Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

/ 3 9

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

ለ. ሚክ. 7.20

ሐ / የተስፋው ቃል ተለይቶ ታወቀ - የይሁዳ ነገድ-የአብርሃም ዘር ከይሁዳ ነገድ ይወጣል ፣ ዘፍ 49.8-10።

1. የትንቢታዊ ቃል ትዕይንት - ከመሞቱ በፊት የያዕቆብ በረከት በልጆቹ ላይ ፣ ዘፍ 49

2. የይሁዳ ነገድ ገዢው እንደሚመጣበት የዘር ሐረግ ተለይቶ ታወቀ (ማለትም “በትረ መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም”)

1

3. በረከቱ ፥ በትረ መንግሥት (የመግዛት መብት) የእርሱ ይሆናል ፣ ለእርሱም የሕዝቦች ሁሉ መታዘዝ ይሆናል (ሁሉን አቀፍ ድነት)

መ / የተስፋው ቃል ተብራራ - የዳዊት ኪዳን

2ኛሳሙኤል7፡ 8-16 “አሁንምዳዊትንባሪያዬንእንዲህበለው፦የሠራዊትጌታእግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አንተ መንጋውን ስትከተል በሕዝቤ በእስራኤል ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ ከበግ ጥበቃ ወሰድሁህ፤ በሄድህበትም ሁሉ ከአንተ ጋር ነበርሁ፥ ጠላቶችህንም ሁሉ ከፊትህ አጠፋሁ፤ በምድርም ላይ እንዳሉ እንደ ታላላቆቹ ስም ታላቅ ስም አደርግልሃለሁ። ለሕዝቤም ለእስራኤል ስፍራ አደርግለታለሁ፥ እተክለውማለሁ፤ በስፍራውም ይቀመጣል፥ ከዚያም በኋላ አይናወጥም፤ እንደ ቀድሞው ዘመንና በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ፈራጆች እንዳስነሣሁበት ጊዜ ግፈኞች ተመልሰው አያስጨንቁትም፤ ከጠላቶችህም አሳርፍሃለሁ። እግዚአብሔርም ደግሞ፦ ቤት እሠራልሃለሁ ብሎ ይነግርሃል። ዕድሜህም በተፈጸመ ጊዜ ከአባቶችህም ጋር ባንቀላፋህ ጊዜ፥ ከወገብህ የሚወጣውን ዘርህን ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ፥ መንግሥቱንም አጸናለሁ። እርሱ ለስሜ ቤት ይሠራል፤ የመንግሥቱንም ዙፋን ለዘላለም አጸናለሁ። እኔም አባት እሆነዋለሁ፥ እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤ ክፉ ነገርም ቢያደርግ፥ ሰው በሚቀጣበት በትርና በሰው ልጆች መቀጫ እገሥጸዋለሁ፤ ከፊቴም ከጣልሁት ከሳኦል እንዳራቅሁ ምሕረቴን ከእርሱ አላርቅም። ቤትህና መንግሥትህም በፊቴ ለዘላለም ይጠነክራል፥ ዙፋንህም ለዘላለም ይጸናል።

1. የአብርሃም በረከት የሚመጣበትን መስመር በትክክልና በግልፅ ያሳያል

Made with FlippingBook - Online catalogs