God the Father, Amharic Mentor Guide
/ 1 3
እግዚአብሔር አብ
ፕሮሌጎሜና ትምህርተ እግዚአብሔር እና የመንግስቱ መስፋት
ትምህርት 1
ገጽ 253 1
ኃያል በሆነው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ለአንተ ይሁን ! የዚህን ትምህርት መጽሐፍ ካነበብክ፥ ካጠናህ፥ ውይይት ካካሄድክና ወደ ተግባር ከቀየርከው በኋላ የሚከተሉትን ማድረግ ትችላለህ:- • የመጀመሪያዎቹን ነገሮች፣ ፕሮሌጎሜና፣ ከትምህርተ እግዚአብሔር አብ መደበኛ ጥናት ጋር ወይም ከtheology proper ጋር በተያያዘ በትክክል ማጥናት ትችላለህ። • እኛ እርሱን ከማወቃችን በፊት እግዚአብሔር ራሱን መግለጡ አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነ መግለጽ ትችላለህ። • እግዚአብሔር በሁሉም ስፍራ ላሉ ሰዎች ሁሉ ራሱን ከሚገልጥበት መንገድ፣ አጠቃላይ መገለጥ እና እግዚአብሔር ራሱን ለተወሰኑ ሰዎች በተወሰኑ ጊዜያትና ቦታዎች ከሚገልጥበት መንገድ፣ ልዩ መገለጥ ጋር የተገናኙትን እውነቶች መረዳት ትችላለህ። • የኒቂያው የእምነት መግለጫ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት የሆነው አንድና እውነተኛ አምላክ ታላቅነት የሚገልጸው እንዴት እንደሆነ ማሳየት ትችላለህ። • የእግዚአብሔርን ፍፁምነት (ማለትም፣ የእግዚአብሔርን በፍጥረት ውስጥ መገኘት እና ያለውን ተሳትፎ) እና ምጡቅነት (የእግዚአብሔር ወሰን የሌለው ተፈጥሮ እና ታውቆ አለመጨረስ) ማስረጃን መስጠት ትችላለህ። • የእግዚአብሔርን ባሕሪያት ትርጉም፣ ችግራቸውንና ዓላማቸውን፣ እንዲሁም ተፈጥሮአቸውን እና ምደባቸውን ማብራራት ትችላለህ። ምንም ሰበብ አይፈቀድም ሮሜ. 1፥18-20 - እውነትን በዓመፃ በሚከለክሉ ሰዎች በኃጢአተኝነታቸውና በዓመፃቸው ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ቍጣ ከሰማይ ይገለጣልና፤ 19እግዚአብሔር ስለ ገለጠላቸው፥ ስለ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚቻለው በእነርሱ ዘንድ ግልጥ ነውና። 20የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤ ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ። ስለዚህ ያለ ሰበብ ናቸው። የኒቂያው የእምነት መግለጫ የሚጀምረው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ስለሆነው አንዱ እውነተኛ አምላክ ታላቅነት ግልጽ በሆነ መግለጫ ነው። “ሁሉን በሚችል፣ ሰማይንና ምድርን የሚታየውንና የማይታየውንም በፈጠረ በአንድ አምላክ እናምናለን” በሚል ሐረግ ይጀምራል። ይህ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በሁሉም ቦታ የተረጋገጠ የእውነት ማረጋገጫ ነው፡ የእግዚአብሔር
የትምህርቱ አላማዎች
ገጽ 253 2
ገጽ 253 3
1
ጥሞና
ገጽ 254 4
Made with FlippingBook - Online magazine maker