God the Father, Amharic Mentor Guide

/ 3 5

እግዚአብሔር አብ

እነዚያ ሁሉ ሰዎችስ? ጌታን ከምታካፍላቸው ከጓደኞችህ አንዱ ጋር በምታደርገው ውይይት፣ስለ ጌታ እና ስለ ድነት ባላቸው አስተሳሰባቸው ውስጥ ሊገነዘቡት ያልቻሉትን ልዩ ችግር አጉልተው ያሳዩሃል። በኢየሱስ በኩል የእግዚአብሔርን የማዳን ሥራ ገና ያልሰሙ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በመኖራቸው ተጨንቆ፣ ጓደኛህ የክርስትና እምነት እጅግ ፍትሃዊ ያልሆነ ነው ብሎ እንደሚያስብ ተናግሯል። “እሺ፣ እግዚአብሔር ራሱን በፍጥረት ውበት ውስጥ እንደገለጠ እስማማለሁ - በጣም ድንቅ ነው። እኔ ግን አሁንም ችግር አለብኝ፤ አጠቃላይ መገለጥ አንድን ሰው በክርስቶስ እንዲያምን ለመምራት በቂ ካልሆነ፣ ስለ ክርስቶስ እስካሁን ያልሰሙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ዕጣ ፈንታ ምንድነው? ለዘላለም ጠፍተው ሊሞቱ ተፈርዶባቸዋልን? ስለ ኢየሱስ ለማወቅ ልዩ መገለጥ ካስፈለገህ፣ ታዲያ እነዚያ ሁሉ ሰዎችስ? የጓደኛህን ጥያቄ እንዴት ትመልሰዋለህ? የማይገኝ አምላክ በማህበረሰቡ ውስጥ ከፍተኛ የጥቃት ወንጀሎች መጠን እየጨመረ በመምጣቱ ቤተክርስትያንህ ለማህበረሰቡ አባላት አካባቢያዊ ሰፊ የጸሎት ስብሰባ እያስተናገደች ነው። የጸሎት ጉዞዎችን እና የጸሎት እንቅስቃሴዎችን በማደራጀት፣ በአሁኑ ወቅት እዚህ አካባቢ ላይ እየተፈጸመ ላለው አይነት ግፍ እና ጭካኔ ምክንያት የሆኑትን መንፈሳዊ ሀይሎች ማኅበረ ቅዱሳኑ ለይቶ አውቋል። በአንደኛው የጸሎት ጊዜ፣ የቤተ ክርስቲያናችሁ አካል ያልሆነ አንድ የማኅበረሰብ ነዋሪ ተነስቶ፣ “እኔ ወደዚህ ቤተ ክርስቲያን አልሄድም፤ እውነቴን ነው እኔ ወደ የትኛውም ቤተ ክርስቲያን አልሄድም ምክንያቱም እግዚአብሔር ለሌሎች እንደሚያስብ ለእኛ የሚያስብ ስለማይመስለኝ፣ ለምንድነው የእኛ ሰፈር ሁል ጊዜ የሚሸበረውና የሚጎሳቆለው? እርሱ እዚህ ታች ካለነው የህብረተሰብ ክፍል ይልቅ ጥሩ ኑሮ ለሚኖሩት ሰዎች የበለጠ ግድ የሚለው ይመስላል። መላው የጸሎት ስብሰባ በአንዴ ጸጥ አለ፣ ለዚህ ተስፋ ለቆረጠው ጎረቤትህ የልብ ጩኸት መልስ ለማግኘት ሁሉም ወደ አንተ ዞሮ ይጠባበቃል። በዚህ የጸሎት ስብሰባ ላይ ለዚህ ምልከታ ምን ዓይነት ማብራሪያና ማጽናኛ ትሰጣለህ? የቆሎ ጓደኛ የሆነው ጌታ “ጥልቅ ውዳሴና አምልኮ” በተሰኘው አዲስ የትኩረት አቅጣጫ ምክንያት በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያንህ አባላት መካከል ረዘም ላለ ጊዜ ውዝግብ ሲካሄድ ቆይቷል። በቀድሞው የዝማሬና የአምልኮ ሥርዓት የተሰላቸው አዲሱ የአምልኮ መሪ በአገልግሎቱ ውስጥ በጥልቀትና በግላዊ መንገድ ስለ እግዚአብሔር የሚናገሩ አዳዲስ የምስጋና እና የአምልኮ ዝማሬዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል። አንዳንድ አንጋፋ ምእመናን ይህን አካሄድ ይቃወማሉ፣ አዲሱ ሙዚቃ እና የአካሄድ ትኩረት እግዚአብሔርን የበለጠ ግላዊ እንዳደረገው እና እርሱ ከእኛ የተለየ አምላክ የመሆኑን ፍርሃት እንዳጠፋብን ይናገራሉ። የእግዚአብሔር ፍርሃት ጌታን እንደ ቆሎ ጓደኛ በማየት ተተክቷል ብለው ይፈራሉ። እንግዲህ እዚህ ጋር ማነው ትክክል እና ማነው ስህተት? ሁለቱም በአንድ ጊዜ ትክክል እና ስህተት ሊሆኑ ይችላሉ - እንዴት? አንተ የዚህች ቤተ ክርስቲያን መሪ ብትሆን፣ ሁለቱም ወገኖች የእግዚአብሔር ህልውና እና ልዕልና ለእግዚአብሔር ያለንን የአምልኮ ልምምድ እንዴት እንደሚያበለጽጉ እንዲረዱ እንዴት መርዳት ትችላለህ?

ጥናቶች

1

ገጽ 258  12

1

2

3

Made with FlippingBook - Online magazine maker