The Kingdom of God, Amharic Mentor Guide
/ 9 9
የ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር መ ን ግ ስ ት
ለ. መጽሐፍ ቅዱስ ከሞት በኋላ ስለንቃተ ኅሊና መኖር በበርካታ ቦታዎች ላይ ያስተምራል። (1) ባለጠጋው ሰው እና አልዓዛር፣ ሉቃስ 16፡19-31 (2) ኢየሱስ በመስቀል ላይ ለነበረው ወንበዴ “እውነት እውነት እልሃለሁ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ” ሉቃ 23፡43
(3) ኢየሱስ በራሱ መንፈስ ለእግዚአብሔር የሰጠው አደራ፣ ሉቃስ 23፡46
(4) ጳውሎስ ሊሄድ እና ከክርስቶስ ጋር መሆን ይፈልጋል፣ ይህም ከሞት በኋላ ከኢየሱስ ጋር በንቃተ ህሊና ያለውን ግንኙነት ያመለክታል፣ ፊልጵ. 1.23.
ሐ. ከሥጋ መለየት ከጌታ ጋር መገኘት ማለት ነው፣ ማለትም ከእርሱ ጋር በንቃተ ኅብረት መሆን እንደሆነ የሚጠቁሙትን ጽሑፎች በቁም ነገር ልንመለከታቸው ይገባል፣ 2ኛ ቆሮ. 5.8.
ሐ. መካከለኛው ሁኔታ እንደ ፐርጋቶሪ
1. ስለ ሞት የካቶሊክ አመለካከት አጠቃላይ እይታ
4
ሀ. አንድ ሰው ከሞተ በኋላ ወዲያውኑ ዘላለማዊ ሁኔታው ይወሰናል።
ለ. በክፋት ውስጥ የሞቱት በቀጥታ የሥቃይ ቦታ ወደሆነው ወደ ሲኦል ይሄዳሉ፣ እንዲሁም በጸጋ ውስጥ እና በሞት ጊዜ የነጹት በቀጥታ ወደ መንግሥተ ሰማያት ይሄዳሉ።
ሐ. በጸጋ ሁኔታ ውስጥ ሆነው በመንፈሳቸው ፍፁም ያልሆኑት ደግሞ ሙሉ በሙሉ ከሥጋዊ ኃጢአታቸው ወይም ከመተላለፋቸው ነፃ ስላልሆኑ የጊዜያዊ ቅጣት ቦታ ወደሆነው ወደ ፐርጋቶሪ ይሄዳሉ።
Made with FlippingBook Digital Publishing Software