God the Father, Amharic Mentor Guide

This is the Amharic version of Capstone Module 6 Mentor Guide.

ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ

THE URBAN MINISTRY INSTITUTE የWORLD IMPACT, INC. አገልግሎት ነው

እግዚአብሔር አብ

የመምህሩ መምሪያ

ሞጁል 6 ስነመለኮት እና ስነምግባር

AMHARIC

የመምህሩ መመሪያ

እግዚአብሔር አብ

ሞጁል 6

ሥነ-መለኮት እና ሥነ-ምግባር

ፕሮሌጎሜና፡

ትምህርተ እግዚአብሔር እና የመንግሥቱ መስፋት

እግዚአብሔር እንደ ፈጣሪ፡

የእግዚአብሔር መግቦት

አምላከ ሥላሴ፡

የእግዚአብሔር ታላቅነት

እግዚአብሔር እንደ አባት፡

የእግዚአብሔር ቸርነት

ይህ ሥርዓተ-ትምህርት የThe Urban Ministry Institute (TUMI) የሺዎች ሰዓታት የሥራ ውጤት በመሆኑ ያለ ፈቃድ ማባዛት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ TUMI እነዚህን መማሪያዎች ለእግዚአብሔር መንግሥት እድገት ለመጠቀም ለሚፈልጉ ሁሉ ድጋፍ ያደርጋል፤ በተጨማሪም ለማባዛት በተመጣጣኝ ዋጋ ፈቃድ ይሰጣል ፡፡ እባክህ ይህ መጽሐፍ በትክክል ፈቃድ ያገኘ መሆኑን ከመምህርህ ጋር በመሆን አረጋግጥ፡፡ በ TUMI እና በፈቃድ አሰጣጥ ፕሮግራማችን ላይ የበለጠ መረጃ ለማግኘት Www.site.org እና Www.tumi.org/license ን ጎብኝ፡፡

ካፕስቶን ሞጁል 6: - እግዚአብሔር አብ የመምህሩ መመሪያ ISBN: 978-1-62932-489-0

© 2005, 2011, 2013, 2015. The Urban Ministry Institute. መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው. የመጀመሪያ እትም 2005 ፣ ሁለተኛ እትም 2011 ፣ ሦስተኛው እትም 2013 ፣ አራተኛ እትም 2015 ፡፡

በ 1976 የቅጂ መብት ሕግ ወይም ከአሳታሚው በፅሁፍ ከሚፈቀደው በስተቀር የእነዚህን መማሪያ ቁሳቁሶች መቅዳት፣ እንደገና ማሰራጨት እና / ወይም መሸጥ ወይም በማንኛውንም ያልተፈቀደ መንገድ ማስተላለፍ የተከለከለ ነው ፡፡ የፍቃድ ጥያቄዎች በሚከተለው አድራሻ መቅረብ አለባቸው፥ The Urban Ministry Institute ፣ 3701 E. 13th Street, Wichita, KS 67208. The Urban Ministry Institute የWorld Impact አገልግሎት ነው በዚህ ሞጁል ውስጥ የተጠቀሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በሙሉ በአዲሱ መደበኛ ትርጉም ላይ የተመሰረተ ነው፡ ፡

ይዘት

የኮርሱ አጠቃላይ እይታ

3 5 7

ስለ ጸሐፊው

የሞጁሉ (የትምህርቱ) መግቢያ

የኮርሱ መስፈርቶች

13 ትምህርት 1

1

ፕሮሌጎሜና: ትምህርተ እግዚአብሔር እና የመንግሥቱ መስፋት

41 ትምህርት 2

2

እግዚአብሔር እንደ ፈጣሪ: የእግዚአብሔር መግቦት

69 ትምህርት 3

3

አምላከ ሥላሴ፡- የእግዚአብሔር ታላቅነት

103 ትምህርት 4

4

እግዚአብሔር እንደ አባት: የእግዚአብሔር ቸርነት

137

አባሪዎች

245 የካፕስቶን ሥርዓተ-ትምህርት መመሪያ

253

የትምህርት 1 የአስተማሪው ማስታወሻዎች

259

የትምህርት 2 የአስተማሪው ማስታወሻዎች

265

የትምህርት 3 የአስተማሪው ማስታወሻዎች

273

የትምህርት 4 የአስተማሪው ማስታወሻዎች

/ 3

እግዚአብሔር አብ

ስለ ጸሐፊው

ቄስ ዶ/ር ዶን ኤል ዴቪስ የዘ አርባን ሚኒስትሪ ኢንስቲትዩት ሥራ አስፈፃሚ እና የዎርልድ ኢምፓክት ከፍተኛ ምክትል ፕሬዚዳንት ናቸው ፡፡ ትምህርታቸውን በዊተን ኮሌጅ እና በዊተን ድህረ ምረቃ ትምህርት ቤት የተከታተሉ ሲሆን በቢብሊካል ስተዲስ የቢ.ኤ. (1988) እና በሲስተማቲክ ቲዎሎጂ የኤም.ኤ (1989) ዲግሪዎችን በቅደም ተከተል ማግኘት ችለዋል ፡፡ በተጨማሪም ከአዮዋ ስኩል ኦፍ ሪሊጅን በሃይማኖት ጥናት (ሥነ-መለኮት እና ሥነ-ምግባር) ፒኤችዲ አግኝተዋል ፡፡ የተቋሙ ሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር እና የዎርልድ ኢምፓክት ዋና ሥራ አስፈፃሚ እንደመሆናቸው መጠን የከተማ ሚስዮናውያንን ፣ የቤተ ክርስቲያን ተካዮችን እና የከተማ መጋቢያን ሥልጠናን በበላይነት የሚቆጣጠሩና የሚመሩ ሲሆን ለከተሞች ክርስቲያን ሠራተኞች በስብከተ ወንጌል ፣ በቤተ ክርስቲያን እድገት እና በተቀዳሚ ተልእኮዎች የሥልጠና ዕድሎችን ያስተባብራሉ ፡፡ በተጨማሪም የተቋሙን ሰፊ የርቀት ትምህርት መርሃግብሮች ይመራሉ እንዲሁም እንደ ፕሪዝን ፌሎውሺፕ ፣ ኢቫንጀሊካል ፍሪ ቸርች ኦፍ አሜሪካ ላሉት ድርጅቶች እና ቤተ እምነቶች የአመራር ልማት ኢድሎችን ያመቻቻሉ ፡፡ የበርካታ የማስተማር እና የአካዳሚክ ሽልማቶች ባለቤቱ ዶ/ር ዴቪስ በበርካታ ዕውቅ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሮፌሰር እና የፋኩልቲ አባል ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በሃይማኖት ትምህርቶች፣ ሥነ መለኮት ፣ ፍልስፍና እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥናቶች (ቢብሊካል ስተዲስ ) እንደ ዊተን ኮሌጅ ፣ ሴንት አምብሮስ ዩኒቨርሲቲ ፣ ሂዩስተን ድህረ ምረቃ የሥነ-መለኮት ትምህርት ቤት ፣ በአዮዋ ዩኒቨርሲቲ ስኩል ኦፍ ሪሊጅን ፣ በሮበርት ኢ ዌበር ኢንስቲትዩት ኦፍ ዎርሺፕ ስተዲስ ባሉ የትምህርት ተቋማት ሲያስተምሩ ቆይተዋል፡፡ የከተማ መሪዎችን ለማስታጠቅ በርካታ መጻሕፍትን ፣ ሥርዓተ-ትምህርቶችን እና የጥናት ጽሑፎችን አዘጋጅተዋል ፣ ከነዚህም ውስጥ የ ‹ካፕስቶን› ሥርዓተ ትምህርት ፣ የ TUMI ፕሪሚየር ሲክስቲን ሞጁል ዲስታንስ ኤጁኬሽን ሴሚናሪ ኢንስትራክሽን፥ የከተሞች አብያተ ክርስቲያናት ታሪካዊቷን የኦርቶዶክስ እምነት እንደገና በማደስ ራሳቸው እንዴት ሊታደሱ እንደሚችሉ የሚያትተው ሴክርድ ሩትስ፡ ኤ ፕሪሚየር ኦን ሪትራይቪንግ ዘ ግሬት ትራዲሽን እና ብላክ ኤንድ ሂዩማን፡ ሪዲስከቨሪንግ ኪንግ አስ ኤ ሪሶርስ ፎር ብላክ ትዎሎጂ ኤንድ ኤቲክስ ተጠቃሾች ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ ዶ/ር ዴቪስ እንደ ስታሊ ሌክቸር ሲሪስ ባሉ ትምህርታዊ ጉባኤዎች፣ እንደ ፕሮሚስ ኪፐርስ ራሊስ ባሉ የተሃድሶ ኮንፈረንሶች እና እንደ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቨርጂኒያ ሊቭድ ቲዎሎጂ ፕሮጄክት ሲሪስ ባሉ ሥነ-መለኮታዊ ጥምረቶች ተሳትፈዋል ፡፡ ዶ/ር ዴቪስ በ 2009 ከአዮዋ ዩኒቨርስቲ የሊበራል አርትስ እና ሳይንስ ኮሌጅ የአልሙናይ የክብር ሽልማት ያገኙ ሲሆን በተጨማሪም የዘ ሶሳይቲ ኦፍ ቢብሊካል ሊትሬቸር እና ዘ አሜሪካን አካዳሚ ኦፍ ሪሊጅን አባል ናቸው ፡፡

/ 5

እግዚአብሔር አብ

የትምህርቱ/የሞጁሉ መግቢያ

ኃያል በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም ላንተ ይሁን!

የአምላካችንን የእግዚአብሔር አብ ማንነት ማጥናት በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ካሉ ጥናቶች ሁሉ እጅግ አስፈላጊ እና እጅግ ጥልቅ ከሆኑት አንዱ ነው። የደቀመዝሙርነታችንን፣ የአምልኮታችንን እና የአገልግሎታችንን ክፍል ሁሉ ይነካል። በእውነት ጌታችን ኢየሱስ “እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት” እንዳለው ነው (ዮሐ. 17፡3)። ፕሮሌጎሜና፡ ትምህርተ እግዚአብሔር እና የመንግሥቱ መስፋት፣ በተሰኘው በመጀመሪያው ትምህርታችን፣ እግዚአብሔር ራሱን ለእኛ የመግለጡን አስፈላጊነት በመመልከት፣ የነገረ መለኮትን ጥናት የሚያስተናግደውን ፕሮሌጎሜና በአጭሩ እንመረምራለን። የጠቅላላ እና የልዩ መገለጥ ጽንሰ ሀሳቦችን እናጠናለን፣ እንዲሁም ትምህርተ እግዚአብሔርን የማጥናት አስፈላጊነትን ከእግዚአብሔር ህልውና አንጻር፣ ማለትም እግዚአብሔር በፍጥረት ውስጥ ስላለው መገኘትና ተሳትፎ፣ እንዲሁም የእርሱን ምጡቅነት/ልዕልና፣ የእግዚአብሔርን የማይወሰን ተፈጥሮና ታውቆ የማይጨረስ ማንነት በጥንቃቄ እንመረምራለን። እግዚአብሔር እንደ ፈጣሪ፡ የእግዚአብሔር መግቦት በተሰኘው በሁለተኛው ትምህርታችን በፍጥረት እና በታሪክ ሁሉ ላይ ያለውን የእግዚአብሔርን የበላይ ሥልጣን እና መግቦትን እንመረምራለን። እግዚአብሔር ሁሉን እንደ ፈቃዱ ይሰራል። ሁሉን ቻይ የሆነው እግዚአብሔር አብ የሁሉም ሉዓላዊ ገዥ፣ የሕይወት ሁሉ ምንጭ፣ እና በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የሁሉ አኗሪ ነው። በተጨማሪም የእግዚአብሔር መግቦት ሁሉንም ነገር በመጠበቅ እና በማስተዳደር እንዴት እንደሚገለጽ እንመረምራለን፤ የእግዚአብሔርን መግቦትን በተመለከተ ጠንካራ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ግንዛቤ በፍልስፍና እና በሥነ-መለኮት ውስጥ ዋና ዋና ዘመናዊ ስህተቶችን ማለትም ፓንቴይዝም፣ ዴይዝም፣ ፋታሊዝም እና እድል እንዴት እንደሚፈታ እንመለከታለን። አምላከ ስላሴ: የእግዚአብሔር ታላቅነት በተሰኘው በሦስተኛው ትምህርታችን ጥቂት ለየት ያለ አቅጣጫ እንይዛለን። ስለ ሥላሴ፣ ማለትም ስለ እግዚአብሔር ሥላሴአዊ ማንነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎችን እንመለከታለን። ቅዱሳት መጻሕፍት አንድ አምላክ ብቻ እንዳለ ያስተምራሉ፣ ነገር ግን ይህ አምላክ ራሱን እንደ እግዚአብሔር አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ገልጿል። የሥላሴ አካላት አንድ፣ ልዩ ልዩና እኩል ናቸው፤ አንድ እውነተኛ አምላክ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ናቸው። ስለ ሥላሴ ካጠናን በኋላ፣ የእግዚአብሔርን የታላቅነቱን ባህሪያት፡ መንፈሳዊነቱን፣ ህያውነቱን፣ ስብዕናውን፣ የማጨረስና የማይለወጥ ማንነቱን በአጭሩ እንመረምራለን። በመጨረሻም፣ በትምህርት አራት እግዚአብሔር እንደ አባት፡ የእግዚአብሔር ቸርነት ወደተሰኘው ክፍል ትኩረታችንን እናዞራለን። እዚህ ላይ የእግዚአብሔርን ድንቅ ቸርነት በሥነ ምግባራዊ ባሕርያቱ ውስጥ ፍጹም የሞራል ንጽህና፣ ፍጹም ጽኑ አቋም እና ገደብ የለሽ ፍቅሩ ውስጥ እንመለከታለን። የእግዚአብሔርን ቸርነት እና ቆራጥነት በመመልከት፣ በእግዚአብሔር ቸርነት እና ጭከና፣ በፍቅሩ እና በፍትህ መካከል ያለውን ግንኙነት በመመርመር ሞጁላችንን እንዘጋለን ።

6 /

እግዚአብሔር አብ

በእውነት አምላካችን አባታችን አንድ፣ እውነተኛና የከበረ የሰማይ አምላክ ነው። እርሱን በደንብ ማወቅ እንደ አገልጋዮቹ በክብር እንድንወከለው ያግዘናል። ስለ ታላቁ እና ኃያሉ አምላካችን ያልተነገሩትን የቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ በትጋት ስለምትመረምር እግዚአብሔር ይባርክህ!

- ቄስ ዶ/ር ዶን ኤል ዴቪስ

/ 7

እግዚአብሔር አብ

የኮርሱ መስፈርቶች

• መጽሐፍ ቅዱስ (ለዚህ ትምህርት ዓላማ ሲባል የአንተ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም መሆን አለበት [ለምሳሌ NIV, NASB, RSV, KJV, NKJV, ወዘተ] እና የትርጓሜ ሐረግ መሆን የለበትም [ለምሳሌ The Living Bible, The Message] • እያንዳንዱ የካፕስቶን ሞጁል በሙሉ ትምህርቱ የሚነበቡ እና የሚያወያዩ የመማሪያ መጽሀፎችን አካትቷል ፡፡ እነዚህን ከመምህርህ እና አብረው ከሚማሩ ተማሪዎች ጋር በመሆን እንድታነብ፣ እንድታሰላስል እና እንድትመልስ እናበረታታሃለን ፡፡ እነዚህ ጽሑፎች በበቂ ሁነታ መገኘት ባለመቻላቸው ምክንያት (ለምሳሌ ፣ በቂ የመጻሕፍቱ ሕትመት ካለመኖሩ የተነሳ) የካፕስቶን አስፈላጊ የመማሪያ መጽሐፍ ዝርዝራችንን በድረ-ገፃችን ላይ እናስቀምጣለን። የዚህን መጽሐፍ (ሞጁል) ጽሑፎች ወቅታዊ ዝርዝር ለማግኘት እባክህን www.tumi.org/booksን ጎብኝ። • የክፍል ውስጥ ሥራዎችን ለመስራት እና ማስታወሻዎችን ለመውሰድ ወረቀት እና ብዕር ፡፡ • Hemphill, Ken. The Names of God. Nashville: Broadman and Holman Publishers, 2001. • Pink, A. W. The Attributes of God. Grand Rapids: Baker Book House, 1991. • Stone, Nathan. The Names of God. Chicago: Moody Press, 1944.

አስፈላጊ መጻሕፍት እና ቁሳቁሶች

የተጠቆሙ ንባቦች

8 /

እግዚአብሔር አብ

የግምገማዎች እና የምዘናዎች ድምር ውጤት በክፍል መገኘት እና የክፍል ውስጥ ተሳትፎ.. . . . . . . . . . . . . . . 30% 90 ነጥቦች

የኮርሱ መስፈርቶች

ፈተናዎች. . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 10% 30 ነጥቦች

የቃል ጥናት ጥቅሶች. . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 15% 45 ነጥቦች

የእክሴጀሲስ ፕሮጀክት. . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 15% 45 ነጥቦች

የሚኒስትሪ ፕሮጀክት. . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 10% 30 ነጥቦች

ንባቦች እና የቤት ስራዎች. . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 10% 30 ነጥቦች

የማጠቃለያ ፈተና................................. 10% 30 ነጥቦች

ጠቅላላ ድምር: 100% 300 ነጥቦች

አጠቃላይ ውጤት መመዘኛ መስፈርቶች በእያንዳንዱ የትምህርት ክፍለ ጊዜ መገኘት የኮርሱ ቅድመ ሁኔታ ነው ፡፡ መቅረት በውጤትህ ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል። በአስገዳጅ ምክንያት መቅረት ግድ በሚሆንበት ጊዜ እባክህ አስቀድመህ ለመምህርህ አሳውቅ ፡፡ ያመለጠህ ክፍለ ጊዜ ሲያጋጥም ያመለጠህን የቤት ሥራ መስራት እና ስለዘገየህበት ሁኔታ ከመምህሩ ጋር መነጋገር የአንተ ኃላፊነት ነው። ይህ ኮርስ ባብዛኛው በውይይት መልክ የሚካሄድ እንደመሆኑ መጠን የአንተ ንቁ ተሳትፎ በእያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ ውስጥ የሚፈለግና የሚጠበቅ ይሆናል። እያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ የሚጀምረው ካለፈው ትምህርት መሠረታዊ በሆኑት ሀሳቦች ላይ በተመሰረተ በአጭር ፈተና ይሆናል። ለፈተናው ለመዘጋጀት ደግሞ የተሻለው መንገድ ባለፈው ትምህርት ወቅት የተወሰዱ የተማሪውን መልመጃ (Student Workbook) እና የክፍል ማስታወሻዎችን መከለስ ነው ፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ አማኝ እና መሪ እንደመሆንህ መጠን በቃልህ ያጠናኸው ጥቅስ(ቃል) ለህይወትህ እና ለአገልግሎትህ መሰረት ነው ፡፡ በአንጻራዊነት ጥቅሶቹ ከቁጥር አንጻር ጥቂት ቢሆኑም በይዘታቸው ግን ጠቀሜታቸው የጎላ ነው፡፡ በእያንዳንዱ የትምህርት ክፍለ ጊዜ የተሰጡትን ጥቅሶች (በቃል ወይም በፅሁፍ) ለመምህርህ እንድትናገር ወይም እንድታነብብ ይጠበቅብሃል ፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔር ወንድ እና ሴት ልጆች ለተጠሩበት የአገልግሎት ድርሻ ሁሉ ለማስታጠቅ የእግዚአብሔር ልዩ መሳሪያ ናቸው (2 ጢሞ. 3.16-17) ፡፡ ለዚህ ኮርስ የሚያስፈልጉትን መመዘኛዎች ለማጠናቀቅ አንድ መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በመምረጥ በንባቡ ላይ ተግባራዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት (ማለትም ፣ የትርጓሜ ጥናት) ማድረግ አለብህ ፡፡ ጥናቱ አምስት ገጾች ርዝመት ሊኖረው ይገባል (በድርብ የተከፋፈለ ፣ ታይፕ የተደረገ ወይም በጥሩ ሁኔታ በእጅ የተፃፈ) እና በዚህ ትምህርት ውስጥ ጎላ ብለው ከተነሱት የክርስቲያን ሚሽን መሠረተ-ትምህርቶች እና መርሆዎች

በክፍል መገኘት እና የክፍል ውስጥ ተሳትፎ

ፈተናዎች

የቃል ጥናት ጥቅስ

የእክሴጀሲስ ፕሮጀክት

/ 9

እግዚአብሔር አብ

ውስጥ አንዱ ላይ ያተኮረ መሆን ይኖርበታል፡፡ ፍላጎታችን እና ተስፋችን ቅዱሳት መጻሕፍት የአንተን እና የምታገለግላቸውን ሰዎች ሕይወት በተጨባጭ ለመለወጥ ያላቸውን አቅም እንዲረዱ ነው። ኮርሱን በምትወስድበት ጊዜ የበለጠ ለማጥናት በምትፈልገው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ የንባብ ክፍል (በግምት ከ4-9 ቁጥሮች) ለማጥናት አታመንታ፡፡ የፕሮጀክቱ ዝርዝሮች በገጽ 10-11 ላይ የተካተቱ ሲሆን በዚህ ትምህርት መግቢያ ክፍል ውስጥ ይብራራሉ ፡፡ እኛ የምንጠብቀው ሁሉም ተማሪዎች ትምህርታቸውን በሕይወታቸው ውስጥ እና በአገልግሎት ድርሻቸው ላይ በተጨባጭ እንዲተገብሩት ነው ፡፡ ተማሪው የተማራቸውን መርሆዎች ከተግባራዊ አገልግሎት ጋር አጣምሮ የሚኒስትሪ ኘሮጀክት የማዘጋጀት ኃላፊነት አለበት ፡፡ የዚህ ፕሮጀክት ዝርዝሮች በገጽ 12 ላይ የተሸፈኑ ሲሆን በትምህርቱ መግቢያ ክፍል ውስጥ ይብራራሉ ፡፡ የክፍል ሥራ እና የተለያዩ ዓይነት የቤት ሥራዎች በክፍል ትምህርት ወቅት በመምህርህ ሊሰጡህ ወይም በተማሪው መልመጃ (Student Workbook) ውስጥ ሊጻፉ ይችላሉ፡፡ ስለሚፈለገው ነገርም ሆነ የቤት ስራ ስለ ማስረከቢያው ጊዜ ጥያቄ ካለህ መምህርህን ጠይቅ። ለክፍል ውይይት ለመዘጋጀት ተማሪው የተመደበውን ንባብ ከጽሑፉ እና ከቅዱሳት መጻሕፍት ማንበቡ አስፈላጊ ነው ፡፡ እባክህ በየሳምንቱ ከአንተ የተማሪው የመልመጃ መጽሐፍ ውስጥ “የንባብ ማጠናቀቂያ ቅጽ” ን ተመልከት። ለሚደረጉ ተጨማሪ ንባቦች ተጨማሪ ዋጋ/ነጥብ የማግኘት እድል ይኖራል ፡፡ በትምህርቱ መጨረሻ ላይ መምህርህ በቤት ውስጥ የሚጠናቀቅ የመጨረሻ ፈተና (የተዘጋ መጽሐፍ) ይሰጥሃል። በትምህርቱ ውስጥ የተማርከውን እና በአገልግሎትህ ላይ ያለህን አስተሳሰብ ወይም አሠራር እንዴት እንደሚነካው እንድታንጸባርቅ የሚረዳ ጥያቄ ትጠየቃለህ፡፡ ስለ መጨረሻው ፈተና እና ሌሎች ጉዳዮች መምህርህ አስፈላጊውን መረጃዎች ይሰጥሃል።

የሚኒስትሪ ፕሮጀክት

የክፍል እና የቤት ሥራ ምደባዎች

ንባቦች

ከቤት-የሚሰራ የማጠቃለያ ፈተና

ውጤት አሰጥጥ የሚከተሉት ውጤቶች በክፍለ-ጊዜው መጨረሻ ላይ በዚህ ክፍል ውስጥ ይሰጣሉ እናም በእያንዳንዱ ተማሪ መዝገብ ላይ ይቀመጣሉ።

A - የላቀ ሥራ

D - የማለፊያ ሥራ

B - በጣም ጥሩ ሥራ

F - አጥጋቢ ያልሆነ ሥራ

C - አጥጋቢ ሥራ

I - ያልተሟላ

ለእያንዳንዱ የመጨረሻ ክፍል አግባብነት ያላቸው ውጤቶች ይሰጣቸዋል ፣ ለእያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ የሚሰጠው የክፍል ነጥብ በጠቅላላው አማካይነት ውጤት ላይ የሚታሰብ ይሆናል። ያልተፈቀደ የስራ መዘግየት ወይም ሥራዎችን አለማስረከብ በውጤትህ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል ፣ ስለሆነም እባክህ አስቀድመህ አቅደህ ከመምህርህ ጋር ተነጋገር።

1 0 /

እግዚአብሔር አብ

የኤክሴጄሲስ ፕሮጀክት ይህ ትግበራ በትምህርተ እግዚአብሔር አብ የጥናት ሞጁል ውስጥ የተሳትፎህ ቁልፍ አካል ነው። ይህንን መስፈርት ለማሟላት የቅዱሳት መጻሕፍትን ምንባብ መርጠህ በጽሑፉ ላይ ኢንዳክቲቭ ጥናት (የትርጓሜ ጥናት) ማድረግ አለብህ። ከሚከተሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ውስጥ አንዱን መምረጥ ትችላለህ፡-  የሐዋርያት ሥራ 17:24-31  ኢሳይያስ 40:22-26  ሮሜ 9:13-18  ዳንኤል 4:34-37  መዝሙረ ዳዊት 103:9-18  ማቴዎስ 6:25-33  መዝሙረ ዳዊት 104:24-30 የዚህ ፕሮጀክት አላማ በእግዚአብሔር መግቦት፣ በፍጥረት ሁሉ ላይ ስላለው ጥበቃ እና አስተዳደር፣ እና ይህ ዛሬ ለህይወታችን ምን ማለት እንደሆነ በሚመለከት አንድ ዋና ክፍል በዝርዝር እንድታጠና እድል ለመስጠት ነው። ምናልባት ለክርስቲያን መሪ የቅዱሳት መጻሕፍትን ትርጉም ግልጽ ከማድረግ እና በዛሬው ጊዜ ካሉት ሰዎች እውነተኛ የሕይወት ጭንቀቶች ጋር ከማዛመድ ችሎታቸው የበለጠ አስፈላጊ ነገር የለም። አላማው የአንቀጹን ትርጉም ግልጽ ማድረግ ብቻ ሳይሆን የክፍሉን ትርጉም በቀጥታ ከራስህ የግል የደቀመዝሙርነት ጉዞ ጋር በማያያዝ እና በቤተክርስቲያንህ ወይም በአገልግሎትህ እንድታገለግል እግዚአብሔር የጠራቸውን ሰዎች እንድታስተምር ነው። ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮጀክት እንደመሆኑ የትርጓሜ ጥናት (ኤክሴጄሲስ) ለመስራት የጥናት ክፍሉን በአውዱ ውስጥ መረዳት ያስፈልጋል። በመቀጠልም ዋናውን ትርጉም ከተረዳህ በኋላ ለሁላችንም ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል መርህ ማውጣትና ይህንም በተጨባጭ ከህይወት ጋር ማዛመድ ይኖርብሃል። ይህን የግል የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ጥናት በምታደርግበት ወቅት እነዚህ ሶስት ደረጃዎች ሊያግዙህ ይችላሉ:- 1. በተሰጠው ምንባብ ውስጥ ለተጠቀሱት ዋና አድማጮች እግዚአብሔር መናገር የፈለገው ምንድነው? 2. ከዚህ ምንባብ ልንማረው የምንችለውና ለሁሉም ዘመንና በየትኛውም ቦታ ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ ልንወስደው የምንችለው መርህ ምንድነው? 3. ዛሬም መንፈስ ቅዱስ እኔን ከተማርኩት መርህ በመነሳት ምን እንዳደርግ ነው የሚፈልግብኝ? እንግዲህ እነዚህን ጥያቄዎች በተገቢው መንገድ ከመለስክ በቀጣይ ለወረቀት ስራህ የግልህን መረዳት ለማቅረብ ዝግጁ ነህ ማለት ነው። ለወረቀት ስራህ ይህን ቅደም ተከተል ተከትሎ መስራት ይረዳሃል፥ 1. የመረጥከው የንባብ ክፍል ዋና ጭብጥ ወይም ሃሳብ ምን እንደሆነ ለይተህ አስቀምጥ። 2. የምንባቡን ዋና ትርጉም በአጭሩ ግለጽ (ይህን በሁለት ወይም በሶስት አንቀጽ ልታስቀምጠው ትችላለህ ወይም ደግሞ በእያንዳንዱ ቁጥር አጫጭር ማጣቀሻ ወይም ማመሳከሪያ እየተጠቀምክ መሄድ ትችላለህ።)

ዓላማ

ዝርዝር መግለጫ እና አወቃቀር

/ 1 1

እግዚአብሔር አብ

3. ይህ የምንባብ ክፍል ሊሰጠን የሚችሉ ከአንድ እስከ ሶስት የሚደርሱ የክርስቲያን ሚሽን መርሆዎችን ዘርዝር። 4. ከመርሆዎቹ ውስጥ አንዱ፣ የተወሰኑት ወይም በጠቅላላው ከሚከተሉት ነጥቦች ጋር እንዴት እንደሚዛመዱ አሳይ፥ ሀ. ከአንተ የግል መንፈሳዊ ህይወት እና ከጌታ ጋር ካለህ ጉዞ ጋር ሐ. ባለህበት ማህበረሰብም ሆነ በጠቅላላው ህብረተሰብ ውስጥ ከሚንጸባረቁ ሁኔታዎችና ችግሮች ጋር የዚህን ትምህርት (ሞጁል) መጽሐፍ እና ማጣቀሻዎችን እንደ መመሪያና እንደ መርጃ ለመጠቀም ነጻነት ይኑርህ፤ ይህን በምታደርግበት ወቅት ግን የሌላን ሰው ምልከታ ከተዋስክ ወይም በዛ ምልከታ ላይ የራስህን ከመሰረትክ ለባለሃሳቡ ዕውቅና መስጠትን መዘንጋት የለብህም። ለዚህም የጽሁፍ ውስጥ ማጣቀሻዎችን፣ የግርጌ ማስታወሻዎችን፣ ወይም የመጨረሻ ማስታወሻዎችን ተጠቀም። የተጠቀምከው የማስታወሻ ዘዴ ተቀባይነት የሚኖረው 1) በጠቅላላው የጽሁፍ ስራህ ውስጥ ወጥነት ያለው ሲሆንና 2) የተጠቀምከውን የሌላን ሰው ሃሳብ በትክክል የሚያመለክት ሲሆንና ተገቢውን እውቅና ሲሰጥ ብቻ ነው ፡፡(ለተጨማሪ መረጃ ከአባሪዎች ገጽ ላይ Documenting Your Work : A guide to Help You Give Credit Where Credit is Due ተመልከት ፡፡) የትርጓሜ ጥናቱ (ኤክሴጄቲካል ፕሮጀክቱ) የሚከተሉትን መመዘኛዎች የሚያሟላ መሆኑን አረጋግጥ:- • በአግባቡ መጻፉን(ታይፕ መደረጉን) • ከላይ ከተሰጡት ምንባቦች የአንዱ ጥናት መሆኑን • ሳይዘገይ በቀኑና በሰኣቱ ገቢ መደረጉን • ርዘመቱ 5 ገጽ መሆኑን • ከላይ የተሰጠውን መመሪያ ተከትሎ መሰራቱንና አንባቢው በቀላሉ ተከትሎ ሊረዳው የሚችል መሆኑን • ምንባቡ ከህይወትና ከአገልግሎት ጋር ያላቸውን ዝምድና የሚያሳይ መሆኑን እነዚህን መመሪያዎች አይተህ አትደናገጥ፤ ይህ የመጽሀፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮጀክት ነው፤ ማድረግ የሚያስፈልግህ ምንባቡን በደንብ ማጥናት፤ ከምንባቡ ውስጥ ትርጉም መፈለግ፤ ከዚያም ቁልፍ የሆኑ መርሆዎችን ከምነባቡ ማውጣት እና መርሆዎቹንም ከህይወትና ከአገልግሎት ጋር ማዛመድ ናቸው፡፡ ይህ የትርጓሜ ጥናት (ኤክሴጄቲካል ፕሮጀክት) የ45 ነጥቦች ዋጋ ያለው ሲሆን ከጠቅላላው የዚህ ኮርስ ውጤት 15% ይይዛል፡፡ ስለዚህ በተቻለህ መጠን ስራህን የላቀና አስተማሪ አድርገሀ ለማቅረብ ሞክር፡፡ ለ. በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ካለህ አገልግሎት ጋር

ምዘና

1 2 /

እግዚአብሔር አብ

የሚኒስትሪ ፕሮጀክት የክርስቲያን መሪነት መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ማወቅ ብቻ አይደለም። ሌሎች እንዲታነጹ እና ለአገልግሎት እንዲዘጋጁ በሚያስችል መንገድ የእግዚአብሔርን ቃል መጠቀም መቻልን ይጨምራል። የእግዚአብሔር ቃል ሕያው እና የሚሰራ ነው፣ ወደ ህይወታችንና ወደ ልባችንም ሃሳብ ዘልቆ ይገባል (ዕብ. 4.12)። ሐዋሪያው ያዕቆብ የእግዚአብሔርን ቃል ሰሚዎች ብቻ ሳይሆን አድራጊዎችም መሆን እንደሚያስፈልገን ገልጿል። ቃሉን እንድንተገብር፣ እንድንታዘዘው ተመክረናል። ይህንን ተግሣጽ ችላ ማለት የተፈጥሮ ፊቱን በመስታወት ተመልክቶ መልኩን ከረሳ ሰው ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው ይጠቁማል። በማንኛውም ሁኔታ፣ የእግዚአብሔርን ቃል የሚያደርግ ሰው በሚሠራው ሁሉ ይባረካል (ያዕቆብ 1፡22-25)። እኛም መሻታችን የምንቀስመውን ትምህርት በግል ህይወትህ፣ በአገልግሎትህና በቤተክርስቲያንህ ውስት ካሉ ተጨባጭ ሁኔታዎችና ፍላጎቶች ጋር በማዛመድ በተግባር ስታውለው መመልከት ነው፡፡ ሥነ መለኮታዊ ጽሑፍ፡ ለጓደኛ የተላከ ደብዳቤ። ቃሉን ማገልገል ብዙውን ጊዜ ስብከት መስበክን ወይም መደበኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ማስተማርን ብቻ ሳይሆን ለጓደኛ፣ ለቤተሰብ አባል ወይም ለሥራ ባልደረባ ያመንከውን ለምን እንደምታምን መንገርንም ያካትታል። የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ስለ አስፈላጊ ሥነ-መለኮታዊ ርዕሰ ጉዳዮች መደበኛ ባልሆነ መንገድ የመናገር ችሎታህን እንድታሳድግ መርዳት ነው። በእግዚአብሔር ማንነት ዙሪያ ካሉ ጉዳዮችና በኢየሱስ ወደ ማመን ከመምጣት ጋር የሚታገል አንድ የምታውቀውን ሰው ወይም ምናባዊ ሰው አስብ። በእግዚአብሔር ማመን አስፈላጊና ትክክል የሆነበትን ምክንያት በመግለጽ ለዚህ ሰው ደብዳቤ ጻፍ። እያንዳንዱ ደብዳቤ በሚከተሉት መመዘኛዎች ይመዘናል፦

ዓላማ

እቅድ እና ማጠቃለያ

• በጥሩ ሁኔታ የተፃፈ ወይም የተተየበ፣ በሰዓቱ የቀረበ • ከሁለት እስከ አራት ገጾች ርዝማኔ ያለው መሆኑ • በዕለት ተዕለት የንግግር ቋንቋ ዘዬ የተጻፈ መሆኑ • ከቅዱሳት መጻሕፍት ግልጽ ማጣቀሻን መጠቀሙ • በክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር እንድናምን ጠንካራ ግብዣን ማድረጉ

ጽሑፍህ ለጓደኛህ የምትጽፈውን አይነት ባህላዊ የደብዳቤ መልክ የተከተለ መሆን አለበት። ደብዳቤህን ይህ ደብዳቤ ስለተጻፈለት ሰው በሚያወራ አጭር አንቀጽ ጀምር። ስለዚህ ሰው ጥቂት ዝርዝሮችን አቅርብ፡ ስለ እድሜው፣ ስለሚኖርበት ቦታ፣ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚያውቀው ነገር (ካለ)፣ አሁን ወይም ከዚህ ቀደም ስለነበረበት ሁኔታ፣ ወዘተ። ስለ ማንኛውም አይነት ሰው እና ሁኔታ ለማሰብ ነፃነት ይኑርህ። በደብዳቤህ ሐተታ ውስጥ፣ በእግዚአብሔር ስለማመን ለጓደኛህ ጉዳዩን አቅርብ። ምክንያቶችንም አቅርብለት፣ ምክንያቶችህንም በቅዱሳት መጻሕፍት አስደግፍ። አስፈላጊ ከሆነ ምን ዓይነት ተቃውሞዎች ሊኖሩት እንደሚችሉ አስበህ ከወዲሁ መልስ ስጥባቸው። አሳማኝ የሆነ አቀራረብ ይኑርህ! አስተውል፣ ይህ የግል ደብዳቤ እንጂ መደበኛ የአካዳሚክ ወረቀት አይደለም። ይህ የሚኒስትሪ ፕሮጀክት የ30 ነጥቦች ዋጋ ያለው ሲሆን ከጠቅላላው የዚህ ኮርስ ውጤት 10% ይይዛል፡፡ ስለዚህ ሃሳብህን በልበ ሙሉነት ማካፈልህንና ግልጽ የሆነ ማብራሪያ ማቅረብህን እርግጠኛ መሆን ይኖርብሃል፡፡

ምዘና

/ 1 3

እግዚአብሔር አብ

ፕሮሌጎሜና ትምህርተ እግዚአብሔር እና የመንግስቱ መስፋት

ትምህርት 1

ገጽ 253  1

ኃያል በሆነው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ለአንተ ይሁን ! የዚህን ትምህርት መጽሐፍ ካነበብክ፥ ካጠናህ፥ ውይይት ካካሄድክና ወደ ተግባር ከቀየርከው በኋላ የሚከተሉትን ማድረግ ትችላለህ:- • የመጀመሪያዎቹን ነገሮች፣ ፕሮሌጎሜና፣ ከትምህርተ እግዚአብሔር አብ መደበኛ ጥናት ጋር ወይም ከtheology proper ጋር በተያያዘ በትክክል ማጥናት ትችላለህ። • እኛ እርሱን ከማወቃችን በፊት እግዚአብሔር ራሱን መግለጡ አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነ መግለጽ ትችላለህ። • እግዚአብሔር በሁሉም ስፍራ ላሉ ሰዎች ሁሉ ራሱን ከሚገልጥበት መንገድ፣ አጠቃላይ መገለጥ እና እግዚአብሔር ራሱን ለተወሰኑ ሰዎች በተወሰኑ ጊዜያትና ቦታዎች ከሚገልጥበት መንገድ፣ ልዩ መገለጥ ጋር የተገናኙትን እውነቶች መረዳት ትችላለህ። • የኒቂያው የእምነት መግለጫ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት የሆነው አንድና እውነተኛ አምላክ ታላቅነት የሚገልጸው እንዴት እንደሆነ ማሳየት ትችላለህ። • የእግዚአብሔርን ፍፁምነት (ማለትም፣ የእግዚአብሔርን በፍጥረት ውስጥ መገኘት እና ያለውን ተሳትፎ) እና ምጡቅነት (የእግዚአብሔር ወሰን የሌለው ተፈጥሮ እና ታውቆ አለመጨረስ) ማስረጃን መስጠት ትችላለህ። • የእግዚአብሔርን ባሕሪያት ትርጉም፣ ችግራቸውንና ዓላማቸውን፣ እንዲሁም ተፈጥሮአቸውን እና ምደባቸውን ማብራራት ትችላለህ። ምንም ሰበብ አይፈቀድም ሮሜ. 1፥18-20 - እውነትን በዓመፃ በሚከለክሉ ሰዎች በኃጢአተኝነታቸውና በዓመፃቸው ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ቍጣ ከሰማይ ይገለጣልና፤ 19እግዚአብሔር ስለ ገለጠላቸው፥ ስለ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚቻለው በእነርሱ ዘንድ ግልጥ ነውና። 20የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤ ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ። ስለዚህ ያለ ሰበብ ናቸው። የኒቂያው የእምነት መግለጫ የሚጀምረው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ስለሆነው አንዱ እውነተኛ አምላክ ታላቅነት ግልጽ በሆነ መግለጫ ነው። “ሁሉን በሚችል፣ ሰማይንና ምድርን የሚታየውንና የማይታየውንም በፈጠረ በአንድ አምላክ እናምናለን” በሚል ሐረግ ይጀምራል። ይህ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በሁሉም ቦታ የተረጋገጠ የእውነት ማረጋገጫ ነው፡ የእግዚአብሔር

የትምህርቱ አላማዎች

ገጽ 253  2

ገጽ 253  3

1

ጥሞና

ገጽ 254  4

1 4 /

እግዚአብሔር አብ

ሕልውና በአጽናፈ ሰማይ እና በፍጥረቱ ግርማ ውስጥ በግልጽ ይታያል። ማህበረሰባችን ስለ እግዚአብሔር መኖር እና አለመኖር፣ ማለትም በእውነት በሰማይ አምላክ ስለመኖሩ ማውራት ቢወድም መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ዓይነት ክርክር ውስጥ አይገባም። በተቃራኒው የእግዚአብሔር ቁጣ በሰዎች በኃጢአተኝነታቸውና በዓመፃቸው ሁሉ ላይ ከሰማይ ይገለጣል ምክንያቱም ስለ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚችለውን ክደዋልና። እንደ ጳውሎስ አባባል የሰው ልጅ በስጋዊ ዓይኑ ሊያያቸው የማይችላቸው የማይታዩት የእግዚአብሔር ባሕርያት፣ ዘላለማዊ ኃይሉና መለኮታዊ ባሕርይው፣ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ግልጽ ተደርገዋል። ታላቁ አምላካችን የሠራቸው ነገሮች፣ ፀሐይና ጨረቃ፣ ከዋክብት በክብራቸው፣ ምድርም በታላቅነቷ፣ የእግዚአብሔር መኖር ብቻ ሳይሆን፣ ሁሉን ቻይ እና የከበረ መሆኑን ያሳያሉ። እንዴት ሰው ወፎችን በክንፍ ሲበርሩ አይቶ፣ አዲስ የተወለደ ሕፃን ጩኸት ሰምቶ፣ የከብት መንጋ በጠራራማ ሰማይ ሥር ባለው አስደናቂ አረንጓዴ መስክ ላይ ሲሰማራ አይቶ አምላክ የለም ሊል ይችላል? አንድ ሰው እንዴት የክረምቱን ምሽት ጥርት ያለ ነፋስ በፊቱ ላይ ሲነፍስ ሰምቶ፣ ጨረቃ ተውባ በድቅድቅ ጨለማ የፀደይ ምሽት ላይ ተንጠልጥላ አይቶ፣ ወይም ፈረስ በግርማው ሲጋልብ አይቶ ከዚህ ከአስደናቂው የምድር ውበት በስተጀርባ ምንም ፈጣሪ አእምሮ እንደሌለ እንዴት ሊያምን ይችላል? ወዳጄ ሆይ፣ ስለእግዚአብሔር መኖር በጣም አሳማኝ የሆነው መከራከሪያ አስተምህሯዊ ሳይሆን አካላዊ ነው። መዝ. 19፡1-3 - “ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል። ቀን ለቀን ነገርን ታወጣለች፥ ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ትናገራለች። ነገር የለም መናገርም የለም፥ ድምፃቸውም አይሰማም።” ንጹሕ የሆነው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በመንቀሳቀስ ላይ ነው፡ ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ በላይ ያለውም ሰማይ የእጁን ሥራ ያውጃል። ማንኛውም ምክንያታዊ የሆነ ሰው ከዚህ ክብር በስተጀርባ መለኮታዊ አካል እንዳለ አምኖ ለመቀበል የሚያስችለው ሁሉ በእግዚአብሔር ፍጥረት ውስጥ በበቂ ሁኔታ ተነግሯል። የከሃዲዎች እና ተጠራጣሪዎች ችግር በቂ ማስረጃ አለመኖሩ ሳይሆን የገዛ ልባቸው የደነደነ መሆኑ ነው። ንስሐ ለመግባት በቂ ማስረጃ አለ፣ ስለዚህም ተጠራጣሪው ወደ መሲሁ ላለመምጣት ምንም ሰበብ የለውም። የኒቂያን የእምነት መግለጫ (በአባሪው ውስጥ ይገኛል) ካነበብክ እና/ወይም ከዘመርክ በኋላ የሚከተለውን ጸሎት ጸልይ፥ አምላኬ ሆይ ታላቅነትህ ምድርን እና አጽናፈ ዓለሙን ሁሉ ይሞላል፣ አጽናፈ ዓለሙም ራሱ አንተን ሊይዝህ አይችልም፣ ከዚያም ያነሰው ምድር፣ እንዲሁም ከምድርም የሚያንሰው የእኔ የሃሳብ አለም።

1

የኒቂያ የእምነት መግለጫ እና ጸሎት

~ Yves Raguin, SJ. Appleton, George, ed. The Oxford Book of Prayer. Oxford; New York: Oxford University Press, 1988. p. 4

/ 1 5

እግዚአብሔር አብ

ሁሉን በጊዜና በቦታ የፈጠርህና ሰውን በመልክህ የፈጠርህ ኃያል አምላክ፡ በፈጠርከው ሁሉ ክንድህን እንድንገነዘብ እና ሁልጊዜም ስለ ጥበብህና ስለ ፍቅርህ እንድናመሰግንህ ምራን፤ ከአንተ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በሁሉም ነገር ላይ አሁን እና ለዘላለም በሚነግሥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል። ~ Church of the Province of South Africa. Minister’s Book for Use With the Holy Eucharist and Morning and Evening Prayer. Braamfontein: Publishing Department of the Church of the Province of South Africa. p. 12

ይህ ትምህርት ፈተና የለውም

ፈተና

1

የቃል ጥናት ጥቅስ ምዘና

ይህን ትምህርት የቃል ጥናት ጥቅስ የለውም

የቤት ስራ/መልመጃ ማስረከቢያ

ይህ ትምህርት የቤት ስራ/መልመጃ የለውም

እውቂያ

“አምላክ አንድ ብቻ ነው - አላህ” የእስልምና ሐገር አባል የሆነን (በሉዊ ፋራካን የሚመራው የጥቁሮች ሙስሊሞች ቡድን) በመንገድ ላይ ጋዜጣ ሲሸጥ አጋጥሞህ፣ ለአፍታ ከእርሱ ጋር ለመነጋገር ቆመሃል። ርዕሰ ጉዳዩ ወደ እግዚአብሔር ማንነትና አምላክነት ሲዞር፣ አይነ ብሩኁ ወጣት የእስልምና እምነት ተከታይ “ከአላህ ሌላ አምላክ የለም፣ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረው እርሱ ብቻ ነው” ይላል። ለእርሱ አስተያየት ምን ምላሽ ትሰጣለህ? “ያኔ የት ነበር?” በሰንበት ትምህርት ቤት ስለአይሁድ ሕዝብ በአሦርና በባቢሎን በምርኮ መወሰድና ስለሚደርስባቸው መከራ ስትነጋገሩ ከታዳጊ ወጣቶቹ አንዱ “ሁልጊዜ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንዳለና እኛንም እንደወደደን እንናገራለን፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ከሆነና የሚንከባከበው ከሆነ፣ ታዲያ ለምን የራሱን ሕዝብ እንዲጎዳና እንዲንገላታ ፈቀደ? ያኔ የት ነበር?” ሲል ጠየቀ። የክፍሉ መምህር እንደመሆንህ፣ የዚህን ተማሪ አስፈላጊ ጥያቄ እንዴት ትመልሰዋለህ?

1

ገጽ 254  5

2

1 6 /

እግዚአብሔር አብ

“እኔ እንጃ” በቅርቡ ከትናንሽ ልጆቿ መካከል አንዷን በሉኪሚያ ያጣችው ወጣት እናት በድብርት እየተሰቃየች ነው። ደጋግማ በሞከረች መጠን፣ አምላክ የለም፣ ወይም ደግሞ እርሱ በርግጥ ካለ አፍቃሪ ሊሆን አይችልም ብሎ የማሰብ ፈተናን ማሸነፍ የቻለች አትመስልም። ለምንድነው ውዷ ትንሿ ማርታን ለረጅም ጊዜ እንድትሰቃይ እና በህጻንነቷ እንድትሞት የፈቀደው? የልቧን ነገር ስታካፍልህ፣ “ስጸልይ፣ መጽሐፍ ቅዱሴን ሳነብ፣ በሌሊት ሰማይን ስመለከት ብቸኝነት ይሰማኛል፣ የምሄድበት ሰባኪና አማካሪ ምን እንደሚሉ አውቃለሁ፣ ነገር ግን አንዳቸውም ቢሆኑ ለምን እንደሆነ እንድገነዘብ አልረዱኝም፣ እግዚአብሔር የሚወደን ከሆነ ይህ ለምን ሆነብን? በርግጥ እግዚአብሔር እውን ነውን? በርግጥስ እግዚአብሔር አፍቃሪ ነውን? እኔ እንጃ።” ለዚህች ውድ ወጣት እህት ግንዛቤ እንዲኖራት ላቀረበችው ጥያቄ ምን ምላሽ ትሰጣለህ?

3

1

ፕሮሌጎሜና፡ ትምህርተ እግዚአብሔር እና የመንግሥቱ መስፋት ሴግመንት 1፡ እግዚአብሔር አለን? ራሱንስ ይገልጣልን?

ይዘት

ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ

በዚህ ሴግመንት በአጠቃላይ እና በልዩ መገለጥ አማካኝነት እግዚአብሔር ራሱን ለሰው ልጆች የመግለጡን ሉዓላዊ ዓላማ እንመረምራለን። የዚህ እግዚአብሔር አለን? ራሱንስ ይገልጣልን? የተሰኘ ሴግመንት ዓላማ፣ የሚከተሉትን እንድታይ ለማስቻል ነው፡- • ፕሮሌጎሜና፣ “የመጀመሪያ ነገሮች”፣ የነገረ መለኮት ትክክለኛ ጥናት (የአምላክ ጥናት)፣ እግዚአብሔርን ማወቅ ከፈለግን እግዚአብሔር ራሱን ሊገልጥልን እንደሚገባ ይጠቁማል። እርሱ ራሱን ካልገለጠልን ማንም ሊያውቀው አይችልም። • እግዚአብሔር ራሱን በሁለት ተያያዥ መንገዶች ማለትም በአጠቃላይና በልዩ መገለጥ ለሰው ልጆች ገልጧል። • በአጠቃላይ መገለጥ እግዚአብሔር በሁሉም ስፍራ ላሉ ሰዎች ሁሉ ራሱን ይገልጣል፣ በልዩ መገለጥ ደግሞ እግዚአብሔር ራሱን ለተወሰኑ ሰዎች በተወሰነ ጊዜና ቦታ ይገልጣል።

የሴግመንት 1 ማጠቃለያ

ገጽ 255  6

/ 1 7

እግዚአብሔር አብ

I. ፕሮሌጎሜና (ሲነበብ እንደ PRAW-ley-gaw-men-uh ነው)፡- ስለ አምላክ ለማጥናት መነሻ መሰረት ሥነ-መለኮት ማለት “የአምላክ ጥናት” ማለት ነው።

የቪዲዮ ሴግመንት 1 መግለጫ

(“ቴኦስ” = አምላክ፣ “ሎጎስ” = የአንድ ነገር ጥናት፣ ቃል)

ዮሐንስ 17፡3 “ እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።”

ሀ. ክርስትና እግዚአብሔር እንዳለ እና ራሱን ካልገለጠልን በቀር እግዚአብሔር የማይታወቅ ነው ብሎ ያምናል።

1

1. እግዚአብሔር በራሱ እንዳለ የማይታወቅ ነው፣ 1ጢሞ. 6፡13-16።

ሀ. ራሱን ሊገልጥልን የሚችለው እግዚአብሔር ራሱ ብቻ ነው፣ እንደዛ ካልሆነ ማንም ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት መፍጠር አይችልም። (1) ዘጸ. 33.20

(2) ዮሐንስ 1፡18

(3) ዮሐንስ 6፡46

ለ. ለእኛ የገለጠልንን መገለጥ በትክክል ሊተረጉም የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው። (1) ዮሐንስ 1፡18

(2) ማቴ. 11.27

2. እግዚአብሔር በታሪክ (በፍጥረት፣ በቤዛነት፣ በቅዱሳት መጻሕፍት እና በኢየሱስ) በፍጥረት ሥራው እና በቤዛነት ራሱን መግለጥ መርጧል።

ሀ. በፍጥረት በኩል

(1) መዝ. 19፡1-3

(2) ኤር. 10፡11-12

1 8 /

እግዚአብሔር አብ

ለ. በታሪክ፣ የሐዋርያት ሥራ 14፡15-17

3. እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ስለ ሕልውናው የማወቅ ችሎታዎችን ሰጥቷቸዋል፣ ሮሜ. 1.18-20.

4. ስለ እግዚአብሔር የማወቅ ጉጉት በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእርሱ ጋር አዲስ ህብረት እንዲኖረን ይጠይቃል እንጂ ስለ እርሱ ያሉትን ሐሳቦችና ጽንሰ ሐሳቦች በአእምሮ ማጥናት ብቻ በቂ አይደለም።

1

ሀ. 1ኛ ዮሐንስ 5፡20

ለ. 2 ቆሮ. 4.6

ለ. ስለ አምላክ ጥናት አንድምታዎች

ገጽ 255  7

1. እግዚአብሔርን እና ማንነቱን ለማወቅ ምክንያታዊነት እና ጥናት በቂ አይደሉም። እግዚአብሔርን ለማወቅ ምክንያታዊነት የመንፈስን ብርሃን ይጠይቃል።

2. እግዚአብሔርን በኢየሱስ ክርስቶስ ለማወቅ ዳግመኛ መወለድ (ዳግም ልደት) አለብን።

ሀ. በሥነ-መለኮት ጥናት ውስጥ የአእምሯዊ ዝግጅት እና ሳይንሳዊ ዘዴዎች ብቻቸውን ውስን ናቸው።

ለ. እግዚአብሔርን በደንብ ለማጥናት እግዚአብሔርን በግል ማወቅ አለብህ።

/ 1 9

እግዚአብሔር አብ

3. ሥነ-መለኮት ስለ መገለጥ ነጸብራቅ ነው፣ የሰው ልጅ ስለ እግዚአብሔር ማንነት እና መገለጥ የሚያስበው ሃሳብ ማለት ነው።

ሀ. ባህላችን ስለ እግዚአብሔር ባለን አስተሳሰብ ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር መንቃት አለብን።

ለ. ያለ መንፈስ ቅዱስ እርዳታ ስለ እግዚአብሔር በራሳችን አተያይ ብቻ ማመን የለብንም።

1

ሐ. ብዙ የሥነ-መለኮት አይነቶች ቢኖሩም የትኛውም ሥነ-መለኮት እግዚአብሔርን ሙሉ በሙሉ አያብራራም።

መ. ትህትና ለሥነ-መለኮት ጥናት መሰረታዊ ነገር ነው።

4. ከቅዱሳት መጻሕፍት እና ከቤተክርስቲያን የሚመጡ ተአማኒ የሆኑ የስነ-መለኮት ጉዳዮች፡ ነገረ መለኮት ማለት በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ዋና በሆነው የእግዚአብሔር መገለጥ ላይ የምታንፀባርቅ ቤተክርስቲያን ማለት ነው።

5. ሥነ መለኮት ሌሎች የትምህርት ዘርፎችን ሊያማክል ይችላል፥ ይሁን እንጂ እነዚያን ትምህርቶች በፍጹም መከተል የለበትም፣ እግዚአብሔር ብቻ በመንፈሱ በቅዱሳት መጻሕፍት ሊገለጥልን ይችላል።

II. ሉዓላዊው አምላክ ራሱን ይገልጥልናል፡ አጠቃላይ እና ልዩ መገለጥ አጠቃላይ መገለጥ፡- “እግዚአብሔር ሁል ጊዜ በሁሉም ቦታ ለሁሉም ሰው የሚናገረው።” ልዩ መገለጥ፡- “ለተወሰኑ ሰዎች በተወሰኑ ጊዜያት የእግዚአብሔር ልዩ ንግግሮች እና መገለጫዎች፣ አሁን የሚገኙት የተወሰኑ ቅዱሳት መጻሕፍትን [ማለትም፣ መጽሐፍ ቅዱስን] በመመልከት ብቻ እግዚአብሔር ራሱን የሚገልጥባቸው ግንኙነቶች እና መገለጫዎች ናቸው።

~ Millard Erickson, Introducing Christian Doctrine, 2nd Ed. Grand Rapids: Baker Book House, 2001. p. 42

2 0 /

እግዚአብሔር አብ

ሀ. አጠቃላይ መገለጥ ፡- እግዚአብሔር በፍጥረት፣ በሰው ልጅ ታሪክ እና በሰው ልጅ ውስጣዊ አቅም ለሁሉም ፍጡራን ራሱን መግለጡ

1. እግዚአብሔር በፍጥረትና በተፈጥሮ ውስጥ ራሱን ገልጧል።

ሀ. መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ (1) ኢሳ. 40.25-26

(2) ሮሜ. 1.18-20

1

(3) የሐዋርያት ሥራ 14፡15-17

(4) የሐዋርያት ሥራ 17፡24-31

ለ. ለናቹራል ቲዎሎጂ ፍልስፍናዊ ክርክሮች፡ ቶማስ አኩዊናስ (1) ኮስሞሎጃዊ ማስረጃ፡- እግዚአብሔር እንደ መጀመሪያው ምክንያት አልባው ምክንያት (2) ቴሌዮሎጂካዊ ማስረጃ፡- እግዚአብሔር የአጽናፈ ሰማይ ሥርዓትና ዓላማ ባለቤት ነው። (3) አንትሮፖሎጂካዊ ክርክር፡- የነገሮች ሥነ ምግባራዊ ሥርዓት የእግዚአብሔርን መኖር እና በድርጊታችን ላይ መፍረዱን ይጠይቃል። (4) ኦንቶሎጂካዊ ክርክር (Anselm)፡- እግዚአብሔር ሊታሰብ ከሚችሉ ፍጥረታት ሁሉ የላቀ ነው።

2. እግዚአብሔር በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ራሱን ገልጧል።

ሀ. የእግዚአብሔር ልዩ ሕዝብ፣ የእስራኤል መጠበቅ

ለ. በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የእግዚአብሔር የማዳን ሥራ፡ የኢየሱስ ታሪክ፣ የሐዋርያት ሥራ 2፡22-23 (1) ሂስቶሬ ፡ ትክክለኛው የሰው ልጅ ታሪክ

/ 2 1

እግዚአብሔር አብ

(2) ሄልስጌስቺክት ፡- ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት የሚያመራ በእስራኤል ህዝብ መካከል እግዚአብሔር ያከናወነው ታሪካዊ ሥራ

3. እግዚአብሔር ራሱን በሰው ልጆች ውስጥ ገልጧል።

ሀ. ምክንያት፣ ኢሳ. 1.18

ለ. የሥነ ምግባር ፍርድ፡ ሕሊና፣ ሮሜ. 2.15

1

ሐ. ኃይማኖታዊ ተፈጥሮ፡ ሁሉም የሰው ልጅ ባህሎች ስለ መለኮት የተወሰነ ግንዛቤ አላቸው። (1) መዝ. 10.4

(2) መዝ. 73.3

ለ. ልዩ መገለጥ ፡ እግዚአብሔር ራሱን ለተወሰኑ ሰዎች በተወሰነ ጊዜና ቦታ ገልጧል

1. ልዩ መገለጥ ግላዊ ነው (እግዚአብሔር ራሱን እየገለጠልን ነው)።

ሀ. እኔ እኔ ነኝ፣ ዘጸ. 3፡14-15።

ለ. የአብርሃም፣ የይስሐቅ እና የያዕቆብ አምላክ (1) ዘጸ. 3.6

(2) ዘጸ. 4.5

2. ልዩ መገለጥ አንትሮፒክ ነው። (አንትሮፖሎጂ = “አንትሮፖስ” ሰው፣ “ሎጎስ” ጥናት)፡ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ለመገናኘት የሰው ቋንቋ እና ቅርጾችን ይጠቀማል።

ሀ. በሰው ቋንቋና ልማድ፣ 1ኛ ቆሮ. 2፡12-13

2 2 /

እግዚአብሔር አብ

ለ. በኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት (1) ዮሐንስ 1፡14

(2) ዮሐንስ 1፡18

(3) ሉቃስ 10፡22

3. ልዩ መገለጥ አናሎጂያዊ ነው። (እግዚአብሔር እርሱ ማን እንደሆነና ከእሱ ጋር ያለን ግንኙነት ምን እንደሚመስል ለማሳየት ምሳሌዎችን ይጠቀማል።)

1

ሀ. ተመሳሳይነት = አንድን ነገር ከሌላው ነገር ጋር በማነፃፀር እንድንረዳ ይጋብዘናል፡- ሀ ከ ለ ጋር ተመሳሳይ እንደሆነው፣ እንዲሁ ሐ ደግሞ ከ መ ጋር ተመሳሳይ ነው። (1) ዮሐንስ 10፡9

(2) ዮሐንስ 10፡14-15

ለ. እግዚአብሔር ለማነጻጸር አንዳንድ ክፍሎችን ይመርጣል፣ እንድንገነዘብም ግንኙነታቸውን ይጠቁመናል።

ሐ. እርሱ በፅንሰ-ሀሳቦች ወይም ሃሳቦች ብቻ ሳይሆን (ለምሳሌ፣ ኢየሱስ የይሁዳ አንበሳ ነው) ከመላው ሰው ጋር ይገናኛል።

4. ልዩ መገለጥ ተጨባጭ ነው።

ሀ. በታሪካዊ ክስተቶች (ለምሳሌ፣ የአብርሃም ጥሪ)፣ ዘፍ. 12.1-3

ለ. በመለኮታዊ ንግግር፣ ለምሳሌ፣ ዕብ. 1.1-2

ሐ. በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ፣ 1ኛ ዮሐንስ 1፡1-3

/ 2 3

እግዚአብሔር አብ

መደምደሚያ

» እንድናውቀው ካስፈለገ እግዚአብሔር ራሱን ሊገልጥልን ይገባል።

» እግዚአብሔር ራሱን በሁለት ልዩ ዘይቤዎች ወይም መንገዶች ይገልጥልናል፡ በአጠቃላይ መገለጥ፣ እግዚአብሔር በሁሉም ስፍራ ላሉ ሰዎች ሁሉ ራሱን ይገልጣል፣ በልዩ መገለጥ ደግሞ እግዚአብሔር ራሱን ለተወሰኑ ሰዎች በተወሰነ ጊዜና ቦታ ይገልጣል።

እባክህ በእነዚህና በሌሎችም በዚህ ቪዲዮ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች በቂ ጊዜ ወስደህ ምላሽ ለመስጠት ሞክር፡፡ እግዚአብሔር ራሱን ለእኛ የመግለጡ አስፈላጊነት እና የአጠቃላይ እና የልዩ መገለጥ ተፈጥሮ በእግዚአብሔር አብ ጥናታችን ውስጥ ማዕከላዊ ጉዳዮች ናቸው። መልሶችህ ግልጽ እና አጭር ይሁኑ፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ በቅዱሳት መጻሕፍት አስደግፍ! 1. “ፕሮሌጎሜና” የሚለው ቃል ምን ማለት ነው? ስለ እግዚአብሔር ማንነት እና ሥራ መደበኛ ጥናት ውስጥ ከመግባትህ በፊት በመጀመሪያ ግምቶችህን ግልጽ ማድረግ አስፈለጊ የሆነው ለምንድነው? 2. አንድ ሰው እግዚአብሔርን በራሱ መንገድ እና በብርታቱ ማወቅ የማይችለው ለምንድን ነው? 3. በአምላክ ጥናት ውስጥ ምክንያታዊነት እና ምርምር ምን ሚና አላቸው? አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር ሙሉ እውቀት እንዲኖረው ለመርዳት በራሳቸው በቂ የማይሆኑት ለምንድነው? 4. እግዚአብሔርን እንድናውቅ ከመርዳት አንጻር የመንፈስ ቅዱስ ድርሻ ምንድን ነው? 5. አጠቃላይ መገለጥ ምንድን ነው? እግዚአብሔር በሁሉም ስፍራ ለሰው ልጆች ሁሉ ራሱን የገለጠው በምን አይነት ልዩ ልዩ መንገዶች ነው? ይህ አይነቱ የእግዚአብሔር እውቀት ለመዳን በቂ ነው? መልስህን አስረዳ። 6. ልዩ መገለጥ ምንድን ነው? የልዩ መገለጥ ባህሪያት ምንድናቸው? እግዚአብሔር ራሱን ለሰው ልጆች የገለጠበት ከሁሉ የበለጠ ግልጽ እና ብርቱው መንገድ የትኛው ነው? 7. በአጠቃላይም ይሁን በልዩ መገለጥ እግዚአብሔር ራሱን ለእኛ ሊገልጥልን ለምን አስፈለገ? ከአምላክ ጥናት ረገድ ምንጊዜም አመለካከታችን ምን መሆን አለበት?

መሸጋገሪያ 1

1

የተማሪው ጥያቄዎች እና ምላሾች

ገጽ 256  8

2 4 /

እግዚአብሔር አብ

ፕሮሌጎሜና፡ ትምህርተ እግዚአብሔር እና የመንግሥቱ መስፋት ሴግመንት 2፡ እግዚአብሔር ሊታወቅ ይችላልን?

ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ

ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ አምላክ እንደመሆኑ፣ አብ በአጽናፈ ዓለም ውስጥ በሁሉም ቦታ የሚገኝ እና የሚሰራ ነው (ማለትም፣ እግዚአብሔር ህልው ነው)፣ እንዲሁም ከነገሮች እና ከፍጥረታት ሁሉ በላይ (ማለትም፣ እግዚአብሔር ምጡቅ ነው)። በሥነ-መለኮት ውስጥ፣ የእግዚአብሔርን ባህሪያት፣ የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ ታላቅነት እና መልካምነት የሚገልጹትን ባህሪያት እናጠናለን። የዚህ እግዚአብሔር ሊታወቅ ይችላልን? የተሰኘ ሴግመንት ዓላማ፣ የሚከተሉትን ማየት እንድትችልል ለማስቻል ነው፡- • እግዚአብሔር የሁሉም ነገር ፈጣሪ እና አድራጊ እንደመሆኑ መጠን ከአጽናፈ ዓለሙ ጋር ልዩ የሆነ ዝምድና አለው ይህም በሁሉንቻይነቱ እና በምጡቅነቱ ሊገለጽ ይችላል። • የእግዚአብሔር ህልውና በፍጥረቱ ሁሉ መካከል ያለውን ያልተቋረጠ ንቁ ተሳትፎን ያመለክታል። • በሌላ በኩል፣ የእግዚአብሔር ልዕልና ማለቂያ የሌለውን የእግዚአብሔርን ተፈጥሮ እና ታውቆ የማይደረስበት መሆኑን ያመለክታል። • የእግዚአብሔር ባሕርያት የአምላከ ስላሴን፣ የአብ፣ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ ባህሪያትን ያመለክታሉ። • የእግዚአብሔርን ባህሪያት ከእግዚአብሔር ታላቅነት እና ቸርነት አንጻር ልንመድባቸው እንችላለን። • የእግዚአብሔር የታላቅነቱ ባህሪያት መንፈሳዊነት፣ ህይወት፣ ስብዕና፣ ማለቂያ የለሽነትል እና ቋሚነት ናቸው። • የእግዚአብሔር የመልካምነት ባህሪያት ደግሞ የሞራል ንጽህና፣ ጽኑ አቋም እና ፍቅርን ያካትታሉ።

የሴግመንት 2 ማጠቃለያ

ገጽ 256  9

1

/ 2 5

እግዚአብሔር አብ

I. የእግዚአብሔር ህልውና እና ልዕልና

የቪዲዮ ሴግመንት 2 መመሪያ

ሀ. ትርጓሜዎች፡- እነዚህ አጽንዖቶች እግዚአብሔር ከፈጠራቸው ከሰማይና ከምድር፣ እንዲሁም ከሚታዩና ከማይታዩት ነገሮች ሁሉ ጋር ካለው ግንኙነት ጋር የተያያዙ ናቸው።

የካፕስቶን ሥርዓተ ትምህርታችን ሥነ-መለኮታዊ መሠረት ሆኖ የሚያገለግለው የኒቂያው የእምነት መግለጫ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እና አባት ስለሆነው አንዱና እውነተኛው አምላክ ታላቅነት ግልጽ በሆነ መግለጫ ይጀምራል። “ሁሉን

1. የእግዚአብሔር ህልውና = እግዚአብሔር በአጽናፈ አለም ውስጥ በሁሉም ስፍራ ይገኛል፣ ይሠራልም።

1

በሚችለው፣ ሰማይንና ምድርን የሚታየውንና የማይታየውንም ሁሉ በፈጠረ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ

2. የእግዚአብሔር ልዕልና = የእግዚአብሔር ማንነት ከፍጥረት ሁሉ የላቀ እና ከእርሱ ከራሱ ውጭ ማንኛውም ፍጡር እርሱን የመረዳት አቅም የሌለው ነው።

እናምናለን” በሚለው ሐረግ ይጀምራል።ይህ አረፍተ ነገር የሚያጎላው የእግዚአብሔርን ልዕልና እና ህልውና ነው።

ለ. የእግዚአብሔር ህልውና

1. እግዚአብሔር በፍጥረት መካከል ይገኛል፣ ይሰራልም።

ሀ. ኤር. 23፡23-24

ለ. መዝ. 135.5-7

2. እግዚአብሔር በፍጥረት መካከል ይገኛል፣ ይሰራልም።

ሀ. መዝ. 139.1-10

ለ. ዳንኤል. 4.35

3. የእግዚአብሔር ህልውና አንድምታ

2 6 /

እግዚአብሔር አብ

ሀ. እግዚአብሔር በአለም ላይ ፈቃዱን ለማድረግ በአጠቃላይ ተደራሽና ሁለንተናዊ የሆኑ መንገዶችን ሊጠቀም ይችላል።

ለ. እግዚአብሔር ፈቃዱን ለመፈጸም ማንኛውንም ነገር እና ማንንም የመጠቀም ነፃነት አለው።

ሐ. የእግዚአብሔር ፍጥረት ሁሉ ክብሩንና እጁን ይገልጣል።

1

መ. ፍጥረት ለሰው ልጆች (በአንድ ደረጃ) የእግዚአብሔርን እውነተኛ እውቀት ይሰጣል።

ሠ. እግዚአብሔር የሁሉም ነገር ፈጣሪ ስለሆነ በሁሉም ህዝቦች ዘንድ እና መካከል የግንኙነት ነጥቦች አሉ።

ሐ. የእግዚአብሔር ልዕልና

1. እግዚአብሔር ከፈጠራቸው ነገሮች ሁሉ በላይ እና ምጡቅ ነው፡ በእርሱ እና ለክብሩ ብቻ ተፈጥረዋል።

ሀ. 1ኛ ነገሥት 8፡27

ለ. 2ኛ ዜና. 6.18

ሐ. ነህ. 9.6

መ. ኢሳ. 66.1

/ 2 7

እግዚአብሔር አብ

2. እግዚአብሔር በሰዎች ጥረት እና ተግባር ሊታወቅ አይችልም፤ ክብሩ እና ማንነቱ ከሰው ልጆች መረዳት እና ልምምድ ወሰን በላይ ናቸው።

ሀ. ዘዳ. 10.14

ለ. መዝ. 113.4-6

3. የእግዚአብሔር ሉዓላዊነት አንድምታ

1

ሀ. የሰው ልጅ ሕይወት በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ከፍተኛው ማንነት/ስብዕና ሆኖ አያውቅም።

ለ. እግዚአብሔር ሥነ መለኮት ወይም ሌላ ትምህርት ስለ እርሱ በሚፈጥሯቸው ጽንሰ-ሐሳቦች ሊገደብ ወይም ሊያዝ አይችልም።

ሐ. እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ከአገዛዙ ስር የሚያደርገው ለእኛ መዳን እና በመጨረሻም ለክብሩ ብቻ ነው።

መ. እግዚአብሔር sui generis የሆነ ማንነት ነው (ማለትም፣ የሚመስለው የሌለ)። ሌላ ፍጡር ወደ ሙሉ ክብሩ ሊደርስ አይችልም።

ሠ. እግዚአብሔር ከሁሉም እና ከምንም ነገር በላይ ሊፈራ ይገባዋል።

ረ. እግዚአብሔር ከእኛ እና ከሀሳባችን በላይ በሁሉም ነገር እንደሚልቅ መጠበቅ አለብን።

2 8 /

እግዚአብሔር አብ

II. የእግዚአብሔርን ማንነት በማጥናት ውስጥ የሚያጋጥመን ፈተና፡ የእግዚአብሔርን ባሕርያት በማጥናት ውስጥ ያለው ችግር እና ዓላማ

ሀ. የእግዚአብሔር አንድነት እና የእግዚአብሔር ባህሪያት

1. የእግዚአብሔር ባህሪያት ትርጓሜ = “የእግዚአብሔርን ማንነቱን የሚያመለክቱ ባሕርያት ናቸው፣ እነዚህም የተፈጥሮው ባህሪያቱ ናቸው።” Erickson, Introducing Christian Doctrine, p. 89.

1

2. የአንዱ አምላከ ሥላሴ ባሕርይ የተዋሃደ እና ሙሉ ነው።

ሀ. የእግዚአብሔር ተፈጥሮ (ለጥናት ሲባል ብቻ) ለትንተና እና ለአምልኮ ብቻ ሲባል ሊለያይ ይችላል።

ለ. እግዚአብሔር ራሱ በፈቃዱና በሥራው ሁሉ ከስላሴ አካላት ጋር በመተባበር ሁሉንም ባህሪያቱን ፍጹም በሆነ መልኩ የሚለማመድ ማንነት ያለው ነው።

3. ችግር፡- የእግዚአብሔርን ልዩ ልዩ ባህሪያቱን በመመርመር መላ ባህርይውን በትክክል ልንረዳው እንችላለን?

ሀ. እግዚአብሔር አንድ ነው። (1) ዘዳ. 6.4

(2) ዘዳ. 4.35

(3) ኢሳ. 42.8

(4) ኢሳ. 44.6

(5) ኢሳ. 44.8

(6) ኤር. 10.10

/ 2 9

እግዚአብሔር አብ

ለ. የእግዚአብሔር ባህሪያት ሁሉም የተሳሰሩ ናቸው።

ሐ. ማንም ሰው የእግዚአብሔርን ማንነት በልቶ ማጥናት አይችልም።

መ. ስለ እግዚአብሔር በምናደርገው ትንታኔ “ሪዳክሽን” (ለአንዱ ባህሪ አፅንዖት በመስጠት ሌሎችን ለመረዳት መሞከር ወይም ማቃለል) እንጠቀማለን።

4. ችግሩን ማሸነፊያ መንገዶች

1

ሀ. በውሳኔዎችህ ጥንቃቄ አድርግ

ለ. የቅነሳ (reduction) ዝንባሌን ተገንዘብ

ሐ. ስለ እግዚአብሔር በምትናገረው ሁሉ ትህትና ይኑርህ።

ለ. የእግዚአብሔርን ባሕርያት የማጥናት ዓላማ

1. ለመተማመን እና ለማመን የእግዚአብሔርን ፍጽምና ለማሰላሰል፣ መዝ. 40.4-5

2. ስለ ኃያል ባህሪው የእግዚአብሔርን አሳብ እንደ እርሱ ለማሰብ፣ ዮሐ 14፡26

3. በፍጥረት እና በኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ክብር ለማወቅ

ሀ. ዮሐንስ 17፡3

ለ. ማቴ. 11፡25-27

3 0 /

እግዚአብሔር አብ

4. እግዚአብሔርን ለሌሎች ለማስተዋወቅ መዝ. 71፡17-19

ዛሬ ቤተክርስቲያን ላይ ያለው በጣም ከባዱ ግዴታ ስለ እግዚአብሔር ያላትን ፅንሰ-ሀሳብ ለእርሱም ሆነ ለራሷ በሚገባ መልኩ እስኪሆን ድረስ ማጥራት እና ከፍ ማድረግ ነው። በጸሎቷ እና በድካሟ ሁሉ ይህ የመጀመሪያ ቦታ ሊኖረው ይገባል። እኛ ካለፉት የዕብራውያን እና የክርስትና አባቶቻችን የተቀበልነውን ያንን የተከበረውን ስለ እግዚአብሔር የሆነ መረዳት ሳይደበዝዝ እና ሳይቀንስ በማስተላለፍ ለሚመጣው የክርስቲያን ትውልድ ትልቁን አገልግሎት እናበረክታለን። ይህ ማንኛውም ጥበብ ወይም ሳይንስ ሊፈጥሩላቸው ከሚችሉት ከማንኛውም ነገር የበለጠ ዋጋ እንደሚያስገኝላቸው ያረጋግጣል። ~ A.W. Tozer. The Knowledge of the Holy . New York: Harper San Francisco, 1961. p. 4.

III. የአምላክ ጥናት ውቅር፡ የእግዚአብሔር ባህሪያት ተፈጥሮ እና ምደባ

ሀ. የእግዚአብሔር ባህሪያት ተፈጥሮ

1. ባህሪያቱ የአምላከ ስላሴን ሁለንተናዊ መለኮታዊ ባህሪያት ያንፀባርቃሉ።

1

ሀ. ከተለያዩ የስላሴ አካላት ጋር ከሚዛመዱት ተግባራዊ ባህሪያት ጋር አንድ አይነት አይደሉም።

ለ. ከስላሴ አካላቱ ተግባራት ወይም ድርጊቶች ጋር ተመሳሳይ አይደሉም፣ ከእያንዳንዱ የስላሴ አካል ባህሪያት ጋር ይለያያሉ።

2. የእግዚአብሔር ባህርያት ውስጣዊ የሆኑ ቋሚ ባሕርያቱ ናቸው።

3. ባህርያቱ ስለ እግዚአብሔር ማንነትና ምንነት ይናገራሉ።

ለ. የእግዚአብሔር ባህሪያት ምደባ

1. የእግዚአብሔር ታላቅነት (እነዚህ ከእግዚአብሔር ግርማ ጋር የተያያዙ ባህሪያቱ፣ እግዚአብሔር በአምላክነቱ፣ በሥነ መለኮት ጥናት ውስጥ “ተፈጥሯዊ ባሕርያት” ይባላሉ)

ሀ. መንፈሳዊነት

ለ. ህይወት

/ 3 1

እግዚአብሔር አብ

ሐ. ስብዕና

መ. ፍፃሜ የለሽነት

ሠ. ቋሚነት

2. የእግዚአብሔር መልካምነት (እግዚአብሔር የሰው ልጆችን ጨምሮ ከፍጥረቱ ጋር ካለው ግንኙነት ጋር የተቆራኙት ባህሪያቱ፣ በሥነ መለኮት ጥናት ውስጥ “የሥነ ምግባር ባሕርያት” ይባላሉ)

1

ሀ. የሞራል ንፅህና

ለ. ታማኝነት

ሐ. ፍቅር

ማጠቃለያ

» እግዚአብሔር የሁሉ ነገር ፈጣሪ እና አድራጊ እንደመሆኑ መጠን ከአጽናፈ ዓለሙ ጋር በህልውናው እና በልዕልናው ይዛመዳል። » በፍጥረት ውስጥ ህልው የሆነ አምላክ እንደመሆኑ መጠን በአጽናፈ ዓለሙ ውስጥ የሚገኝ እና የሚሰራም ነው። » እግዚአብሔር ልዕለ-ኃያል እንደመሆኑ መጠን ወሰን የለውም፣ እንድናየውና እንድናውቀው ካልረዳንም በቀር ሊታወቅ እና ሊደረስበት አይችልም። » የእግዚአብሔር ባህሪያት የእግዚአብሔርን ታላቅነት እና መልካምነት የሚያመለክቱ ባህሪያቱ ናቸው።

3 2 /

እግዚአብሔር አብ

የሚከተሉት ጥያቄዎች በሁለተኛው የቪዲዮ ሴግመንት ውስጥ ያለውን ሐሳብ እንድትገመግም ለመርዳት ታስበው የተዘጋጁ ናቸው። የኒቂያው የእምነት መግለጫ እንደሚያመለክተው አንድ አምላክ ብቻ አለ፣ እርሱም ሁሉን ቻይ የሆነው፣ ሰማይንና ምድርን፣ የሚታየውንና የማይታየውንም ሁሉ የፈጠረ እግዚአብሔር አብ ነው። በፍጥረቱ መካከል እንደሚገኝና እንደሚሰራ እንዲሁም ከፍጥረቱ ሁሉ የመጠቀ ልዕለ-አምላክ እንደመሆኑ መጠን ባህሪያቱን ከታላቅነቱ እና ከመልካምነቱ አንፃር ልንረዳው ይገባል። ቀጥሎ በቀረቡት ጥያቄዎች ላይ ስታሰላስል፣ መልሶችህን ቀላል እና ቀጥተኛ ለማድረግ ሞክር፣ አስፈላጊ ሲሆን ደግሞ መልሶችህን በቅዱሳት መጻሕፍት አስደግፍ! 1. የኒቂያው የእምነት መግለጫ ሁሉን ቻይ የሆነው እግዚአብሔር አብ ሰማይንና ምድርን፣ እንዲሁም የሚታየውንና የማይታየውን ሁሉ የፈጠረ መሆኑን ይጠቁማል። ስለ እግዚአብሔር ለሚደረጉ ውይይቶች እና ጥናቶች ሁሉ ይህ የመጀመሪያው እና መሰረታዊው እውነት የሆነው ለምን ይመስልሃል? መልስህን አስረዳ። 2. የእግዚአብሔር ህልውና ተፈጥሮ ምንድ ነው? እግዚአብሔር በፍጥረቱና በሰው ልጆች ጉዳዮች ውስጥ በንቃት ተሳትፎ እንደሚያደርግ የሚያሳየን በምን መንገዶች ነው? 3. ለእኛ እንደ ነገረ መለኮት ተማሪነታችን ስለ እግዚአብሔር ሕልውና ማወቅ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ይህ ትምህርት ለሚሽን፣ ስለ እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት የሌላቸውን ሰዎች ለመድረስ የሚኖረው አንዳንድ አንድምታዎች ምን ሊሆኑ ይችላሉ? 4. የእግዚአብሔር ልዕልና ተፈጥሮ ምንድን ነው? እግዚአብሔር ያለ መንፈስ ቅዱስ እርዳታ ሊታወቅ እንደማይችል መረዳት ያለብን ለምንድነው? 5. እግዚአብሔር ልዕለ-ኃያል መሆኑን የመረዳት አንድምታው ምንድን ነው? ይህ ትምህርት እግዚአብሔርን ለማምለክና ለማገልገል የሚረዳን እንዴት ነው? 6. የእግዚአብሔር ባህሪያት ማለት ምን ማለት ነው? የእግዚአብሔርን የግል ባህሪያቱን ስናጠና ሁልጊዜ የእግዚአብሔርን አንድነት ማስታወስ አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድን ነው? አንዱን ከሌላው ለይተን የእግዚአብሔርን ባሕርያት አንድ በአንድ ለመረዳት በምንፈልግበት ጊዜ ልናስወግዳቸው የሚገቡን ስህተቶች የትኞቹ ናቸው? 7. የነገረ መለኮት ሊቃውንት የእግዚአብሔርን ባሕርያት እንዴት ይመድባሉ? ከእግዚአብሔር ታላቅነት ጋር የተያያዙት ባህሪያት የትኞቹ ናቸው? ከመልካምነቱ ጋር የተያያዙትስ የትኞቹ ናቸው?

መሸጋገሪያ 2

የተማሪው ጥያቄዎች እና ምላሾች

1

/ 3 3

እግዚአብሔር አብ

ግንኙነት

ይህ ትምህርት የሚያተኩረው ለጠንካራ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የስነ አምላክ ትምህርት ጥናት ወሳኝና የመጀመሪያ በሆኑ እውነቶች ላይ ነው። የአምላክን ማንነትና ሥራ የሚመለከቱትን ከባድ ጉዳዮች ከመመርመራችን በፊት የጥናታችንን “ትልቅ ሥዕል” መመሥረቱ አስፈላጊ ነው። ከጥናታችን በስተጀርባ ያሉትን መላ ምቶችን ካወቅን በኋላ፣ ወደ ስነ እግዚአብሔር ትምህርት እውነት እንሄዳለን። የእግዚአብሔርን ማንነት ከቅዱሳት መጻሕፍት ነጸብራቅና ከመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ውጪ እንደምንረዳው እንዳናስብ በእያንዳንዱ እርምጃ ከትዕቢት ልንጠበቅ ይገባል። ከዚህ ቀጥሎ የቀረቡት በመጀመሪያው ጥናታችን ውስጥ ከተመለከትናቸው ቁልፍ ሀሳቦች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው። ³ ፕሮሌጎሜና፣ የእግዚአብሔርን ትምህርት “የመጀመሪያዎቹ ነገሮች” ጥናት፣ ትክክለኛ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የእግዚአብሔር አብ ትምህርት ወይም ትክክለኛ ሥነ-መለኮት ጥናት ወሳኝ ነው። ³ ከእግዚአብሔር ተፈጥሮ እና ከማያልቅ ባህሪያችን የተነሳ፣ እርሱን ከማወቃችን በፊት እግዚአብሔር ራሱን ሊገልጥልን እንደሚገባ ማረጋገጥ አለብን። ³ አምላክ ከራሳችን የማሰብና የማሰብ ችሎታ በላይ እንደሆነ ስለምናውቅ ስለ አምላክና ስለ ማንነቱ በምንናገረው ሐሳብና ንግግሮች ሁሉ ትሑትና ጠንቃቃ መሆን አለብን። እሱን በግል ማወቅ ከፈለግን አምላክ ራሱን ሊገልጥልን ይገባል። ³ የሁሉም ነገር ፈጣሪ እንደመሆኑ መጠን በሁለት ልዩ መንገዶች ራሱን ገልጦልናል። በአጠቃላይ መገለጥ፣ እግዚአብሔር በየቦታው ላሉ ሰዎች ሁሉ ራሱን ይገልጣል፣ እና በልዩ መገለጥ፣ እግዚአብሔር ራሱን ለተወሰኑ ሰዎች በተወሰነ ጊዜና ቦታ ይገልጣል። ³ የኒቂያው የሃይማኖት መግለጫ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ስለ አንድ እውነተኛ አምላክ ታላቅነት ግልጽ መግለጫ ይሰጣል። ³ የእግዚአብሔር መሻገር የሚያመለክተው እግዚአብሔር ማለቂያ የሌለው በመሆኑ በፍጥረት ውስጥ ሊካተት ወይም ሊታወቅ የማይችል ራሱን ለሌሎች ለመግለጥ ያለ ሉዓላዊ ምርጫ ነው። ³ የእግዚአብሔር ባሕርያት የሙሉ አምላክነት፣ የአብ፣ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስን ባሕርያት ያመለክታሉ፣ እናም በታላቅነቱና በቸርነቱ ሊመደቡ ይችላሉ። ³ ከአምላክ ታላቅነት ጋር የተያያዙት ባሕርያት መንፈሳዊነቱ፣ ሕይወቱ፣ ማንነቱ፣ ማለቂያ የሌለው እና ቋሚነቱ ይገኙበታል። ³ ከአምላክ ጥሩነት ጋር የተያያዙት ባሕርያት የእሱ የሥነ ምግባር ንጽሕና፣ ጽኑ አቋምና ፍቅር ይገኙበታል። ³ አምላክ ከተፈጠረው አጽናፈ ዓለም ጋር ባለው ዝምድና ውስጥ ሕያውና ተሻጋሪ ነው። ³ አምላክ በፍጥረቱ ውስጥ ያለውን የአሁኑን እና ንቁ ተሳትፎን ያመለክታል።

የቁልፍ ጽንሰ ሐሳቦች ማጠቃለያ

ገጽ 257  10

1

3 4 /

እግዚአብሔር አብ

በዚህ የትምህርታችን ክፍል ውስጥ ስለ ትምህርተ እግዚአብሔር በአእምሮህ ውስጥ ለሚነሱ ልዩ ጥያቄዎች ከክፍል ጓደኞችህ ጋር የምትወያይበት ጊዜ አሁን ነው። እስካሁን ካጠናሃቸው ነገሮች አንጻር ወደ አእምሮህ የሚመጡት ጥያቄዎች ምንድናቸው? ከዚህ በታች የቀረቡት ጥያቄዎች የአንተን ጥያቄዎች፣ ምልከታዎችና ተግዳሮቶች ሊዳስሱልህ ይችላሉ:- * ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ የሰማይና የምድር ፈጣሪ፣ የሚታዩትንና የማይታዩትን ነገሮች የፈጠረ እንጂ አካላዊ ያልሆነ ኃይል አለመሆኑን መገንዘብ ምን ለውጥ ያመጣል? የቤተክርስቲያን አባቶች የእምነት መግለጫውን በዚህ ማረጋገጫ የጀመሩት ለምን ይመስልሃል? * እግዚአብሔር ራሱ ግንኙነትነትን ካልጀመረ ማንም እግዚአብሔርን ሊያውቅ እንደማይችል በሙሉ ልብ መናገር ያለብን ለምንድን ነው? ይህ ከሆነና እግዚአብሔር ግንኙነቱን መጀመር ካለበት፣ እግዚአብሔር እንዴት አንድን ሰው ወደ እርሱ ስላልመጣና ስላላወቀው ሊወቅሰው ይችላል? * አንድ ሰው ከልዩ መገለጥ አስፈላጊነት ይልቅ አጠቃላይ መገለጥን ቢያጎላ ምን ይሆናል? በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ሰው በአጠቃላይ መገለጥ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ሚና ሳይረዳ ልዩ መገለጥን ቢያጎላ ምን ይሆናል? * እግዚአብሔር በወንጀሎችና በቡድን ዓመፅ በተሞላው ማኅበረሰብ ጉዳይ ውስጥም ይገኛል ማለት ምን ማለት ሊሆን ይችላል? እግዚአብሔር እንደዚህ ባሉ ሁኔታዎች ውስጥ በህልውናው ካለ በመካከላችንስ መገኘቱን እንዴት እናውቃለን? * እግዚአብሔር ከተማዋን ትቷታል ሳትል ከብዙ የከተማ ማህበረሰቦች ትርምስ በላይ የእግዚአብሔርን ልዕልና እንዴት ታረጋግጣለህ? ዛሬ በከተሞችና በሰፈራችን ጉዳይ ላይ የእግዚአብሔር ህልውና እና ልዕልና እንዴት ሊሆን ይችላል? * በከተማ ባሉ አብያተ ክርስቲያኖቻችን በምናገለግልበት ወቅት የእግዚአብሔር የህልውና እና የልዕልና ትምህርት እንዴት ተጽዕኖ ሊያደርግብን ይገባል? ስለ አምልኮ ባለን ግንዛቤ ላይ ምን ተጽዕኖ ሊያሳድር ይገባል? ለተጎዱት በምናደርገው አገልግሎትስ? በማህበረሰቡ ውስጥ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ በሚያልፉትስ? በራሳችን ህይወት እና አገልግሎትስ? * አንድ ሰው ሌሎቹን በመተው አንዱ ላይ ብቻ ሳያተኩር የእግዚአብሔርን ባሕርያት በማጥናት እንዴት የበለጠ ጥቅም ማግኘት ይችላል? ከእግዚአብሔር ታላቅነት ጋር የተያያዙት የትኞቹ ባሕርያት ናቸው? ከመልካምነቱ ጋር የተያያዙት የትኞቹ ባሕርያት ናቸው? * የራስህ ሕይወትና አገልግሎት እግዚአብሔር የሁሉም አስደናቂ ባሕርያቱ አንድነት እንደሆነ እንደምትገነዘብ ያሳያል ወይስ ከሌሎቹ ይበልጥ የምታተኩረው በአንዱ ባሕርይ ላይ ነው? በዶክትሪን ጥናት ውስጥ ይህን የተለመደ ዝንባሌ እንዴት ማሸነፍ ይቻላል?

የተማሪው ትግበራ እና አንድምታ

ገጽ 257  11

1

/ 3 5

እግዚአብሔር አብ

እነዚያ ሁሉ ሰዎችስ? ጌታን ከምታካፍላቸው ከጓደኞችህ አንዱ ጋር በምታደርገው ውይይት፣ስለ ጌታ እና ስለ ድነት ባላቸው አስተሳሰባቸው ውስጥ ሊገነዘቡት ያልቻሉትን ልዩ ችግር አጉልተው ያሳዩሃል። በኢየሱስ በኩል የእግዚአብሔርን የማዳን ሥራ ገና ያልሰሙ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በመኖራቸው ተጨንቆ፣ ጓደኛህ የክርስትና እምነት እጅግ ፍትሃዊ ያልሆነ ነው ብሎ እንደሚያስብ ተናግሯል። “እሺ፣ እግዚአብሔር ራሱን በፍጥረት ውበት ውስጥ እንደገለጠ እስማማለሁ - በጣም ድንቅ ነው። እኔ ግን አሁንም ችግር አለብኝ፤ አጠቃላይ መገለጥ አንድን ሰው በክርስቶስ እንዲያምን ለመምራት በቂ ካልሆነ፣ ስለ ክርስቶስ እስካሁን ያልሰሙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ዕጣ ፈንታ ምንድነው? ለዘላለም ጠፍተው ሊሞቱ ተፈርዶባቸዋልን? ስለ ኢየሱስ ለማወቅ ልዩ መገለጥ ካስፈለገህ፣ ታዲያ እነዚያ ሁሉ ሰዎችስ? የጓደኛህን ጥያቄ እንዴት ትመልሰዋለህ? የማይገኝ አምላክ በማህበረሰቡ ውስጥ ከፍተኛ የጥቃት ወንጀሎች መጠን እየጨመረ በመምጣቱ ቤተክርስትያንህ ለማህበረሰቡ አባላት አካባቢያዊ ሰፊ የጸሎት ስብሰባ እያስተናገደች ነው። የጸሎት ጉዞዎችን እና የጸሎት እንቅስቃሴዎችን በማደራጀት፣ በአሁኑ ወቅት እዚህ አካባቢ ላይ እየተፈጸመ ላለው አይነት ግፍ እና ጭካኔ ምክንያት የሆኑትን መንፈሳዊ ሀይሎች ማኅበረ ቅዱሳኑ ለይቶ አውቋል። በአንደኛው የጸሎት ጊዜ፣ የቤተ ክርስቲያናችሁ አካል ያልሆነ አንድ የማኅበረሰብ ነዋሪ ተነስቶ፣ “እኔ ወደዚህ ቤተ ክርስቲያን አልሄድም፤ እውነቴን ነው እኔ ወደ የትኛውም ቤተ ክርስቲያን አልሄድም ምክንያቱም እግዚአብሔር ለሌሎች እንደሚያስብ ለእኛ የሚያስብ ስለማይመስለኝ፣ ለምንድነው የእኛ ሰፈር ሁል ጊዜ የሚሸበረውና የሚጎሳቆለው? እርሱ እዚህ ታች ካለነው የህብረተሰብ ክፍል ይልቅ ጥሩ ኑሮ ለሚኖሩት ሰዎች የበለጠ ግድ የሚለው ይመስላል። መላው የጸሎት ስብሰባ በአንዴ ጸጥ አለ፣ ለዚህ ተስፋ ለቆረጠው ጎረቤትህ የልብ ጩኸት መልስ ለማግኘት ሁሉም ወደ አንተ ዞሮ ይጠባበቃል። በዚህ የጸሎት ስብሰባ ላይ ለዚህ ምልከታ ምን ዓይነት ማብራሪያና ማጽናኛ ትሰጣለህ? የቆሎ ጓደኛ የሆነው ጌታ “ጥልቅ ውዳሴና አምልኮ” በተሰኘው አዲስ የትኩረት አቅጣጫ ምክንያት በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያንህ አባላት መካከል ረዘም ላለ ጊዜ ውዝግብ ሲካሄድ ቆይቷል። በቀድሞው የዝማሬና የአምልኮ ሥርዓት የተሰላቸው አዲሱ የአምልኮ መሪ በአገልግሎቱ ውስጥ በጥልቀትና በግላዊ መንገድ ስለ እግዚአብሔር የሚናገሩ አዳዲስ የምስጋና እና የአምልኮ ዝማሬዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል። አንዳንድ አንጋፋ ምእመናን ይህን አካሄድ ይቃወማሉ፣ አዲሱ ሙዚቃ እና የአካሄድ ትኩረት እግዚአብሔርን የበለጠ ግላዊ እንዳደረገው እና እርሱ ከእኛ የተለየ አምላክ የመሆኑን ፍርሃት እንዳጠፋብን ይናገራሉ። የእግዚአብሔር ፍርሃት ጌታን እንደ ቆሎ ጓደኛ በማየት ተተክቷል ብለው ይፈራሉ። እንግዲህ እዚህ ጋር ማነው ትክክል እና ማነው ስህተት? ሁለቱም በአንድ ጊዜ ትክክል እና ስህተት ሊሆኑ ይችላሉ - እንዴት? አንተ የዚህች ቤተ ክርስቲያን መሪ ብትሆን፣ ሁለቱም ወገኖች የእግዚአብሔር ህልውና እና ልዕልና ለእግዚአብሔር ያለንን የአምልኮ ልምምድ እንዴት እንደሚያበለጽጉ እንዲረዱ እንዴት መርዳት ትችላለህ?

ጥናቶች

1

ገጽ 258  12

1

2

3

3 6 /

እግዚአብሔር አብ

ፕሮሌጎሜና፣ የእግዚአብሔርን ትምህርት “የመጀመሪያዎቹ ነገሮች” ጥናት፣ እርሱን ከማወቃችን በፊት እግዚአብሔር ራሱን ሊገልጥልን እንደሚገባ በትህትና ያረጋግጣል። እግዚአብሔር ራሱን በሁለት ልዩ ሁነታዎች ገልጦልናል። በአጠቃላይ መገለጥ፣ እግዚአብሔር በየቦታው ላሉ ሰዎች ሁሉ ራሱን ይገልጣል፣ እና በልዩ መገለጥ፣ እግዚአብሔር ራሱን ለተወሰኑ ሰዎች በተወሰነ ጊዜና ቦታ ይገልጣል። ከፈጠራቸው አጽናፈ ዓለማት ጋር ባለው ግንኙነት፣ እግዚአብሔር ፍጡር እና ተሻጋሪ ነው። የእግዚአብሔር ህልውና በፍጥረቱ ሁሉ ያለውን የአሁን እና ንቁ ተሳትፎን የሚያመለክት ሲሆን የእግዚአብሔር መሻገር ደግሞ እግዚአብሔር ማለቂያ የሌለው መሆኑን እና ስለዚህ በፍጥረት ውስጥ ሊካተት ወይም ሊታወቅ እንደማይችል እውነትን የሚያመለክት ሉዓላዊ ምርጫው ከሌለ ራሱን ለሌሎች መግለጥ ነው። የእግዚአብሔር ባሕርያት የሙሉ መለኮትን፣ የአብ፣ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስን ባሕርያት ያመለክታሉ፣ እናም በታላቅነቱና በቸርነቱ ሊመደቡ ይችላሉ። የታላቅነቱ ባህሪያት መንፈሳዊነቱን፣ ህይወቱን፣ ስብዕናውን፣ ማለቂያ የሌለውን እና ቋሚነትን ያጠቃልላል፣ የመልካምነቱ ግን የሞራል ንፅህናው፣ ታማኝነቱ እና ፍቅሩ ያጠቃልላል።

የትምህርቱን ንድፈ ሃሳብ በድጋሚ መጻፍ

1

ስለ ፕሮሌጎሜና፡ ትምህርተ እግዚአብሔር እና የመንግሥቱ መስፋት አንዳንድ ተጨማሪ ሀሳቦችን ለመከታተል ፍላጎት ካለህ እነዚህን መጻሕፍት መመልከት ይረዳህ ይሆናል:

ማጣቀሻዎች

Evans, William. The Great Doctrines of the Bible. Chicago: Moody Press, 1976.

Schaeffer, Francis A. The God Who is There. Chicago: InterVarsity Press, 1968.

Stone, Nathan J. Names of God. Chicago: Moody Press, 1993.

ስለእነዚህ እውነቶች ለግል ህይወትህ እና ለአገልግሎትህ ያለውን ትርጉም በተግባር የምታስብበት ጊዜ አሁን ነው። በዛሬው የህይወት ሁኔታዎችህ ላይ አተኩር፤ በመቀጠልም የእግዚአብሔርን ማንነት እና ስራ በተመለከተ መንፈስ ቅዱስ እነዚህን እውነቶች አሁን ከምታደርገው ነገር ጋር እንድታዛምዳቸው የሚፈልግበትን መንገድ አስብ። በያዕቆብ 1፡22-25 ላይ ያለው የያዕቆብ የተስፋ ቃል ልዩ በረከቱ የእግዚአብሔርን ቃል ሰሚ ብቻ ላልሆኑ ነገር ግን ለሚያደርጉት እንደሚመጣ ነው። ስለ እግዚአብሔር አጠቃላይ እና ልዩ መገለጥ፣ ስለ ልዕልናውና ህልውናው እንዲሁም እግዚአብሔር ዛሬ እንድትሰራ ለጠራህ ነገር የእነዚህን ታላቅ እውነቶች ትርጉም በተመለከተ መንፈስ ቅዱስ በዚህ ሳምንት ምን እንደሚመክርህና ምን ላይ እንድታተኩር እንደሚፈልግ አስብ። በትምህርተ እግዚአብሔር ውስጥ ስላየሃቸው ስለእነዚህ እውነቶች ስታስብ ለራስህ ግንዛቤ እና ትግበራ ምን የተለየ ሰው፣ ክስተት ወይም ሁኔታ ወደ አእምሮህ ይመጣል? እነዚህን እውነቶች አሁን ተግባራዊ እንድታደርግ የሚጠይቅ የሕይወትህ እና የአገልግሎትህ ክፍል አለ? ከሆነ፣ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ እግዚአብሔር ምን እንድታደርግ ይፈልጋል? በተለይ በእነዚህ እውነቶች ላይ የእግዚአብሔርን ቃል ትምህርት በሕይወቱ ውስጥ ሊረዳና ሊተገብር የሚገባውን ሰው እያገለገልክ ነው? ትምህርቱን እንዴት ታስተዋውቀዋለህ? ለዚህ ግለሰብ እነዚህን ግንዛቤዎችዎ ለማካፈል የተሻለው ጊዜ ወይም ምቹ ሁኔታ መቼ ነው?

የአገልግሎት ግንኙነቶች

/ 3 7

እግዚአብሔር አብ

የዚህ ትምህርት ማዕከላዊ ሃሳብ እግዚአብሔር ያለና የሚሰራ እንዲሁም ምጡቅ እና ሉዓላዊ መሆኑ ነው። እርሱ በክቡር ፍጥረቱ አማካኝነት ለሰው ሁሉ ይገለጣል፣ ነገር ግን ንስሐ ለሚገቡ እና በመሲሑ ኢየሱስ ለሚያምኑ ሁሉ የገዛ ልቡንና ማንነቱን በግል ይገልጣል። ስለ እግዚአብሔር በምታውቀውና በምታምነው ነገር ለመኖር ብርታቱን እና ጥበቡን ጌታ እንዲሰጥህ እሻ፣ የእግዚአብሔርን የከበሩ ባህሪያት እና ስብዕናን በሚመለከት እውነቱን በበለጠ ግልጽነት እና ድፍረት እንድትናገር እንዲረዳህ ጌታን ለምን። እግዚአብሔር በሚናገረህ በማንኛውም ጉዳይ ላይ ከመሪዎችህ እና ከመምህሮች ድጋፍ ጠይቅ፤ ከተማርከው ነገር የተነሳ እግዚአብሔር በዚህ ሳምንት በልብህና በአእምሮህ እንድታደርገው የሚፈልገውን ሁሉ ሳትዘገይ እንድትታዘዝ የእግዚአብሔርን መንፈስ ሙላት ጠይቅ።

ምክር እና ጸሎት

ምደባዎች

1

መዝሙረ ዳዊት 19፡1-3

የቃል ጥናት ጥቅስ

ለክፍል ለመዘጋጀትና የሚቀጥለውን ሳምንት የምንባብ ምደባ ለማግኘት www.tumi.org/booksን ጎብኝ ወይም መምህርህን ጠይቅ።

የንባብ የቤት ስራ

ውድ ተማሪ ሆይ፣ በቀጣዩ ክፍለ ጊዜ ስለዚህኛው ሳምንት የትምህርት ይዘት (የቪዲዮ ትምህርቱን ይዘትና መመሪያውን) አጭር ፈተና ይሰጥሃል፡፡ የትምህርቱን ዋና ዋና ሃሳቦች በጥናትህ መሸፈንህን አረጋግጥ፡፡ የተሰጠህን የንባብ ስራ በሚገባ አጠናቅቀህ አዘጋጅ፡፡ የተመደበውን ንባብ አንብበህ እያንዳንዱን ንባብ ከአንድ ወይም ከሁለት በማይበልጥ አንቀጽ አጠቃልል። በዚህ ማጠቃለያ በእያንዳንዱ ንባብ ውስጥ ዋና ነጥብ ነው ብለህ የምታስበውን የተሻለ ግንዛቤ አቅርብ። ስለ ዝርዝር ጉዳዮች ብዙ መጨነቅ ሳያስፈልግህ የዚህን የመጽሐፍ ክፍል ዋና ሃሳብ ብቻ አቅርብ፡፡ እባክህ እነዚህን ማጠቃለያዎች በሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ይዘሃቸው ቅረብ፡፡ (እባክህ በዚህ ትምህርት መጨረሻ የሚገኘውን “የንባብ ማጠናቀቂያ ገጽ” ተመልከት፡፡) በሚቀጥለው ትምህርታችን ትኩረታችንን በፍጥረት እና በታሪክ ሁሉ ላይ የእግዚአብሔርን የበላይ ስልጣን እና መግቦትን በመረዳት ላይ እናደርጋለን። እግዚአብሔር አብ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ሉዓላዊ፣ የሁሉም ነገር ምንጭ እና የሁሉ አኗሪ እንደሆነ እንመለከታለን። በክርስቶስ ዳግመኛ ምጽአት ፍጥረትን ሁሉ ወደ ቀደመ ክብሩ ለመመለስ በገባው ቃል ኪዳን እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር የሚጠብቅበትን እና በፍጥረት ሁሉ ላይ ያለውን አገዛዝ እንመረምራለን።

ሌሎች የቤት ስራዎች

ገጽ 258  13

ለቀጣዩ ትምህርት መዘጋጀት

ይህ ሥርዓተ-ትምህርት የThe Urban Ministry Institute (TUMI) የሺዎች ሰዓታት የሥራ ውጤት በመሆኑ ያለ ፈቃድ ማባዛት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ TUMI እነዚህን መማሪያዎች ለእግዚአብሔር መንግሥት እድገት ለመጠቀም ለሚፈልጉ ሁሉ ድጋፍ ያደርጋል፤ በተጨማሪም ለማባዛት በተመጣጣኝ ዋጋ ፈቃድ ይሰጣል ፡፡ እባክህ ይህ መጽሐፍ በትክክል ፈቃድ ያገኘ መሆኑን ከመምህርህ ጋር በመሆን አረጋግጥ፡፡ በ TUMI እና በፈቃድ አሰጣጥ ፕሮግራማችን ላይ የበለጠ መረጃ ለማግኘት Www.site.org እና Www.tumi.org/license ን ጎብኝ፡፡

ስም _________________________________________

ሞጁል 6: እግዚአብሔር አብ ንባብ ማጠናቀቂያ ገፅ

ቀን _________________________________________

ለእያንዳንዱ ለተመደበው ንባብ የጸሃፊውን ዋና ነጥብ አጭር ማጠቃለያ (አንድ ወይም ሁለት አንቀጽ) ጻፍ ፡፡ (ለተጨማሪ ንባብ ፣ የዚህን ገጽ ጀርባ ተጠቀም ፡፡)

ንባብ 1

ርዕሱ እና ጸሐፊው: ______________________________________________ ገጾች _____________

ንባብ 2

ርዕሱ እና ጸሐፊው: ______________________________________________ ገጾች ______________

/ 4 1

እግዚአብሔር አብ

እግዚአብሔር እንደ ፈጣሪ የእግዚአብሔር መግቦት

ትምህርት 2

ገጽ 259  1

የትምህርቱ ዓላማዎች

ኃያል በሆነው በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ለአንተ ይሁን! የዚህን ሞጁል (ትምህርት) መጽሐፍ ካነበብክ፣ ካጠናህ፣ ውይይት ካደረግህና ወደ ተግባር ከቀየርክ በኋላ የሚከተሉትን ማድረግ ትችላለህ:- • የእግዚአብሔር የበላይ ስልጣን እና መግቦት በፍጥረት እና በታሪክ ሁሉ ላይ እንዴት እንደሚታይ ማብራራት ትችላለህ። • “መግቦት” ማለት “እግዚአብሔር ለራሱና ለፍጥረታቱ ለበጎ ያለውን ዓላማውን ለመፈጸም ሁሉም ነገሮች በእሱ ፍላጎት የተያዙበትን ሉዓላዊ ፈቃዱን በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ይሠራል” ማለት እንደሆነ ማሳየት ትችላለህ። • እግዚአብሔር አብ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ሉዓላዊ፣ የሁሉም ነገር ምንጭ እና የሁሉ አኗሪ እንደሆነ ለማሳየት ቅዱሳት መጻሕፍትን መጠቀም ትችላለህ። እርሱ ክብሩን ሁሉ ይወስድ ዘንድ ሁሉም ነገር ከእርሱ ፈቃድ ጋር ለመስማማት እንደተዘጋጀ ማሳየት ትችላለህ። • የእግዚአብሔር ልዩ የመግቦት ሥራ በእርሱ ሁለንተናዊ ጥበቃ እና አገዛዝ እንዴት እንደሚገለጥ ማሳየት ትችላለህ። • ከዘመናዊው ፍልስፍና እና ሃይማኖት ጋር ከተያያዙት ስህተቶች ውስጥ ምን ያህሉ እግዚአብሔር በፍጥረት እና በታሪክ ላይ ያለውን መግቦት ካለመረዳት እንደመጡ ግልጽ ማድረግ ትችላለህ። • በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ፍጥረትን ወደነበረበት ለመመለስ እግዚአብሔር ካለው ፍላጎት አንጻር ስለ እግዚአብሔር የጥበቃ እና የአገዛዝ ቁልፍ አካላት ያለህን ግንዛቤ ማሳየት ትችላለህ። • መግቦተ እግዚአብሔር እንደ ፓንቴይዝም፣ ዴኢዝም፣ ፋታሊዝም እና አጋጣሚ ላሉ አንዳንድ ዘመናዊ የፍልስፍና እና የነገረ-መለኮት ስህተቶችን እንዴት እንደሚፈታ በአጭሩ ማብራራት ትችላለህ። በእውነቱ አንድ ዓይነት 1 ጢሞ. 6፡13-16 ሁሉን በሕይወት በሚጠብቅ በእግዚአብሔር ፊት፥ በጴንጤናዊውም በጲላጦስ ዘንድ መልካሙን መታመን በመሰከረ በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት አዝሃለሁ፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪገለጥ ድረስ ያለ እድፍና ያለ ነቀፋ ሆነህ ትእዛዙን ጠብቅ፤ ያንም መገለጡን በራሱ ጊዜ ብፁዕና ብቻውን የሆነ ገዥ፥ የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ፥ ያሳያል። እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም

2

ጥሞና

ገጽ 260  2

4 2 /

እግዚአብሔር አብ

ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን። sui generis የሚለው ቃል (SUE-ee gin-air-us ይባላል) የላቲን ሀረግ ትርጉሙ፣ “በዓይነቱ ልዩ የሆነ” ወይም “የሚስተካከለው የሌለ ልዩ” ማለት ነው። በአጭሩ “በዓይነቱ ብቸኛው” የሚል ትርጉም አለው። ይህ እጅግ በጣም የምንወድደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክ እና አባትን የምንገልፅበት አስደናቂ መንገድ ነው። ለአንድ የእግዚአብሔር ሰው በጣም አስፈላጊ ከሆኑት እውነቶች አንዱ እግዚአብሔርን ሁሉን ለራሱ ደስታ እንደፈቃዱ እንደሚያደርግ እንደ ሉዓላዊ የመግቦት አምላክ መረዳት ነው። የጌታችን የኢየሱስ አምላክ እና አባት የሉዓላዊ ዓላማ አምላክ እንደሆነ ይህ እውነት በሁሉም የቅዱሳት መጻሕፍት ትምህርቶች እና ትእዛዛት ማዕከል ሆኖ ይገኛል። ይሖዋ እውነተኛ አምላክ፣ የሁሉም ነገር ፈጣሪና አኗሪ እንደመሆኑ መጠን በእሱ ዘንድ ተቀባይነት ባለው በማንኛውም ምክንያት የፈለገውን ማድረግ ይችላል። ሁኔታው ምንም ያህል አስፈሪ ቢመስልም፣ ችግሩም ምንም ያህል ከባድ ቢሆን፣ ሁኔታዎች ምንም ያህል አሳዛኝ ቢመስሉም፣ እርሱ የአብርሃም አምላክ፣ የጌታችን የኢየሱስ አምላክ፣ ያው ሙታንን የሚያስነሣና ሕይወትን ሁሉ የሚለውጥ ከራሱ ፈቃድና ዓላማ ጋር እንዲስማማ የሚያደርግ አምላክ ነው። የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ አጽናፈ ሰማይን ፈጥሮ በፈለገው መንገድ እንዲሄድ ትቶት ከዚያ ፈቀቅ ያለ አምላክ እንዳይደለ መጽሃፍ ቅዱስ ምስክርነት ይሰጣል። ለተወሰነ ጊዜ ክፋት እንዲኖር የፈቀደ ቢሆንም በልጁ በመሲሁ በኢየሱስ አማካኝነት ፍጥረቱን የመቤዠት ዕቅድ ከመጀመሪያው አንስቶ ነድፏል። አሁን ልጁ ቤዛነቱን ፈጽሟል፣ እርሱ በመረጠው ጊዜ ሁሉም ነገር ለዘላለም በሉዓላዊ አገዛዙ ሥር የሚመለስበትን ጊዜ ወስኗል። ከዚህም በተጨማሪ የተባረከና ብቸኛው ሉዓላዊ ገዥ በሆነው የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ በሆነው በኢየሱስ በኩል ይህን ሁሉ ለመፈጸም ወስኗል። ከላይ በጽሑፋችን ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ እንደገለጸው፣ በዚያ ማንም በማይቀርበው በአባቱ ብርሃን ውስጥ የሚኖረው፣ የማይሞተው ብቸኛው፣ ማንም ሰው የማያየው፣ ሊያየውም የማይችለው ሉዓላዊው አምላካችን ኢየሱስ ብቻ ነው። አምላካችን ሁሉን እንደ ጥበቡና ኃይሉ የሚሠራ የዓለማት ሉዓላዊ ፈጣሪ እውነተኛ አምላክ ነው። ፈቃዱን መቃወም ቢቻልም ነገር ግን በጭራሽ ማሸነፍ ወይም ማክሸፍ አይቻልም። እርሱ ሁሉን ፈጥሯል፣ ሁሉንም ደግፎ ይዟል፣ ሁሉንም ደግሞ ለራሱ ክብር ይጠቀልላል። እርሱ ሁሉንም ነገር ይጠብቃል፣ ሁሉን ያስተዳድራል፣ ሁሉንም ነገር እርሱ ወደ ወሰነው ፍጻሜው ይመራል፤ ኃሳቡንም ከመፈጸም የሚያግደው ምንም ነገር እና ማንም የለም። እርሱ አምላክ ነው! ይህ ታላቅ አምላክ አምላካችን ስለሆነ፣ ጳውሎስ “ክብርና የዘላለም ኃይል ለእርሱ ይሁን፤ አሜን” እንዳለ ለእርሱ የሚገባውን ክብር ልንሰጠው ይገባናል። ባለ ግርማ ሞገስ ለሆነው ለዚህ ታላቅ አምላክ የምንሰጠው አምልኮ እና ምንም ቅድመ ሁኔታ የሌለው መገዛት ብቻ ነው። እስቲ ይህንን ግባችን እናድርገው፣ ራሳችንን ከፍ ካለው ከዚህ ታላቅ አምላክ ሃሳብ ጋር ለማስማማት እና ለእርሱ በእውነት የሚገባውን ክብር እና ምስጋና ለመስጠት። በእውነት አምላካችን ምሳሌ የሌለው ልዩ አምላክ ነው።

2

/ 4 3

እግዚአብሔር አብ

የኒቂያን የእምነት መግለጫ (በአባሪው ውስጥ የሚገኝ) ካነበብክ እና/ወይም ከዘመርክ በኋላ የሚከተለውን ጸሎት ጸልይ: አምላክ ሆይ ከዓለም ውብ ነገሮች እይታ ወደ ፈጣሪያቸው ወደ አንተ አሳብ ምራን። የውበት መጀመሪያና ባለቤት፣ የስራህ ሁሉ ሉዓላዊ ጌታ፣ ለዘላለም የተባረከው አንተ በፍጥረትህ ውብ ነገሮች የምናገኘውን ደስታ በአንተ ደስ እንዲለን ስጠን ።

የኒቂያ የእምነት መግለጫ እና ጸሎት

~ Appleton, George, ed. The Oxford Book of Prayer. Oxford; New York: Oxford University Press, 1988. p. 62.

የኃይልና የችሎት ሁሉ ጌታ የመልካም ነገር ሁሉ ምንጭ እና ሰጪ፡ የስምህን ፍቅር በልባችን አኑር። በእኛ ውስጥ እውነተኛ ሃይማኖት ይጨምር፣ በመልካምነት ሁሉ ሙላን፣ በውስጣችንም የመልካም ሥራ ፍሬ ያብብ። ከአንተና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕያው ሆኖ በሚነግሥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አንድ አምላክ ከዘላለም እስከ ዘላለም። አሜን። ~ The Episcopal Church. The Book of Common Prayer and Administrations of the Sacraments and Other Rites and Ceremonies of the Church, Together with the Psalter or Psalms of David. New York: The Church Hymnal Corporation, 1979. p. 233.

2

ማስታወሻዎችህን አስቀምጥ፣ ሀሳብህን ሰብስበህ የትምህርት 1ን “ፕሮሌጎሜና፡ ትምህርተ እግዚአብሔር እና የመንግሥቱ መስፋት” ፈተና ውሰድ።

አጭር ፈተና ገጽ 260  3

የቃል ጥናት ክፍል ቅኝት

ከሌላ ሰው ጋር በመሆን ላለፈው ክፍለ ጊዜ የተመደበውን የቃል ጥናት ክፍል ፃፍ ወይም በቃልህ አንብብ: መዝ. 19.1-3

ባለፈው ሳምንት ለተሰጠው የንባብ የቤት ስራ መምህርህ የሚጠብቅብህን ዋና ዋና ነጥቦችና ማጠቃለያ አቅርብ (ንባብ ማጠናቀቂያ ገጽ)።

የቤት ስራ ማስረከቢያ

4 4 /

እግዚአብሔር አብ

እርሱ አያውቅም ወይም ግድ አይሰጠውም በምሳ እረፍት፣ በቅርቡ ስለፈነዳው እና ብዙ ንፁሃንን ስለጎዳው አሰቃቂ የአሸባሪ የቦምብ ጥቃት አንዱ የስራ ባልደረባህ ስለሁኔታው የአንተን አስተያየት አጥብቆ ማወቅ ይፈልጋል። ክርስቲያን መሆንህን ስለሚያውቅ እንዲህ ይላል፡- “ይህ ሁሉ መጥፎ ነገር ፍጹም ንጹሐን በሆኑ ሰዎች ላይ ሲደርስ እያየህ እንዴት እግዚአብሔር አለ ትላለህ? ይህ ምንም ትርጉም አይሰጥም። አየህ፣ እግዚአብሔር ስለዚህ ነገር የሚያውቅ ከሆነ ሊያቆመው ይገባል፣ አይደል? እርሱ ይህን የሚያውቅ ከሆነ እና ምንም ነገር ካላደረገ፣ እንግዲህ እግዚአብሔር ለሰዎች ግድ የሚሰጠው እንዴት ነው? “አየህ፣ እነዚህ ነገሮች እየሆኑ እግዚአብሔር ምንም የማያደርግ ከሆነ ምንም ትርጉም የለውም።” ይህ ሁሉ እንዴት እንደሚሰራ እንድታብራራ ሁሉም ዓይኖች ወደ አንተ ዞረው ከጠየቁህ ምላሽህ ምን ይሆናል? ደስታው ጠፍቷል በአካባቢህ ካሉት ወጣቶች ከአንዱ ጋር ስትነጋገር፣ ለሕይወት ምንም ዓይነት ትልቅ ዓላማ እንደሌለ፣ ከሁሉም ነገሮች በስተጀርባ አንድም ምክንያት ወይም ዓላማ እንደሌለ እንደሚያምን ስትገነዘብ ትገረማለህ። በዚህ ሕይወት ውስጥ የሚያውቀው ነገር ሁሉ ሀዘን እና መከራ እንደሆነ ይናገራል፤ ነገሮችም ሁሉ አልተሳኩለትም፣ ሁል ጊዜ ውራ፣ ሁል ጊዜም ባዶ ነው፣ ደስተኛም አይደለም። ይህ አይነቱ ነገር በቤት ውስጥ ባሉት ሰዎች እና በመላው ቤተሰቡ ሕይወት ውስጥ ስለሚንጸባረቅ ከዚህ የተለየ ጊዜን ማሰብ እንኳን አይችልም። ለእርሱ የህይወት ደስታ The Thrill Is Gone እንደተሰኘው የቢ.ቢ. ኪንግ ዘፈን ነው ይላል፣ ደስታው ጠፍቷል። በእርሱ የህይወት ተስፋ መቁረጥ ሳንወሰድ ከዚህ ወንድም ጋር በሱ ደረጃ እንዴት መወያየት እንችላለን? አምላክ ሁሉም ነገር እና በሁሉም ቦታ ነው በሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል ውስጥ ካሉ ወጣት ጎልማሳዎች አንዷ በጁኒየር ኮሌጅ በምትማርበት ክፍል ያለችና እግዚአብሔር የመላው ዩኒቨርስ አካል ነው ብላ የምታምን መምህሯን ምን ማድረግ እንዳለባት እንደማታውቅ ተናግራለች። መምህሯ በክፍል ውስጥ “እግዚአብሔር በሁሉም ቦታ እና በሁሉም ነገር ውስጥ አለ። እኛ የተደራጀ ሃይማኖት አያስፈልገንም ምክንያቱም ሁሉም ነገር የተቀደሰ ነው፣ ምክንያቱም ሁሉም ነገር አምላክ ነው።” ይህች የኮሌጅ ተማሪ መምህሯ ስለ አምላክ ከምትናገረው አንጻር እንዴት ልትመልስ ትችላለች?

እውቂያ

1

ገጽ 261  4

2

2

3

/ 4 5

እግዚአብሔር አብ

እግዚአብሔር እንደ ፈጣሪ፡ የእግዚአብሔር መግቦት ሴግመንት 1፡ የሁሉን ቻዩ የእግዚአብሔር አብ የኒቂያ ማረጋገጫ

ይዘት

ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ

ሁሉን ቻይ የሆነው እግዚአብሔር አብ ሰማይና ምድርን የፈጠረ፣ በፈጠረው ሁሉ ላይ ሉዓላዊ ነው፣ በሁሉም ቦታ የሕይወት ሁሉ ምንጭ ነው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩልም ሁሉን ደግፎ ያኖራል። እግዚአብሔር የሚያደርገው ሁሉ በሰማይና በምድር ሁሉ ስሙ ከፍ እንዲልና እንዲከበር ነው። የዚህ የሁሉን ቻዩ የእግዚአብሔር አብ የኒቂያ ማረጋገጫ የተሰኘ ሴግመንት አላማ የሚከተሉትን እንድታይ ለማስቻል ነው፦ • ሁሉን የሚገዛ የጌታችን የኢየሱስ አምላክና አባት በፍጥረትና በታሪክ ሁሉ ላይ የበላይ ባለሥልጣንና አሳቢ ገዥ መሆኑን። • እግዚአብሔር “የመግቦት” አምላክ መሆኑን፣ “በጽንፈ ዓለሙ ውስጥ ሉዓላዊ ፈቃዱን ይፈጽማል” ማለት ሲሆን ለራሱም ሆነ ለፍጥረታቱ ለበጎ ያለውን ዓላማውን ለመፈጸም ሁሉም ሁኔታዎች በእርሱ እንደተዘጋጁ። • እንደ ጌታ እና ፈጣሪ፣ እግዚአብሔር አብ በሁሉ ሉዓላዊ፣ የሁሉም ምንጭ እና በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ሁሉን ነገር ደግፎ አኗሪ መሆኑን። • እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ለራሱና ከፈቃዱ ጋር እንዲስማማ አድርጎ የሚመራው እና የሚያንቀሳቅሰው መሆኑን ይህም ለእርሱ ክብር ይሆን ዘንድ መሆኑን እንድታይ ነው።

የሴግመንት 1 ማጠቃለያ

2

I. ሁሉን ቻይ የሆነው እግዚአብሔር አብ በሁሉም ላይ ሉዓላዊ ነው።

የቪድዮ ሴግመንት 1 ዝርዝር

ሀ. በፍጥረት ሁሉ ላይ ሉዓላዊ ነው፣ 1ጢሞ. 6፡15-16።

1. አብ ሰማይንና ምድርን ፈጠረ, መዝ. 33.6.

2. ፍጥረት የእግዚአብሔር ነው፣ መዝ. 115.16.

3. እግዚአብሔር ለራሱ ዓላማ ከፍጥረቱ ጋር መስተጋብር ይፈጥራል።

Made with FlippingBook - Online magazine maker