God the Father, Amharic Mentor Guide

/ 5 1

እግዚአብሔር አብ

ማጠቃለያ

1 ጢሞ. 1.17 ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይጠፋው ለማይታየውም ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።

» እግዚአብሔር አብ በፍጥረትና በታሪክ ሁሉ ላይ የበላይነትና የመግዛት ሥልጣን አለው።

» የአምላክ “መግቦት” የሚያመለክተው እግዚአብሔር ለራሱም ሆነ ለፍጥረታቱ ያለውን በጎ ዓላማውን ለመፈጸም ሲል ሁኔታዎች ሁሉ በእርሱ የተፈጠሩበትን ሉዓላዊ ፈቃዱን እንዲፈጽሙ የሚያደርግበትን እውነት ነው። » ሁሉን ቻይ የሆነው እግዚአብሔር አብ የሁሉ ሉዓላዊ ጌታ፣ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ የሁሉ ሕይወት ሰጪ ምንጭ እና ደግፎ አኗሪ ነው።

እባክህ በነዚህና በሌሎችም በዚህ ቪዲዮ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች በቂ ጊዜ ወስደህ ምላሽ ለመስጠት ሞክር፡፡ ይህ ሴግመንት በተለይ የእግዚአብሔርን “አምላክነት” ማለትም የጌታችን የኢየሱስ አምላክ እና አባት የሁሉ ነገር ሉዓላዊ ጌታ እንደሆነ፣ በፍጥረት ስር ላሉ ነገሮች ሁሉ ፍላጎቶችን በመፍጠር፣ በመደገፍ እና በማቅረብ ላይ ያለውን ሃሳብ ያረጋግጣል። እንዲህ ያለው ከፍ ያለ እውነት አንዳንድ የማወቅ ጉጉትን የሚፈጥሩ ወይም ማብራሪያ የሚፈልጉ ጥያቄዎችን ማስነሳቱ አይቀርም። እንደተለመደው መልሶችህ ግልፅ እና አጭር ይሁኑ፣ አስፈላጊ ሲሆን ደግሞ መልሶችህን በቅዱሳት መጻሕፍት አስደግፍ፡፡ 1. እግዚአብሔር የምድሩና የአጽናፈ ዓለሙ ሁሉ ፈጣሪና ባለቤት መሆኑን መገንዘብ እርሱን በሁሉም ነገር ላይ ሉዓላዊ ገዥ መሆኑን እንድንገነዘብ የሚረዳን እንዴት ነው? 2. ፍጥረት የእግዚአብሔር ከሆነ እና ሰማያትንና ምድርን ሁሉ የፈጠረው እርሱ ከሆነ ሁልጊዜ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር በሚፈልገው መልኩ የማይሆነው ለምንድነው? 3. እግዚአብሔር ከፍጥረት ጋር የሚገናኘው ለራሱ ዓላማ ነው ሲባል ምን ማለት ነው? ታዲያ እግዚአብሔር በየዓመቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት የሚቀጥፉት የመሬት መንቀጥቀጦች፣ አውሎ ነፋሳትና መናወጦች የእግዚአብሔር ዓላማ ናቸው ማለት ነው? 4. በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ በተከሰቱት ጦርነቶችና ውድመቶች ሁሉ መካከል እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር በምድር ላይ እንደ ፈቃዱ እየሠራ ነው ማለት የምንችለው እንዴት ነው? 5. መግቦት የሚለው ቃል ምን ማለት ነው? ይህ ጽንሰ-ሐሳብ እግዚአብሔር ከፈጠረው ጽንፈ ዓለሙ ጋር ያለውን ግንኙነት ግልጽ የሚያደርገው እንዴት ነው? 6. እንደ ቅዱሳት መጻሕፍት አባባል እግዚአብሔር የሁሉም ነገር ምንጭና መጋቢ ሊሆን የቻለው ለምንድን ነው? እግዚአብሔር ብርታቱን ፈጽሞ ሳያጣ ወይም በማንነቱ ምንም አይነት ድካም ሳይታይበት ሁሉን ነገር ደግፎ ማኖር የሚችለው እንዴት ነው?

መሸጋገሪያ 1

2

የተማሪው ጥያቄዎችና መልሶች

ገጽ 261  5

Made with FlippingBook - Online magazine maker