Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

4 6 /

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

CONNECTION

ይህ ትምህርት የሚያተኩረው እግዚአብሔር በዓለም ላይ እያከናወነ ስላለው ነገር “ትልቁን ምስል” እንድናገኝ በሚያስችለን በሁለት የተለያዩ የሚሽን ዓላማዎች ላይ እና የመንግሥቱን አገዛዝ ከማሳደግ ተልእኳችን ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ነው ፡፡ የሚከተሉት መግለጫዎች በትምህርቱ ውስጥ የተካተቱትን ማዕከላዊ ፅንሰ-ሀሳቦችን ይወክላሉ ፣ እናም ለአፅንዖት እና ግንዛቤ እንደገና መከለስ አለባቸው። (ሁል ጊዜ ይህን አስታውስ ፣ ተመሳሳይ ፅንሰ-ሀሳቦች እንዲደጋገሙና እንዲገመገሙ ማድረግ መረዳታቸውን ማረጋገጥ ነው ፣ ኢያሱ 1.8 ፣ ፊል. 3:1) ³ “ፕሮሌጎሜና” የሚለው ቃል “የመጀመሪያ ቃል” ማለት ሲሆን ለሚሽን ፕሮሌጎሜና መጀመር ያለበት እግዚአብሔር በናዝሬቱ በኢየሱስ ሰውነት አማካኝነት በምድር ላይ ስላለው ስራ ካለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ ነው። ³ ሚሽን እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነት እና ሥራ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ለሰው ልጆች ሁሉ ያደረገውን ማዳን እና ቤዛነት ማወጅ እንደሆነ ሊተረጎም ይችላል። ³ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሚሽን መረዳት ከቅዱሳት መጽሐፍት የሚቀዱ ነጥቦችን አጠቃሎ ይይዛል፡፡ ሚሽን መመስረት ያለበት ስለ እግዚአብሔርና ለፍጥረት ሁሉ ስላለው አላማ ግልጽ የሆነ ግንዛቤ በመያዝ ነው፡፡ የመጽሀፍ ቅዱሳዊው ሚሽን ምልከታ መመስረት ያለበት መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ ስለ እየሱስ ማንነትና ስራ በሚናገረው ላይ ሆኖ ይህም በምስል፡ በስእሎች እና በታሪኮች መተረክ ያስፈልገዋል፡፡ ³ አራቱን መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሚሽን ማእቀፎች/ምስሎች ማለትም ሚሽንን እንደ ሁልጊዜ ክስተት (በታሪክ ውስጥ እንደ ዋና ገጸ ባህሪ) እንደ መጠበቅ፤ እንደ ዘመናት የፍቅር ግንኙነት (እግዚአብሔር ለተዋጀው ህዝቡ እንደ ሙሽራ)፤ እና እንደ ሽፍቶች ጦርነት እግዚአብሔር በፍጥረት አለሙ ላይ መንግስቱን ድጋሚ እንደሚመሰርት ጦረኛ፡፡) ³ ከዘመን በፊት (የእግዚአብሔር ቅድመ ህልውና እና አላማ፤ የአመጻን ሚስጥር እና ኢፍትሀዊ ኃይል የሚያሳይ)፤ የጊዜ መጀመሪያ (እርሱም የአጽናፈ አለሙን እና የሰው ልጅ ፍጥረትን፤ ውድቀትና እርግማን ፕሮቶኢቫንጌሊየምን፤ የኤደንን መጨረሻ፤ የሞትን አገዛዝ እና የመጀመሪያዎቹን የጸጋ ምልክቶች ያጠቃልላል) ፥ የጊዜ መገለጥ (አብርሃማዊውን ተስፋ፣ ዘጸአትን፣ የመሬትን ምርኮ፣ የከተማ-መቅደስ-ዙፋን፣ የግዞት እና የቅሬታዎችን መመለስ ያጠቃልላል።) ³ ስለዘመንፍጻሜየማይታጠፈውየእግዚአብሔርተስፋ፤ የኢየሱስንስጋመልበስ፤ የመንግስቱን መገለጥ፤ የኢየሱስን ህማማት፤ ሞት፤ ትንሳኤና እርገት ያጠቃልላል፡፡ የመጨረሻው ዘመን ደግሞ የመንፈስ ቅዱስን መውረድ፤ የቤተክርስትያንን ተሀድሶ፤ የአህዛብን መካተትና የአለማቀፋዊውን ሚሽን ያጠቃልላል፡፡ ³ የዘመን ፍፃሜ አለም አቀፉን ስብከተ ወንጌል ማብቃት፤ የቤተክርስቲያንን ክህደት፤ ታላቁ ነጩን ዙፋን፤ የእሳት ባህርንና የእየሱስ ክርስቶስ መንግስቱን ለእግዚአብሔር አሳልፎ መስጠትን ያጠቃልላል። ከዘመን ፍጻሜ በኋላ አዲሲቷን ምድር ፤ የአዲሲቱን ኢየሩሳሌም የመታደስ ዘመንና ሊመጣ ስላለው ዘመን ያጠቃልላል፡፡

የቁልፍ ፅንሰ ሀሳቦች ማጠቃለያ

1

Made with FlippingBook - Online catalogs