God the Father, Amharic Mentor Guide
5 2 /
እግዚአብሔር አብ
7. እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ደግፎ በማኖሩ ሂደት ውስጥ ጌታችን ኢየሱስ ምን ሚና ይጫወታል? ኢየሱስ መላውን አጽናፈ ዓለም በመፍጠር ረገድ ምን ሚና ተጫውቷል? 8. ዋነኛው እና የማያከራክረው የፍጥረት ሁሉ ዓላማ ምንድን ነው? አጽናፈ ዓለሙ ይህን የላቀ ዓላማ በእርግጥ እንደሚፈጽም እንዴት እናውቃለን?
እግዚአብሔር እንደ ፈጣሪ፡ የእግዚአብሔር መግቦት ክፍል 2፡ የኒቂያው ማረጋገጫ አንድምታ
ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ
እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር በመጠበቅ እና በማስተዳደር ሉዓላዊነቱን ይገልፃል። እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ይጠብቃል ስንል ሁሉም ነገሮች በእግዚአብሔር ሉዓላዊ እንክብካቤ እና መግቦት አማካኝነት እንደሚኖሩ እና እንደሚቆዩ ይጠቁማል። በተመሳሳይም እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ይቆጣጠራል ስንል እግዚአብሔር በአጽናፈ ዓለሙ ውስጥ ሥልጣኑን እንደሚጠቀም እና ያሰበውን ማንኛውንም ነገር በፍጥረቱ እንደሚያደርግ እያረጋገጥን ነው። የዚህ የኒቂያው ማረጋገጫ አንድምታ የተሰኘ ሴግመንት ዓላማ የሚከተሉትን እንድትመለከት ለማስቻል ነው፡- • • የእግዚአብሔር ልዩ የመግቦት ስራ ሁሉንም ነገር በመጠበቅ እና በማስተዳደር ውስጥ ተገልጧል። • “ጥበቃ” የሚያመለክተው ሁሉም ነገሮች በእግዚአብሔር ሉዓላዊ እንክብካቤ እና መግቦት አማካኝነት እንደሚኖሩ እና እንደሚቆዩ ነው። • ስለ አጽናፈ ዓለም አመጣጥ የተሰጡ ንድፈ ሐሳቦች ምንም ይሁኑ ምን፣ ማንም እና ምንም ነገር እግዚአብሔር የፍጥረት ሁሉ ምንጭ ነው ከማለት ውጪ የሆነ ነጻነት አለኝ ሊል አይችልም። • “አገዛዝ” የሚያመለክተው እግዚአብሔር በፍጥረት ላይ ያሰበውን ማንኛውንም ነገር ለማድረግ ሙሉ ሥልጣን ያለውና በመላው ጽንፈ ዓለም ላይ ሉዓላዊ መሆኑን ነው። • እግዚአብሔር ፍጥረትን ሁሉ ከክፉ መጋለጥ በክርስቶስ የክብር ዳግም ምጽአት ያድነዋል። • የእግዚአብሔር መግቦትን በትክክል ማስተማር እንደ ፓንቴይዝም ፣ ዴይዝም ፣ ፋታሊዝም እና እጣፈንታ ያሉ አንዳንድ ዘመናዊ የፍልስፍና እና የስነ-መለኮትን ስህተቶችን ለማረም ይረዳል።
2
የሴግመንት 2 ማጠቃለያ
Made with FlippingBook - Online magazine maker