God the Father, Amharic Mentor Guide
/ 9 9
እግዚአብሔር አብ
ትክክለኛ ባሕርይ ያለው፣ በመለኮታዊ ተፈጥሮውና በባሕርይው ወሰን የለሽ ነው፣ ማንነቱም ፈጽሞ አይለወጥም።
ስለ ሥላሴ ተፈጥሮ እና ሁሉን ቻይ ስለሆነው እግዚአብሔር አብ ታላቅነት ተጨማሪ ሀሳቦችን ለመከታተል ፍላጎት ካለህ እነዚህን መጻሕፍት መመልከት ይረዳህ ይሆናል (አስተውል፣ እነዚህ ቀላል ንባቦች አይደሉም!) Charnock, Stephen. The Existence and Attributes of God. Grand Rapids: Baker Book House, 1996. O’Collins, Gerald, S. J. The Tripersonal God: Understanding and Interpreting the Trinity. Mahwah, NJ: Paulist Press, 1999. White, James R. The Forgotten Trinity: Recovering the Heart of Christian Belief. Bloomington, MN: Bethany House Publishing, 1998. የሥላሴ አስተምህሮ እና የእግዚአብሔር አብ ታላቅነት የሚመረመሩ እና የሚቀርቡ ሥነ-መለኮታዊ ጭብጦች ብቻ አይደሉም። በተቃራኒው እነዚህ የእምነት ታላላቅ እውነቶች ናቸው፣ በእነርሱም ላይ ለረጅም ጊዜ የሚያሰላስሉ ሰዎች ከጥልቅ ጥሞናቸው የተነሳ ለዘላለም ይለወጣሉ። እነዚህን ታላላቅ እውነቶች ከህይወትህ እና ከአገልግሎትህ ጋር ማዛመድ ሊለውጥህ ይችላል፤ ዋጋውም የእግዚአብሔርን ቃል በራስህ ህይወት ላይ ያተኮረ ማድረጉ ነው። በዚህ ትምህርት ላይ በተሰጡት ሃሳቦች ላይ ስታሰላስል፣ መንፈስ ቅዱስ እዚህ ካመለከተህ እውነቶች የተነሳ እንዴት እንድታድግ፣ እንድትለውጥ ወይም የአገልግሎት አቀራረብህን እንድትቀይር እንደሚፈልግ ጌታን ጠይቅ። በእነዚህ እውነቶች ላይ ስታሰላስልና ከእነዚህም ጋር ስለተገናኘው ስለራስህ ህይወት እና አገልግሎት ስታስብ፣ ስለእነዚህ እውነቶች የእግዚአብሔር መንፈስ አሁን ምን እንድታደርግ እየጠራህ እንደሆነ ለማወቅ ሞክር። በእግዚአብሔር ተፈጥሮ እና ታላቅነት እውነት ላይ በማሰላሰል በጌታ ፊት ጊዜ አሳልፍ፤ ትምህርቱንም እንዴት እና በምን መንገድ እንደምትተገብረው ጌታን ጠይቅ። እንዲሁም፣ ለዚህ ሞጁል የአገልግሎት ፕሮጄክትህን ለመጻፍ በምታስብበት ወቅት ስራህን ከእነዚህ ጭብጦች ጋር ማገናኘት ትፈልግ ይሆናል። ምሪትን በሚመለከት የጌታን ፊት ፈልግ፤ ግንዛቤዎችህንም በክፍልህ ላሉ ሌሎች ተማሪዎች ለማካፈል ዝግጁ ሆነህ በሚቀጥለው ሳምንት ተመለስ። ስለ እግዚአብሔር ተፈጥሮ እንደ ስላሴ እና ስለ እግዚአብሔር አብ ታላቅነት በእነዚህ እውነቶች ላይ በማሰላሰል አንድ ሰው በግል ህይወቱ ብቻ ሳይሆን በምንወዳቸው እና በምናገለግላቸው ሰዎች ህይወት ውስጥ ሁሉንም ፍላጎቶች ለማሟላት የአምላካችንን በቂነት ማየት ይጀምራል። ምናልባት በዚህ ትምህርት ሂደት ውስጥ፣ የእግዚአብሔር አብን ታላቅነት እያሰላሰልክ፣ አንዳንድ ወሳኝ ፍላጎቶችን እንድታውቅ ተደርገሃል። መንፈስ ቅዱስ በአንድ የተወሰነ ጉዳይ፣ ፍላጎት ወይም አሳሳቢ ጉዳይ ላይ እንድታተኩር አድርጎሃል፣ ጌታንም ለዚህ ጥንካሬ እና እርዳታን እንድትጠይቀው ያስፈልግሃል። ፍላጎቶቻችሁን ለመካፈል እና አንዳችሁ ለሌላችሁ ለመጸለይ ጊዜው አሁን ነው። አሁን አብራችሁ ለመማለድ ጊዜው የማይፈቅድ ከሆነ፣ ሸክምህን የምታካፍለውና ልመናችሁን አብራችሁ ወደ ጌታ
ማጣቀሻዎች
የአገልግሎት ግንኙነቶች
3
ምክር እና ጸሎት
Made with FlippingBook - Online magazine maker