The Kingdom of God, Amharic Mentor Guide
/ 1 2 3
የ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር መ ን ግ ስ ት
የሚኒስትሪ ፕሮጀክቱ የተነደፈው ለዚህ ነው፣ በሚቀጥሉትም ቀናት እነዚህን ግንዛቤዎች በእውነተኛ ህይወት እና በአገልግሎት አካባቢዎችህ ለማካፈል እድሉን ታገኛለህ። በፕሮጀክትህ ውስጥ ያስተዋልከውን ስታካፍል እግዚአብሔር ማስተዋል እንዲሰጥህ ጸልይ።
በዚህ ትምህርት በጥናትህ ምክንያት ጸሎት የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች፣ ሰዎች፣ ሁኔታዎች ወይም እድሎች አሉ? በዚህ ትምህርት ላይ ትኩረት ያደረገ ልመና እና ጸሎት የሚያስፈልጋቸው እግዚአብሔር በልብህ ላይ ያስቀመጣቸው ጉዳዮች ወይም ሰዎች እነማን ናቸው? ይህንን ለማሰላሰል ጊዜ ውሰድ፣ መንፈስም እንደመራህ በምክር እና በጸሎት አስፈላጊውን ድጋፍ ተቀበል።
ምክር እና ጸሎት
ምደባዎች
የቤት ስራ ማስረከቢያ የለም
የቃል ጥናት ጥቅስ
የቤት ስራ ማስረከቢያ የለም
የንባብ የቤት ስራ
የአገልግሎት ፕሮጄክትህ እና የትርጓሜ ፕሮጄክትህ አሁን ሊገለጹ፣ ሊወሰኑ እና በአስተማሪህ ተቀባይነት ሊኖራቸው ይገባል። ስራህን በወቅቱ ማቅረብ እንድትችል አስቀድመህ ማቀድህን አረጋግጥ።
ሌሎች የቤት ስራዎች
ገጽ 319 17
4
የመጨረሻው በቤት የሚሰራ ፈተና ይሆናል ፤ ከመጀመሪያዎቹ ሶስት ፈተናዎች የተወሰዱ ጥያቄዎችን ፣ ከዚህ ትምህርት የተገኙ አዳዲስ ጥያቄዎችን እና አጫጭር ምላሾችን የሚጠይቁ የጹሑፍ ጥያቄዎችንም ያጠቃልላል ፡፡ እንዲሁም በፈተናው ላይ ለትምህርቱ የተሰጡትን የቃል ጥናት ጥቅሶች በማንበብ ወይም በመፃፍ ላይ መዘጋጀት አለብህ፡፡ ፈተናህን ስታጠናቅቅ እባክህ ለመምህርህ በማሳወቅ ቅጂህን ማግኘቱን አረጋግጥ። ማስታወሻ - የመጨረሻውን ፈተና ካልወሰድክ እና ለአስተማሪህ የተሰጡትን የቤት ስራዎች ሁሉ (የሚኒስትሪ ኘሮጀክት ፣ የኤክሴጀሲስ ፕሮጀክት እና የመጨረሻ ፈተና) ባግባቡ ካላጠናቀቅህ በዚህ ሞጁል የሚኖርህን አጠቃላይ ውጤት ማስላት አይቻልም። እግዚአብሔርን ይመስገን፣ በእግዚአብሔር መንግሥት ላይ ያለውን የካፕስቶን ሞጁል ጨርሰሃል፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር መንግሥት ላይ ያሉትን የበለጸጉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሀብቶች መመርመር ጀምረሃል። ለሕይወትና ለአገልግሎት የምትፈልጉት ሁሉ ይጨመርላችሁ ዘንድ አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ትፈልጉ ዘንድ እግዚአብሔር ጸጋንና ጥበብን ይስጣችሁ። አሜን።
የማጠቃለያ ፈተና ማስታወቂያ
ስለዚህ ትምህርት (ሞጁል) የመጨረሻ ቃል
ገጽ 320 18
Made with FlippingBook Digital Publishing Software