.5-10) ፡፡ የእግዚአብሔርን ትክክለኛነት (እውነተኛነት) እና ሉዓላዊነት የምናውቅበት የማረጋገጫ ክፍላችንን ከፀሎት የመጨረሻ ዝግጅት ጋር እንተዋለን ፡፡ ጌታን ለመጠበቅ ፣ የእርሱን መምጣት ለመፈለግ ፣ ልባችንን የሚያጸናውን እርሱን ብቻ ለመጠበቅ አንድ ላይ ቃል እንገባለን (መዝ. 27.14) ፡፡ በጸሎታችን ቢደክመንም ፣ እንደ ፈቃዱ እና እንደ ልቡ ሃሳብ እየጸለይን ስለሆነ ከእግዚአብሔር ጋር እንደምንጸና እርግጠኞች ነን (ኢሳ. 40.28-31) ፡፡ አንጠራጠርም ወይም ተስፋ አንቆርጥም ወይም አናመነታም (ያዕቆብ 1.5 ፤ ገላ. 6.9) ፡፡ መማለድ ከጀመርን ፣ እንፍገመገም ይሆናል እንጂ ልክ መበለቷ ዳኛውን እስኪፈርድላት ድረስ እንደነዘነዘችው ፣ እኛም እርሱ እስኪመልስልን ድረስ እግዚአብሔርን መጠየቅ እንዳለብን እርስ በእርስ እናሳስባለን (ሉቃስ 18.1-8) ፡፡ ልባችን ጨክኗል፤ እኛም እንደ አባታችን እንደ ያዕቆብ ከእግዚአብሔር ጋር ለመታገል ፣ ለመለመን ፣ እሱን ለመያዝ እና እስኪባርከን ድረስ ላለመልቀቅ ቁርጥ ውሳኔ አድርገናል (ዘፍ. 32.24-32) ፡፡ ልክ እንደ ኢዮሳፍጥ ፣ እኛ አሁን ባሉት የጨለማ ገዥዎች ላይ እና የአሜሪካን ውስጣዊ ከተሞች ለማጥፋት በተሰባሰቡ መንፈሳዊ ኃይሎች ላይ ምንም ሃይል የለንም፥ ምን ማድረግ እንዳለብንም አናውቅም ግን ዓይኖቻችን ወደ ጌታ ናቸው (2 ዜና 20.12)። አንድ ቀን እግዚአብሔር የዚህ ዓለም ከተሞችን ለልጁ (የአሜሪካን ውስጣዊ ከተሞችንም ጭምር) እንደሚሰጠው እርግጠኞች ነን ፣ እነዚህም እግዚአብሔር ድል ለነሳው ጌታ ለመስጠት ያዘጋጀው ርስት አንድ ወሳኝ አካል ብቻ ናቸው (መዝ. 2.8) . ጠላቶቹ ሁሉ ከእግሩ በታች እስኪገዙለት ድረስ ጌታችን ኢየሱስ ሊነግሥ እንደሚገባ በማወቅ (1 ቆሮ. 15.24-28) ፣ የእርሱን ዓላማ አንጠራጠርም ወይም ምላሽ እስኪሰጠን ትዕግሥት አናጣም ፡፡ እግዚአብሔር ለእኛ በራሱ ጊዜ እና በራሱ መንገድ ምላሽ ይሰጠናል፡፡ በተለይ በ ተፅዕኖ እና በግንኙነት አካባቢዎቻችን ውስጥ እንደገና ለመበተን ስብሰባችንን ለቅቀን ብንወጣም የፀሎታችን ክፍለ-ጊዜ ግማሽ ሰዓት ፣ ሙሉ ጠዋት ፣ ሙሉ ቀን
Made with FlippingBook - Online catalogs