God the Father, Amharic Mentor Guide
1 2 /
እግዚአብሔር አብ
የሚኒስትሪ ፕሮጀክት የክርስቲያን መሪነት መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ማወቅ ብቻ አይደለም። ሌሎች እንዲታነጹ እና ለአገልግሎት እንዲዘጋጁ በሚያስችል መንገድ የእግዚአብሔርን ቃል መጠቀም መቻልን ይጨምራል። የእግዚአብሔር ቃል ሕያው እና የሚሰራ ነው፣ ወደ ህይወታችንና ወደ ልባችንም ሃሳብ ዘልቆ ይገባል (ዕብ. 4.12)። ሐዋሪያው ያዕቆብ የእግዚአብሔርን ቃል ሰሚዎች ብቻ ሳይሆን አድራጊዎችም መሆን እንደሚያስፈልገን ገልጿል። ቃሉን እንድንተገብር፣ እንድንታዘዘው ተመክረናል። ይህንን ተግሣጽ ችላ ማለት የተፈጥሮ ፊቱን በመስታወት ተመልክቶ መልኩን ከረሳ ሰው ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው ይጠቁማል። በማንኛውም ሁኔታ፣ የእግዚአብሔርን ቃል የሚያደርግ ሰው በሚሠራው ሁሉ ይባረካል (ያዕቆብ 1፡22-25)። እኛም መሻታችን የምንቀስመውን ትምህርት በግል ህይወትህ፣ በአገልግሎትህና በቤተክርስቲያንህ ውስት ካሉ ተጨባጭ ሁኔታዎችና ፍላጎቶች ጋር በማዛመድ በተግባር ስታውለው መመልከት ነው፡፡ ሥነ መለኮታዊ ጽሑፍ፡ ለጓደኛ የተላከ ደብዳቤ። ቃሉን ማገልገል ብዙውን ጊዜ ስብከት መስበክን ወይም መደበኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ማስተማርን ብቻ ሳይሆን ለጓደኛ፣ ለቤተሰብ አባል ወይም ለሥራ ባልደረባ ያመንከውን ለምን እንደምታምን መንገርንም ያካትታል። የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ስለ አስፈላጊ ሥነ-መለኮታዊ ርዕሰ ጉዳዮች መደበኛ ባልሆነ መንገድ የመናገር ችሎታህን እንድታሳድግ መርዳት ነው። በእግዚአብሔር ማንነት ዙሪያ ካሉ ጉዳዮችና በኢየሱስ ወደ ማመን ከመምጣት ጋር የሚታገል አንድ የምታውቀውን ሰው ወይም ምናባዊ ሰው አስብ። በእግዚአብሔር ማመን አስፈላጊና ትክክል የሆነበትን ምክንያት በመግለጽ ለዚህ ሰው ደብዳቤ ጻፍ። እያንዳንዱ ደብዳቤ በሚከተሉት መመዘኛዎች ይመዘናል፦
ዓላማ
እቅድ እና ማጠቃለያ
• በጥሩ ሁኔታ የተፃፈ ወይም የተተየበ፣ በሰዓቱ የቀረበ • ከሁለት እስከ አራት ገጾች ርዝማኔ ያለው መሆኑ • በዕለት ተዕለት የንግግር ቋንቋ ዘዬ የተጻፈ መሆኑ • ከቅዱሳት መጻሕፍት ግልጽ ማጣቀሻን መጠቀሙ • በክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር እንድናምን ጠንካራ ግብዣን ማድረጉ
ጽሑፍህ ለጓደኛህ የምትጽፈውን አይነት ባህላዊ የደብዳቤ መልክ የተከተለ መሆን አለበት። ደብዳቤህን ይህ ደብዳቤ ስለተጻፈለት ሰው በሚያወራ አጭር አንቀጽ ጀምር። ስለዚህ ሰው ጥቂት ዝርዝሮችን አቅርብ፡ ስለ እድሜው፣ ስለሚኖርበት ቦታ፣ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚያውቀው ነገር (ካለ)፣ አሁን ወይም ከዚህ ቀደም ስለነበረበት ሁኔታ፣ ወዘተ። ስለ ማንኛውም አይነት ሰው እና ሁኔታ ለማሰብ ነፃነት ይኑርህ። በደብዳቤህ ሐተታ ውስጥ፣ በእግዚአብሔር ስለማመን ለጓደኛህ ጉዳዩን አቅርብ። ምክንያቶችንም አቅርብለት፣ ምክንያቶችህንም በቅዱሳት መጻሕፍት አስደግፍ። አስፈላጊ ከሆነ ምን ዓይነት ተቃውሞዎች ሊኖሩት እንደሚችሉ አስበህ ከወዲሁ መልስ ስጥባቸው። አሳማኝ የሆነ አቀራረብ ይኑርህ! አስተውል፣ ይህ የግል ደብዳቤ እንጂ መደበኛ የአካዳሚክ ወረቀት አይደለም። ይህ የሚኒስትሪ ፕሮጀክት የ30 ነጥቦች ዋጋ ያለው ሲሆን ከጠቅላላው የዚህ ኮርስ ውጤት 10% ይይዛል፡፡ ስለዚህ ሃሳብህን በልበ ሙሉነት ማካፈልህንና ግልጽ የሆነ ማብራሪያ ማቅረብህን እርግጠኛ መሆን ይኖርብሃል፡፡
ምዘና
Made with FlippingBook - Online magazine maker