God the Father, Amharic Mentor Guide
/ 2 7
እግዚአብሔር አብ
2. እግዚአብሔር በሰዎች ጥረት እና ተግባር ሊታወቅ አይችልም፤ ክብሩ እና ማንነቱ ከሰው ልጆች መረዳት እና ልምምድ ወሰን በላይ ናቸው።
ሀ. ዘዳ. 10.14
ለ. መዝ. 113.4-6
3. የእግዚአብሔር ሉዓላዊነት አንድምታ
1
ሀ. የሰው ልጅ ሕይወት በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ከፍተኛው ማንነት/ስብዕና ሆኖ አያውቅም።
ለ. እግዚአብሔር ሥነ መለኮት ወይም ሌላ ትምህርት ስለ እርሱ በሚፈጥሯቸው ጽንሰ-ሐሳቦች ሊገደብ ወይም ሊያዝ አይችልም።
ሐ. እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ከአገዛዙ ስር የሚያደርገው ለእኛ መዳን እና በመጨረሻም ለክብሩ ብቻ ነው።
መ. እግዚአብሔር sui generis የሆነ ማንነት ነው (ማለትም፣ የሚመስለው የሌለ)። ሌላ ፍጡር ወደ ሙሉ ክብሩ ሊደርስ አይችልም።
ሠ. እግዚአብሔር ከሁሉም እና ከምንም ነገር በላይ ሊፈራ ይገባዋል።
ረ. እግዚአብሔር ከእኛ እና ከሀሳባችን በላይ በሁሉም ነገር እንደሚልቅ መጠበቅ አለብን።
Made with FlippingBook - Online magazine maker