God the Father, Amharic Mentor Guide
4 2 /
እግዚአብሔር አብ
ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን። sui generis የሚለው ቃል (SUE-ee gin-air-us ይባላል) የላቲን ሀረግ ትርጉሙ፣ “በዓይነቱ ልዩ የሆነ” ወይም “የሚስተካከለው የሌለ ልዩ” ማለት ነው። በአጭሩ “በዓይነቱ ብቸኛው” የሚል ትርጉም አለው። ይህ እጅግ በጣም የምንወድደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክ እና አባትን የምንገልፅበት አስደናቂ መንገድ ነው። ለአንድ የእግዚአብሔር ሰው በጣም አስፈላጊ ከሆኑት እውነቶች አንዱ እግዚአብሔርን ሁሉን ለራሱ ደስታ እንደፈቃዱ እንደሚያደርግ እንደ ሉዓላዊ የመግቦት አምላክ መረዳት ነው። የጌታችን የኢየሱስ አምላክ እና አባት የሉዓላዊ ዓላማ አምላክ እንደሆነ ይህ እውነት በሁሉም የቅዱሳት መጻሕፍት ትምህርቶች እና ትእዛዛት ማዕከል ሆኖ ይገኛል። ይሖዋ እውነተኛ አምላክ፣ የሁሉም ነገር ፈጣሪና አኗሪ እንደመሆኑ መጠን በእሱ ዘንድ ተቀባይነት ባለው በማንኛውም ምክንያት የፈለገውን ማድረግ ይችላል። ሁኔታው ምንም ያህል አስፈሪ ቢመስልም፣ ችግሩም ምንም ያህል ከባድ ቢሆን፣ ሁኔታዎች ምንም ያህል አሳዛኝ ቢመስሉም፣ እርሱ የአብርሃም አምላክ፣ የጌታችን የኢየሱስ አምላክ፣ ያው ሙታንን የሚያስነሣና ሕይወትን ሁሉ የሚለውጥ ከራሱ ፈቃድና ዓላማ ጋር እንዲስማማ የሚያደርግ አምላክ ነው። የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ አጽናፈ ሰማይን ፈጥሮ በፈለገው መንገድ እንዲሄድ ትቶት ከዚያ ፈቀቅ ያለ አምላክ እንዳይደለ መጽሃፍ ቅዱስ ምስክርነት ይሰጣል። ለተወሰነ ጊዜ ክፋት እንዲኖር የፈቀደ ቢሆንም በልጁ በመሲሁ በኢየሱስ አማካኝነት ፍጥረቱን የመቤዠት ዕቅድ ከመጀመሪያው አንስቶ ነድፏል። አሁን ልጁ ቤዛነቱን ፈጽሟል፣ እርሱ በመረጠው ጊዜ ሁሉም ነገር ለዘላለም በሉዓላዊ አገዛዙ ሥር የሚመለስበትን ጊዜ ወስኗል። ከዚህም በተጨማሪ የተባረከና ብቸኛው ሉዓላዊ ገዥ በሆነው የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ በሆነው በኢየሱስ በኩል ይህን ሁሉ ለመፈጸም ወስኗል። ከላይ በጽሑፋችን ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ እንደገለጸው፣ በዚያ ማንም በማይቀርበው በአባቱ ብርሃን ውስጥ የሚኖረው፣ የማይሞተው ብቸኛው፣ ማንም ሰው የማያየው፣ ሊያየውም የማይችለው ሉዓላዊው አምላካችን ኢየሱስ ብቻ ነው። አምላካችን ሁሉን እንደ ጥበቡና ኃይሉ የሚሠራ የዓለማት ሉዓላዊ ፈጣሪ እውነተኛ አምላክ ነው። ፈቃዱን መቃወም ቢቻልም ነገር ግን በጭራሽ ማሸነፍ ወይም ማክሸፍ አይቻልም። እርሱ ሁሉን ፈጥሯል፣ ሁሉንም ደግፎ ይዟል፣ ሁሉንም ደግሞ ለራሱ ክብር ይጠቀልላል። እርሱ ሁሉንም ነገር ይጠብቃል፣ ሁሉን ያስተዳድራል፣ ሁሉንም ነገር እርሱ ወደ ወሰነው ፍጻሜው ይመራል፤ ኃሳቡንም ከመፈጸም የሚያግደው ምንም ነገር እና ማንም የለም። እርሱ አምላክ ነው! ይህ ታላቅ አምላክ አምላካችን ስለሆነ፣ ጳውሎስ “ክብርና የዘላለም ኃይል ለእርሱ ይሁን፤ አሜን” እንዳለ ለእርሱ የሚገባውን ክብር ልንሰጠው ይገባናል። ባለ ግርማ ሞገስ ለሆነው ለዚህ ታላቅ አምላክ የምንሰጠው አምልኮ እና ምንም ቅድመ ሁኔታ የሌለው መገዛት ብቻ ነው። እስቲ ይህንን ግባችን እናድርገው፣ ራሳችንን ከፍ ካለው ከዚህ ታላቅ አምላክ ሃሳብ ጋር ለማስማማት እና ለእርሱ በእውነት የሚገባውን ክብር እና ምስጋና ለመስጠት። በእውነት አምላካችን ምሳሌ የሌለው ልዩ አምላክ ነው።
2
Made with FlippingBook - Online magazine maker