God the Father, Amharic Mentor Guide
8 4 /
እግዚአብሔር አብ
ማጠቃለያ
» የእግዚአብሔር ቃል አንድ እግዚአብሔር ብቻ እንዳለ ያስተምራል ነገርግን ይህ እግዚአብሔር ራሱን እንደ እግዚአብሔር አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ገልጧል። » ከዚህም በተጨማሪ ቅዱሳት መጻሕፍት የሚያስተምሩት እግዚአብሔር አንድ አምላክ መሆኑን ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር ሦስት አካላት ማለትም አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ መሆኑንም ይናገራሉ።
እነዚህን እና ሌሎች ቪዲዮው ያነሳቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ የምትችለውን ያህል ጊዜ ውሰድ። በሥላሴ ላይ ያለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ለመረዳት እና ለመገንዘብ ቀላልም ፈጣንም አይደለም። መረዳት ያለብን ግን፣ ሥላሴ እንደ አንድ አምላክ የእግዚአብሔርን አንድነት፣ እና የአብ፣ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስን መለኮትነት በሙሉ ሥልጣንና ታማኝነት ለመቀበል የሚደረግ ሙከራ መሆኑን ነው። በዚህ ጠቃሚ ትምህርት ላይ ቁልፍ የሆኑትን ፅንሰ-ሀሳቦች አሰላስል፣ የምታቀርበውንም ማንኛውንም ሃሳብ ከቅዱሳት መጻህፍት ጋር አብረው መሄዳቸውን ለመከላከል መቻልህን አረጋግጥ (ሐዋ. 17፡11)። 1. “ትምህርተ ሥላሴ” ማለት ምን ማለት ነው? ይህ ቃል የሚያመለክተው የትኛውን የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርት ነው? 2. እግዚአብሔር አንድ መሆኑን እና የአብ፣ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስን መለኮትነት ቅዱሳት መጻሕፍት እንዴት እንደሚያረጋግጡ ጠቅለል አድርገህ ጻፍ። 3. እያንዳንዱ የሥላሴ አካል (አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ) አምላክ መሆኑን ለማስረገጥ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃዎችን ምሳሌዎችን ስጥ (ማለትም፣ እያንዳንዱ አካላት የእግዚአብሔርን ባሕርያት እንዴት እንደያዙ፣ የእግዚአብሔርን ሥራ እንደሚሠሩ፣ አምላክ እንደሚባሉ እና እንደ አምላክ ሥልጣን እንደሚኖራቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ አሳይ)። 4. ሁለቱንም የእግዚአብሔርን አንድነት እና የእግዚአብሔርን ብዝሃነት ማረጋገጥ የምንችለው ከምን አንጻር ነው? 5. የእግዚአብሔር አካላት እና የእግዚአብሔር ነጠላ ማንነት ትርጉም እና ግንኙነት ምንድን ነው? ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ በሥላሴ ላይ የሚሰጠውን ትምህርት ለመረዳት እንዴት ሞከረች (ምሳሌ ዘርዝር)። 6. የሥላሴን ሐሳብ ሦስት አማልክት ናቸው ማለት ነው ብሎ መግለጽ ፈጽሞ ትክክል ያልሆነው ለምንድን ነው? ቤተክርስቲያን ሦስቱን የእግዚአብሔር አካላት ለማረጋገጥ እና የእግዚአብሔርን ነጠላ አምላክነት ለመለየት መጠንቀቅ ያስፈለጋት ለምንድነው?
መሸጋገሪያ 1
የተማሪው ጥያቄዎች እና ምላሾች
ገጽ 269 4
3
Made with FlippingBook - Online magazine maker