The Kingdom of God, Amharic Mentor Guide

/ 1 5

የ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር መ ን ግ ስ ት

እግዚአብሔር በእርግጥ ከወደደን . . . በቅርቡ ልጁ አላስፈላጊ በሆነ የወሮበሎች ቡድን ተኩስ ወደተገደለበት አንድ ውድ ቤተሰብ ቤት እንደሄድክ አስብ። ቤተሰቡን ለማጽናናት በምትሞክርበት ጊዜ ከቤተሰቡ አባላት አንዱ በተሰብሳቢዎቹ ሁሉ ፊት እንዲህ ብሏል:- “ይህ መከሰቱ እግዚአብሔር በእርግጥ እንደማይወደን ያሳያል። እግዚአብሔር በእውነት ከወደደን እንደዚህ አይነት ነገሮች በፍፁም አይሆኑብንም ነበር። መልካም አምላክ እንደዚህ አይነት ነገር በጣም ወጣት እና በጣም ንጹህ በሆነ ሰው ላይ እንዲደርስ እንዴት ይፈቅዳል?” ለእርሱ እና ለእንደዚህ አይነቱ አሳዛኝ ክስተት ይህን አይነት አስተያየት ለሰሙት ለሌሎቹ ምላሽህ ምን ይሆን?

3

1

የእግዚአብሔር መንግሥት ተግዳሮት ገጠመው ክፍል 1

ይዘት

ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ

እግዚአብሔር እንደ ጌታ በሁሉ ላይ ነግሷል፣ ነገር ግን ግዛቱ ተግዳሮት የገጠመው በሰማያት ባለው ሰይጣናዊ አመጽ፣ እና በምድር ላይ በነበሩት የመጀመሪያዎቹ ባልና ሚስት በፈቃደኝነት በማመጻቸው እና ባለመታዘዛቸው ነው። ይህ ተግዳሮት በፍጥረት ላይ ወደ ሞት የሚያደርስ እና ከሁሉም የሰው ልጆች አሳዛኝ ክስተቶች ሁሉ ትልቁ የሆነውን በቤተክርስቲያን “ውድቀት” ተብሎ የሚጠራውን እርግማን አስከትሏል። ለዚህ የእግዚአብሔር መንግሥት ተግዳሮት ገጠመው የተሰኘ ትምህርት የመጀመሪያ ክፍል አላማችን የሚከተሉትን እንድታይ ለማስቻል ነው፡- • እግዚአብሔር የአጽናፈ ሰማይ ሉዓላዊ ግርማ ነው። • ጌትነቱን በዲያብሎስና በመላእክቱ እንዲሁም በመጀመሪያዎቹ ባልና ሚስት አዳምና ሔዋን በአትክልቱ ስፍራ ሆን ብለው ባለመታዘዛቸው ተግዳሮት ገጠመው። • በዓለም ውስጥ ያለው ኃጢአት የሚከሰተው በዚህ የእግዚአብሔርን ግርማ እና የግል መንግሥቱን ንግሥና በመቃወም ነው። • የእግዚአብሔር ሐሳብ ሰማይንና ምድርን ሁሉ በንግሥናው ወደነበረበት መመለስ እና እንደገና ስሙ ብቻ የሚከበርበትን ፍትሃዊ እና ሰላሙ ለዘላለም የሚገዛበትን አጽናፈ ሰማይ ማቋቋም ነው።

የክፍል 1 ማጠቃለያ

ገጽ 280  6

Made with FlippingBook Digital Publishing Software