God the Father, Amharic Mentor Guide
3 4 /
እግዚአብሔር አብ
በዚህ የትምህርታችን ክፍል ውስጥ ስለ ትምህርተ እግዚአብሔር በአእምሮህ ውስጥ ለሚነሱ ልዩ ጥያቄዎች ከክፍል ጓደኞችህ ጋር የምትወያይበት ጊዜ አሁን ነው። እስካሁን ካጠናሃቸው ነገሮች አንጻር ወደ አእምሮህ የሚመጡት ጥያቄዎች ምንድናቸው? ከዚህ በታች የቀረቡት ጥያቄዎች የአንተን ጥያቄዎች፣ ምልከታዎችና ተግዳሮቶች ሊዳስሱልህ ይችላሉ:- * ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ የሰማይና የምድር ፈጣሪ፣ የሚታዩትንና የማይታዩትን ነገሮች የፈጠረ እንጂ አካላዊ ያልሆነ ኃይል አለመሆኑን መገንዘብ ምን ለውጥ ያመጣል? የቤተክርስቲያን አባቶች የእምነት መግለጫውን በዚህ ማረጋገጫ የጀመሩት ለምን ይመስልሃል? * እግዚአብሔር ራሱ ግንኙነትነትን ካልጀመረ ማንም እግዚአብሔርን ሊያውቅ እንደማይችል በሙሉ ልብ መናገር ያለብን ለምንድን ነው? ይህ ከሆነና እግዚአብሔር ግንኙነቱን መጀመር ካለበት፣ እግዚአብሔር እንዴት አንድን ሰው ወደ እርሱ ስላልመጣና ስላላወቀው ሊወቅሰው ይችላል? * አንድ ሰው ከልዩ መገለጥ አስፈላጊነት ይልቅ አጠቃላይ መገለጥን ቢያጎላ ምን ይሆናል? በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ሰው በአጠቃላይ መገለጥ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ሚና ሳይረዳ ልዩ መገለጥን ቢያጎላ ምን ይሆናል? * እግዚአብሔር በወንጀሎችና በቡድን ዓመፅ በተሞላው ማኅበረሰብ ጉዳይ ውስጥም ይገኛል ማለት ምን ማለት ሊሆን ይችላል? እግዚአብሔር እንደዚህ ባሉ ሁኔታዎች ውስጥ በህልውናው ካለ በመካከላችንስ መገኘቱን እንዴት እናውቃለን? * እግዚአብሔር ከተማዋን ትቷታል ሳትል ከብዙ የከተማ ማህበረሰቦች ትርምስ በላይ የእግዚአብሔርን ልዕልና እንዴት ታረጋግጣለህ? ዛሬ በከተሞችና በሰፈራችን ጉዳይ ላይ የእግዚአብሔር ህልውና እና ልዕልና እንዴት ሊሆን ይችላል? * በከተማ ባሉ አብያተ ክርስቲያኖቻችን በምናገለግልበት ወቅት የእግዚአብሔር የህልውና እና የልዕልና ትምህርት እንዴት ተጽዕኖ ሊያደርግብን ይገባል? ስለ አምልኮ ባለን ግንዛቤ ላይ ምን ተጽዕኖ ሊያሳድር ይገባል? ለተጎዱት በምናደርገው አገልግሎትስ? በማህበረሰቡ ውስጥ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ በሚያልፉትስ? በራሳችን ህይወት እና አገልግሎትስ? * አንድ ሰው ሌሎቹን በመተው አንዱ ላይ ብቻ ሳያተኩር የእግዚአብሔርን ባሕርያት በማጥናት እንዴት የበለጠ ጥቅም ማግኘት ይችላል? ከእግዚአብሔር ታላቅነት ጋር የተያያዙት የትኞቹ ባሕርያት ናቸው? ከመልካምነቱ ጋር የተያያዙት የትኞቹ ባሕርያት ናቸው? * የራስህ ሕይወትና አገልግሎት እግዚአብሔር የሁሉም አስደናቂ ባሕርያቱ አንድነት እንደሆነ እንደምትገነዘብ ያሳያል ወይስ ከሌሎቹ ይበልጥ የምታተኩረው በአንዱ ባሕርይ ላይ ነው? በዶክትሪን ጥናት ውስጥ ይህን የተለመደ ዝንባሌ እንዴት ማሸነፍ ይቻላል?
የተማሪው ትግበራ እና አንድምታ
ገጽ 257 11
1
Made with FlippingBook - Online magazine maker