God the Father, Amharic Mentor Guide

5 4 /

እግዚአብሔር አብ

ሐ. እግዚአብሔር ዓለማትን ፈጥሯል፣ በምድርም ላይ ያሉትን ፍጥረታት ሁሉ ሕይወት ይጠብቃል፣ ኢሳ. 42.5.

የማይለካው የቅዱሳት መጻሕፍት ትምህርት ሁሉን ቻይ የሆነው ሰማያትንና ምድርን የፈጠረው የሚታየውንና የማይታየውን ሁሉ የፈጠረው እግዚአብሔር አብ ሥልጣኑ ሥራውንና ፍጥረቱን ሁሉ የሚነካ ሉዓላዊ አምላክ ነው የሚል ነው። ከእርሱ ውጭ ህይወት ያለው ነገር የለም፣ ከእርሱ እንክብካቤ ውጭ ራሱን ደግፎ የሚያኖር ነገር የለም፣ ማንም ሰው ህይወቱን ወይም ህልውናውን እርሱ ከወሰነው በላይ ለአንዲት ሰከንድ እንኳን ሊያቆይ አይችልም። እርሱ የሕይወት ጌታ ነው፣ የሁሉንም ነገር ሕይወት እንደ በጎ ፈቃዱ ይጠብቃል።

መ. እንቅስቃሴያችን እና መኖራችን ሁሉ በእግዚአብሔር ብቻ ነው፣ ሐዋ 17፡28.

ለ. በአጽናፈ ሰማይ ውስጥ ባሉት ነገሮች ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ጥበቃ አንድምታ

1. ስለ ዝግመተ ለውጥ ክርክርስ? አንድ ሰው የዝግመተ ለውጥ ሳይንስን እምነት መቀበሉ ሁሉን ቻይ የሆነው እግዚአብሔር አብ የሰማይና የምድር ፈጣሪ ነው የሚለውን እምነት እንዲክድ ያደርገዋል?

2

ሀ. የመጽሐፍ ቅዱስ ማዕከላዊ ዓላማ አምላክ የለሽ ተጠራጣሪዎችን የሚያረካ ሳይንሳዊ ማብራሪያዎችን መስጠት አይደለም፣ ነገር ግን ሁሉን ቻይ የሆነውን አብ የሁሉም ነገር ምንጭ እና አኗሪ መሆኑን በግልፅ መግለጥ ነው።

ለ. የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች በ21ኛው መቶ ዘመን ስለ ፍጥረት ጅማሬ ከተነሱት ክርክሮች የተለየ ዓላማ ነበራቸው፣ ይህ ማለት ግን ስለ አጽናፈ ዓለም የሰጡትን ትምህርት ችላ ማለት አለብን ማለት አይደለም። (1) እግዚአብሔር አብ የሰማይና የምድር ፈጣሪ ነው።

(2) እግዚአብሔር ከፈጠራቸው ዓለማት ጋር መነጻጸር የለበትም።

(3) ሕይወት ሁሉ ሕልውናውን የሚያገኘው በእግዚአብሔር ነው።

(4) ያለ እግዚአብሔር መግቦትና ጥንቃቄ ምንም ነገር አይኖርም ወይም አይቀጥልም፣ ሁሉም ነገሮች ምንጫቸውንና ሕይወታቸውን የሚያገኙት በእግዚአብሔር ነው።

2. እግዚአብሔር አጽናፈ አለምን ለመፍጠር በትክክል ምን ያህል ጊዜ ፈጅቶበታል - ሳምንት ወይስ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ዓመታት?

Made with FlippingBook - Online magazine maker