God the Father, Amharic Mentor Guide
/ 4 5
እግዚአብሔር አብ
እግዚአብሔር እንደ ፈጣሪ፡ የእግዚአብሔር መግቦት ሴግመንት 1፡ የሁሉን ቻዩ የእግዚአብሔር አብ የኒቂያ ማረጋገጫ
ይዘት
ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ
ሁሉን ቻይ የሆነው እግዚአብሔር አብ ሰማይና ምድርን የፈጠረ፣ በፈጠረው ሁሉ ላይ ሉዓላዊ ነው፣ በሁሉም ቦታ የሕይወት ሁሉ ምንጭ ነው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩልም ሁሉን ደግፎ ያኖራል። እግዚአብሔር የሚያደርገው ሁሉ በሰማይና በምድር ሁሉ ስሙ ከፍ እንዲልና እንዲከበር ነው። የዚህ የሁሉን ቻዩ የእግዚአብሔር አብ የኒቂያ ማረጋገጫ የተሰኘ ሴግመንት አላማ የሚከተሉትን እንድታይ ለማስቻል ነው፦ • ሁሉን የሚገዛ የጌታችን የኢየሱስ አምላክና አባት በፍጥረትና በታሪክ ሁሉ ላይ የበላይ ባለሥልጣንና አሳቢ ገዥ መሆኑን። • እግዚአብሔር “የመግቦት” አምላክ መሆኑን፣ “በጽንፈ ዓለሙ ውስጥ ሉዓላዊ ፈቃዱን ይፈጽማል” ማለት ሲሆን ለራሱም ሆነ ለፍጥረታቱ ለበጎ ያለውን ዓላማውን ለመፈጸም ሁሉም ሁኔታዎች በእርሱ እንደተዘጋጁ። • እንደ ጌታ እና ፈጣሪ፣ እግዚአብሔር አብ በሁሉ ሉዓላዊ፣ የሁሉም ምንጭ እና በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ሁሉን ነገር ደግፎ አኗሪ መሆኑን። • እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ለራሱና ከፈቃዱ ጋር እንዲስማማ አድርጎ የሚመራው እና የሚያንቀሳቅሰው መሆኑን ይህም ለእርሱ ክብር ይሆን ዘንድ መሆኑን እንድታይ ነው።
የሴግመንት 1 ማጠቃለያ
2
I. ሁሉን ቻይ የሆነው እግዚአብሔር አብ በሁሉም ላይ ሉዓላዊ ነው።
የቪድዮ ሴግመንት 1 ዝርዝር
ሀ. በፍጥረት ሁሉ ላይ ሉዓላዊ ነው፣ 1ጢሞ. 6፡15-16።
1. አብ ሰማይንና ምድርን ፈጠረ, መዝ. 33.6.
2. ፍጥረት የእግዚአብሔር ነው፣ መዝ. 115.16.
3. እግዚአብሔር ለራሱ ዓላማ ከፍጥረቱ ጋር መስተጋብር ይፈጥራል።
Made with FlippingBook - Online magazine maker