The Kingdom of God, Amharic Mentor Guide
/ 5
የ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር መ ን ግ ስ ት
የሞጁሉ መግቢያ
ሃያል በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ላንተ ይሁን!
የናዝሬቱ ኢየሱስ ከሰበካቸውና ካስተማራቸው ትምህርቶች ሁሉ፣ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ርዕሰ ጉዳይ ያስተማረውን ያህል ጉልህና አከራካሪ ጉዳይ የለም። ወግ አጥባቂዎቹም ሆኑ ሊበራል ሊቃውንት የኢየሱስ ተወዳጅ ርዕሰ ጉዳይና በብዛትም የሰበከው እና ያስተማረው ስለ እግዚአብሔር መንግሥት እንደሆነ ይስማማሉ። ይህ የድነት መልእክቱ፣ ማስተር ፕላኑ እና የሥነ-መለኮቱ ልብ ነበር። በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ዘመናዊቷ ቤተክርስቲያን ኢየሱስ በትንቢታዊ እና በመሲሐዊ አገልግሎቱ ውስጥ በጣም አስፈላጊ ነው ብሎ ለሚጠራው ነገር ብዙም ትኩረት የሰጠች አይመስልም። እንግዲህ ተስፋችን ልብህ በመንግሥቱ ታሪክ - በንጉሡ እና በመንግሥቱ - እንደሚያዝና በግል ደቀ መዝሙርነት እና አገልግሎት ህይወትህ ውስጥ ያለውን ጠቀሜታ እንደምትመለከት ነው። የእግዚአብሔር አገዛዝ ተግዳሮት ገጠመው የሚለው የመጀመሪያው ትምህርት በእግዚአብሔር ሉዓላዊ ግርማ ላይ ያተኩራል። በዲያብሎስና በመላእክቱ እንዲሁም በመጀመሪያዎቹ ባልና ሚስት አዳምና ሔዋን በገነት ውስጥ ሆን ብለው ባለመታዘዛቸው የእግዚአብሔርን ፍፁም ሉዓላዊነት እና ጌትነት እንዴት እንደተቃወመ ያብራራል። ይህ አመፅ በአለም፣ በሰው ተፈጥሮ እና የአጋንንትን ወደ አለም መልቀቅ አሳዛኝ ውጤቶችን አስገኝቷል። እኛ ምንም ያህል ብናምጽም እንኳን እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ሁሉ በንግሥናው ሊመልስ እና ስሙ የሚከበርበት እና ፍትሐዊው ሰላምም ለዘላለም የሚገዛበት አጽናፈ ሰማይን ሊፈጥር ይፈልጋል። በሁለተኛው ትምህርታችን፣ በተመረቀው የእግዚአብሔር መንግሥት፣ በውድቀት ምክንያት የመጡትን ሁሉንም አለመታዘዝ እና አመጽን ለማጥፋት ያለውን የእግዚአብሔርን ሐሳብ እንመረምራለን - እግዚአብሔር በዚህ በወደቀው ዓለም ውስጥ ተዋጊ ይሆናል። በእርሱ በኩል ሰላምና የፍትህ መንግሥት ወደ ምድር የሚመጣበትን ዘር እንደሚያመጣ እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር ቃል ኪዳን ገብቷል ። ይህ የቃል ኪዳን ተስፋ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር፣ ለእስራኤላውያን ሕዝብ፣ ለይሁዳ ነገድ እና በመጨረሻም ለዳዊት ቤተሰብ ታድሷል። እዚህ ጋር የእግዚአብሔር መንግሥት ወደዚህ ወደ ወደቀና በኃጢአት ወደ ተረገመ ዓለም እንዴት እንደሚመለስ የመሲሑን አመጣጥ በደማቁ እንመለከታለን። የናዝሬቱ ኢየሱስ የመንግሥቱ መገኘት ማረጋገጫ ሲሆን ይህም የእግዚአብሔር አገዛዝ በሥጋ በመገለጡ፣ በሞቱ፣ በትንሣኤው እና በማረጉ ነው። በትምህርት ሶስት እና አራት እንደየቅደም ተከተላቸው ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ወረራ እና የእግዚአብሔር አገዛዝ ፍጻሜ እንመለከታለን። አሁን ጌታችን ኢየሱስ ሞቶ፣ ተነሥቷል፣ ወደ ሰማይም ካረገ በኋላ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት በየቤተክርስቲያናቱ በዓለም ሁሉ እየተሰበከ ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ማዕከል - የእግዚአብሔር የማዳን ስፍራ ወይም አውድ፣ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል መገኘት እና የእውነተኛው መንግሥት ሰላም፣ የእግዚአብሔር መገኘት እና ኃይል በነጻነት የሚታዩበት ቦታ ነው። የእግዚአብሔር መንግሥት በኢየሱስ ዳግም ምጽዓት ትፈፀማለች: ሞት፣ ደዌ፣ እና ክፋት ሁሉ የሚደመሰሱበት፣ ሰማይና ምድር ሁሉ የሚታደሱበት፣ እግዚአብሔርም ሁሉ-በሁሉ የሚሆንበት ይሆናል።
Made with FlippingBook Digital Publishing Software