God the Father, Amharic Mentor Guide
9 8 /
እግዚአብሔር አብ
አንድ አምላክ፣ በሦስት መልክ በቅርቡ አንድ ታዋቂ ቴሌቫንጀሊስት/ሰባኪ በክርስቲያን ማህበረሰብ ውስጥ ስለ ሥላሴ የብዙዎችን ቀልብ የሳበን እይታ አውጥቷል። በሦስት የተለያዩ አካላት (አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ) ራሱን የሚገልጥ አምላክ አንድ አምላክ ነው የሚለውን ትውፊታዊ ክርስቲያናዊ አመለካከት ከማረጋገጥ ይልቅ፣ ይህ ታዋቂ መምህር እንደሁኔታው ራሱን በሦስት መልክ የሚገልጥ አንድ አምላክ እንዳለ ያምናል። በሌላ አነጋገር፣ እግዚአብሔር አንድ መሆኑን ቢያረጋግጥም፣ የሥላሴ አካላት ግን የተለያዩ አካላት መሆናቸውን ይክዳል። ራሱን በሦስት የተለያዩ መንገዶች የሚገለጥ አንድ አምላክ ብቻ ነው። ይህ አመለካከት በእግዚአብሔር ቃል መሠረት ተቀባይነት የሌለው የሚሆነው ለምንድን ነው? ይህን አመለካከት እንደ ምንፍቅና መቁጠር ይቻላል? ለምን? “ትንሽ የበዛ ወዳጅነት” በዚህ ወቅት ያሉት ብዙዎቹ የምስጋና እና የአምልኮ መዝሙሮች አማኙ ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ቁርኝት እና ግላዊ ግንኙነት ያጎላሉ። ብዙዎቹ መዝሙሮች ስለ እግዚአብሔር ወዳጅነት፣ ታማኝነት፣ እንዲሁም አፍቃሪነት ያወሳሉ፤ ከእግዚአብሔር ጋር ባለን ግንኙነት ግላዊ ገጽታ ላይ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣሉ። ነገር ግን፣ በብዙ ቤተክርስቲያናት ውስጥ ጽኑ አስተምህሮ ባለመኖሩ፣ እና በአብዛኞቹ ሕብረቶች ውስጥ አስተምህሯዊ ዝማሬዎች እየቀነሱ ባሉበት ሁኔታ በርካታ አማኞች ሁሉን በሚችል የእግዚአብሔር አብ ታላቅነት ባህሪያት ላይ ምንም ዓይነት ግንዛቤ እንደሌላቸው ግልጽ ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ፣ የብዙ አብያተ ክርስቲያናት አምላክ የልባችንን ፍላጎት ብቻ የሚያሟላ፣ የዓለምን ችግሮች የማይፈታ፣ ሌላው ቀርቶ አጽናፈ አለሙ ከቁጥጥሩ ውጭ የሆነበት አይነት ነው። ይህንን ሁኔታ አንድ ሰው እንደገለጸው፡- “የብዙ አብያተ ክርስቲያናት አምላክ ጥሩ ወዳጅ ነው፣ ነገር ግን ታላቁ አምላክና መድኃኒታችን፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት አይመስልም። የሚበላ እሳት ከሆነው ከእርሱ ጋር ትንሽ የበዛ ወዳጅነት ያለን እንመስላለን። በቤተክርስቲያንህ ውስጥ የሙዚቃ እና የአምልኮ አገልጋይ እንድትሆን ጌታ እንደጠራህ አስብ። በቤተክርስቲያንህ ውስጥ ያሉ አማኞች በአምልኮ እና በጋራ ህይወታችሁ ስለእግዚአብሔር ታላቅነት የበለጠ፣ የበለጸገ እና የጠለቀ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረዳትንና መደነቅን እንዲያገኙ ለመርዳት ስምንት የተለያዩ አጽንዖቶችን ወይም ነገሮችን ዘርዝር። የሥላሴ አስተምህሮ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ ነው፣ የእግዚአብሔር ተፈጥሮ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ አይነት ማንነት ያላቸው የሦስት አካላት አንድነት መሆኑን ያረጋግጣል። መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር አንድ አምላክ እንደሆነ ይናገራል (ዘዳ. 6.4)፣ ነገር ግን ይህ አንድ አምላክ በሦስት የተለያዩ ግን እኩልና ዘላለማዊ የሆኑ አካላት እንደሚኖር ይናገራል፤ እያንዳንዳቸውም በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ አምላክ ተብለው ተጠቅሰዋል፣ እንዲሁም የመለኮትን ባሕርይ ክብር ይካፈላሉ። ቅድስት ሥላሴ (ማለትም፣ እግዚአብሔር አብ፣ ወልድ፣ እና መንፈስ ቅዱስ) ቅዱሳት መጻሕፍት የራሳቸውን የአንድ አምላክ አካላት አንድነት፣ ልዩነት እና እኩልነት ለማረጋገጥ የተሰጠ ስም ነው። የሥላሴ የመጀመሪያ አካል የሆነው ሁሉን ቻይ የሆነው እግዚአብሔር አብ፣ ስለ ታላቅነቱ በኃይል እና በትክክል የሚናገሩ ባሕርያት አሉት። እግዚአብሔር አብ መንፈስ ነው፣ በራሱ ሕይወት ያለው፣
2
3
3
የትምህርቱን ንድፈ ሃሳብ በድጋሚ መጻፍ
Made with FlippingBook - Online magazine maker