God the Father, Amharic Mentor Guide

1 6 /

እግዚአብሔር አብ

“እኔ እንጃ” በቅርቡ ከትናንሽ ልጆቿ መካከል አንዷን በሉኪሚያ ያጣችው ወጣት እናት በድብርት እየተሰቃየች ነው። ደጋግማ በሞከረች መጠን፣ አምላክ የለም፣ ወይም ደግሞ እርሱ በርግጥ ካለ አፍቃሪ ሊሆን አይችልም ብሎ የማሰብ ፈተናን ማሸነፍ የቻለች አትመስልም። ለምንድነው ውዷ ትንሿ ማርታን ለረጅም ጊዜ እንድትሰቃይ እና በህጻንነቷ እንድትሞት የፈቀደው? የልቧን ነገር ስታካፍልህ፣ “ስጸልይ፣ መጽሐፍ ቅዱሴን ሳነብ፣ በሌሊት ሰማይን ስመለከት ብቸኝነት ይሰማኛል፣ የምሄድበት ሰባኪና አማካሪ ምን እንደሚሉ አውቃለሁ፣ ነገር ግን አንዳቸውም ቢሆኑ ለምን እንደሆነ እንድገነዘብ አልረዱኝም፣ እግዚአብሔር የሚወደን ከሆነ ይህ ለምን ሆነብን? በርግጥ እግዚአብሔር እውን ነውን? በርግጥስ እግዚአብሔር አፍቃሪ ነውን? እኔ እንጃ።” ለዚህች ውድ ወጣት እህት ግንዛቤ እንዲኖራት ላቀረበችው ጥያቄ ምን ምላሽ ትሰጣለህ?

3

1

ፕሮሌጎሜና፡ ትምህርተ እግዚአብሔር እና የመንግሥቱ መስፋት ሴግመንት 1፡ እግዚአብሔር አለን? ራሱንስ ይገልጣልን?

ይዘት

ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ

በዚህ ሴግመንት በአጠቃላይ እና በልዩ መገለጥ አማካኝነት እግዚአብሔር ራሱን ለሰው ልጆች የመግለጡን ሉዓላዊ ዓላማ እንመረምራለን። የዚህ እግዚአብሔር አለን? ራሱንስ ይገልጣልን? የተሰኘ ሴግመንት ዓላማ፣ የሚከተሉትን እንድታይ ለማስቻል ነው፡- • ፕሮሌጎሜና፣ “የመጀመሪያ ነገሮች”፣ የነገረ መለኮት ትክክለኛ ጥናት (የአምላክ ጥናት)፣ እግዚአብሔርን ማወቅ ከፈለግን እግዚአብሔር ራሱን ሊገልጥልን እንደሚገባ ይጠቁማል። እርሱ ራሱን ካልገለጠልን ማንም ሊያውቀው አይችልም። • እግዚአብሔር ራሱን በሁለት ተያያዥ መንገዶች ማለትም በአጠቃላይና በልዩ መገለጥ ለሰው ልጆች ገልጧል። • በአጠቃላይ መገለጥ እግዚአብሔር በሁሉም ስፍራ ላሉ ሰዎች ሁሉ ራሱን ይገልጣል፣ በልዩ መገለጥ ደግሞ እግዚአብሔር ራሱን ለተወሰኑ ሰዎች በተወሰነ ጊዜና ቦታ ይገልጣል።

የሴግመንት 1 ማጠቃለያ

ገጽ 255  6

Made with FlippingBook - Online magazine maker