God the Father, Amharic Mentor Guide
/ 1 5
እግዚአብሔር አብ
ሁሉን በጊዜና በቦታ የፈጠርህና ሰውን በመልክህ የፈጠርህ ኃያል አምላክ፡ በፈጠርከው ሁሉ ክንድህን እንድንገነዘብ እና ሁልጊዜም ስለ ጥበብህና ስለ ፍቅርህ እንድናመሰግንህ ምራን፤ ከአንተ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በሁሉም ነገር ላይ አሁን እና ለዘላለም በሚነግሥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል። ~ Church of the Province of South Africa. Minister’s Book for Use With the Holy Eucharist and Morning and Evening Prayer. Braamfontein: Publishing Department of the Church of the Province of South Africa. p. 12
ይህ ትምህርት ፈተና የለውም
ፈተና
1
የቃል ጥናት ጥቅስ ምዘና
ይህን ትምህርት የቃል ጥናት ጥቅስ የለውም
የቤት ስራ/መልመጃ ማስረከቢያ
ይህ ትምህርት የቤት ስራ/መልመጃ የለውም
እውቂያ
“አምላክ አንድ ብቻ ነው - አላህ” የእስልምና ሐገር አባል የሆነን (በሉዊ ፋራካን የሚመራው የጥቁሮች ሙስሊሞች ቡድን) በመንገድ ላይ ጋዜጣ ሲሸጥ አጋጥሞህ፣ ለአፍታ ከእርሱ ጋር ለመነጋገር ቆመሃል። ርዕሰ ጉዳዩ ወደ እግዚአብሔር ማንነትና አምላክነት ሲዞር፣ አይነ ብሩኁ ወጣት የእስልምና እምነት ተከታይ “ከአላህ ሌላ አምላክ የለም፣ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረው እርሱ ብቻ ነው” ይላል። ለእርሱ አስተያየት ምን ምላሽ ትሰጣለህ? “ያኔ የት ነበር?” በሰንበት ትምህርት ቤት ስለአይሁድ ሕዝብ በአሦርና በባቢሎን በምርኮ መወሰድና ስለሚደርስባቸው መከራ ስትነጋገሩ ከታዳጊ ወጣቶቹ አንዱ “ሁልጊዜ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንዳለና እኛንም እንደወደደን እንናገራለን፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ከሆነና የሚንከባከበው ከሆነ፣ ታዲያ ለምን የራሱን ሕዝብ እንዲጎዳና እንዲንገላታ ፈቀደ? ያኔ የት ነበር?” ሲል ጠየቀ። የክፍሉ መምህር እንደመሆንህ፣ የዚህን ተማሪ አስፈላጊ ጥያቄ እንዴት ትመልሰዋለህ?
1
ገጽ 254 5
2
Made with FlippingBook - Online magazine maker