God the Father, Amharic Mentor Guide
/ 4 3
እግዚአብሔር አብ
የኒቂያን የእምነት መግለጫ (በአባሪው ውስጥ የሚገኝ) ካነበብክ እና/ወይም ከዘመርክ በኋላ የሚከተለውን ጸሎት ጸልይ: አምላክ ሆይ ከዓለም ውብ ነገሮች እይታ ወደ ፈጣሪያቸው ወደ አንተ አሳብ ምራን። የውበት መጀመሪያና ባለቤት፣ የስራህ ሁሉ ሉዓላዊ ጌታ፣ ለዘላለም የተባረከው አንተ በፍጥረትህ ውብ ነገሮች የምናገኘውን ደስታ በአንተ ደስ እንዲለን ስጠን ።
የኒቂያ የእምነት መግለጫ እና ጸሎት
~ Appleton, George, ed. The Oxford Book of Prayer. Oxford; New York: Oxford University Press, 1988. p. 62.
የኃይልና የችሎት ሁሉ ጌታ የመልካም ነገር ሁሉ ምንጭ እና ሰጪ፡ የስምህን ፍቅር በልባችን አኑር። በእኛ ውስጥ እውነተኛ ሃይማኖት ይጨምር፣ በመልካምነት ሁሉ ሙላን፣ በውስጣችንም የመልካም ሥራ ፍሬ ያብብ። ከአንተና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕያው ሆኖ በሚነግሥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አንድ አምላክ ከዘላለም እስከ ዘላለም። አሜን። ~ The Episcopal Church. The Book of Common Prayer and Administrations of the Sacraments and Other Rites and Ceremonies of the Church, Together with the Psalter or Psalms of David. New York: The Church Hymnal Corporation, 1979. p. 233.
2
ማስታወሻዎችህን አስቀምጥ፣ ሀሳብህን ሰብስበህ የትምህርት 1ን “ፕሮሌጎሜና፡ ትምህርተ እግዚአብሔር እና የመንግሥቱ መስፋት” ፈተና ውሰድ።
አጭር ፈተና ገጽ 260 3
የቃል ጥናት ክፍል ቅኝት
ከሌላ ሰው ጋር በመሆን ላለፈው ክፍለ ጊዜ የተመደበውን የቃል ጥናት ክፍል ፃፍ ወይም በቃልህ አንብብ: መዝ. 19.1-3
ባለፈው ሳምንት ለተሰጠው የንባብ የቤት ስራ መምህርህ የሚጠብቅብህን ዋና ዋና ነጥቦችና ማጠቃለያ አቅርብ (ንባብ ማጠናቀቂያ ገጽ)።
የቤት ስራ ማስረከቢያ
Made with FlippingBook - Online magazine maker