God the Father, Amharic Mentor Guide

/ 5 5

እግዚአብሔር አብ

ሀ. መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፍጥረት “ሳይንስ” የተለየ ዝርዝር መግለጫ ስለማይሰጥ፣ የጌታ ዋነኛ ዓላማ ስለ ፍጥረት “እንዴት” ሳይንሳዊ ማብራሪያ እንዳልሆነ መገመት እንችላለን። በእርግጥ ትኩረቱ “እንዴት” በሚለው ዝርዝር ሳይንሳዊ ማብራሪያ ላይ ሳይሆን “ማን” በሚለው ላይ ነው።)

ለ. መጽሐፍ ቅዱሳዊውን የአዳም የራስነት አቋም መቀበል አለብን (ይህም በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በሁሉም ቦታ እንዲሁም በራሱ በጌታ ኢየሱስ የተረጋገጠ ነው)።

ሐ. የአጽናፈ ዓለሙ የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚወሰነው ስለ አመጣጡ በሚነሱ አዳዲስ ሳይንሳዊ ንድፈ ሃሳቦች ላይ ሳይሆን ሁሉን ቻይ በሆነው በእግዚአብሔር አብ የመግቦት እቅድ ላይ ነው!

2

II. የእግዚአብሔር ልዩ የመግቦት ሥራ በሁሉም ነገር ላይ ባለው አገዛዙ ውስጥ ይገለጣል።

ሀ. በአጽናፈ ዓለሙ ላይ የእግዚአብሔር አገዛዝ ትርጓሜ

1. አገዛዝ = እግዚአብሔር የዓለማት ሉዓላዊ ገዥ ነው፣ ፍጥረቱን በወደደው መንገድ የመምራት ከፍተኛው ሥልጣን የእርሱ ነው፣ መዝ. 47.2.

2. እግዚአብሔር ሁሉን ይገዛል፣ አጽናፈ ሰማይ እና የታሪክ አካሄድ ሁሉ በእጁ ነው፣ 2ኛ ዜና. 20.6

3. የሰውን ጉዳይ ሁሉ ወደ አላማው ለመመለስ፣ ታላቅና ብርቱ ማድረግ በእግዚአብሔር እጅ ነው።

ሀ. እግዚአብሔር የመንግሥቱ ጌታ ነው፣ 1 ዜና. 29፡11-12።

ለ. ከአሕዛብ በላይ ከፍ ከፍ ብሏል መዝ. 47.8.

Made with FlippingBook - Online magazine maker