God the Father, Amharic Mentor Guide

/ 8 5

እግዚአብሔር አብ

7. የእምነት መግለጫዎች ትምህርተ ሥላሴን በተመለከተ እውነት ያልሆነውን እንድንገነዘብ የሚረዳን እንዴት ነው? ከእነዚህ ሃሳቦች - የእግዚአብሔር አንድነት፤ በአብ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ መካከል ያለው ልዩነት እና የአካላት እኩልነት - ውስጥ አንዱን ክደህ አሁንም ስለ ስላሴ ተቀባይነት ያለው አመለካከት ሊኖርህ ይችላል?

አምላከ ሥላሴ፡ የእግዚአብሔር ታላቅነት ሴግመንት 2፡ የእግዚአብሔር የሦስትነት ክብር፡ ሥላሴ

ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ

የሴግመንት 2 ማጠቃለያ

ሁሉን ቻይ የሆነው፣ ብዙ ጊዜ የሥላሴ የመጀመሪያ አካል ተብሎ የሚጠራው፣ እግዚአብሔር አብ ስለ ታላቅነቱ በኃይል እና በፍፁም የሚናገሩ ባህሪያት አሉት። በሁሉም መንገድ፣ እግዚአብሔር አብ መንፈስ ነው፣ በራሱ ሕይወት ያለው፣ ትክክለኛ ባሕርይ ያለው፣ በመለኮታዊ ባሕርዩና ጠባዩ ወሰን የለሽ ነው፣ ማንነቱም ፈጽሞ የማይለወጥ ነው። የዚህ የእግዚአብሔር የሶስትነት ክብር፡ ሥላሴ የተሰኘ ሴግመንት አላማ የሚከተሉትን እንድታይ ለማስቻል ነው፡- • ሁሉን ቻይ የሆነው እግዚአብሔር አምላክ ነው፣ እናም በባሕርይው ውስጥ የታላቅነት መለኮታዊ ባሕርያት አሉት። • ሁሉን ቻይ የሆነው አብ መንፈስ እንጂ ከቁስ አካል ወይም ከሥጋዊ ተፈጥሮ የተዋቀረ አይደለም። • ሁሉን ቻይ የሆነው እግዚአብሔር አብ ደግሞ ሕይወት አለው፤ ይህም ህይወት የማይጠፋና የማይሞት ነው። • ሁሉን ቻይ የሆነው እግዚአብሔር አብ ስብዕና ነው፣ ራሱን የሚያውቅ፣ የማወቅ፣ የመሰማት እና የመምረጥ ችሎታ ያለው እና ከሌሎች ፍጥረታት ሁሉ ጋር መገናኘት የሚችል ነው። • እግዚአብሔር አብ ወሰን የለሽ ነው፡ በህዋ ላይ እርሱ በሁሉም ቦታ አለ፣ በጊዜውም ዘላለማዊ ነው፣ በእውቀትም እርሱ ሁሉን አዋቂ ነው፣ እና በስልጣን ላይ እርሱ ሁሉን ቻይ ነው። • ሁሉን ቻይ የሆነው እግዚአብሔር አብ በመጨረሻ የማይለወጥ እና የማናወጥ ነው፡ ሁል ጊዜም ቢሆን የሆነውን ነው፣ እናም በፍጽምናው፣ በክብሩ እና በትልቅነቱ አይለወጥም።

3

Made with FlippingBook - Online magazine maker