The Kingdom of God, Amharic Student Workbook
/ 1 0 9
የ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር መ ን ግ ስ ት
ለ. ትልቁን ገጽታ መረዳት፡- መንግሥቱን የሚፈፀመው በእግዚአብሔር ጊዜ በኢየሱስ ነው። (1) የቅዱሳት መጻሕፍት ተማሪዎች በዚህ ሐሳብ ይለያያሉ። (2) ከማንኛውም አመለካከት ይበልጥ አስፈላጊ የሆነው የጌታችን ዳግመኛ መምጣቱና እግዚአብሔር በራሱ ጊዜ መንግሥቱን እንደሚፈጽም ያለው እርግጠኝነት ነው።
ለ. አከራካሪው የመከራ ጥያቄ ኢየሱስ ክርስቶስ ከታላቁ መከራ በፊት ሕዝቡን ከዓለም እንደሚያስወግድ (ቅድመ መከራ ተብሎ ይጠራል) ወይም ኢየሱስ ከመከራ በኋላ (ድህረ መከራ) ተመልሶ እንደሚመጣ ወይም በታላቁ የመከራ ዘመን (መካከለኛው መከራ) መካከል ተመልሶ እንደሚመጣ የሚጠይቅ ነው። ።
1. የክርስቶስ ምጽአቱ ሁለት ደረጃዎች እንደሚኖሩት ፕሪትሪቢዩሊሽኒስቶች ይናገራሉ።
ሀ. አንደኛ ደረጃ የሚታየው በማቴዎስ 24 “ከታላቁ መከራ” በፊት ማለትም በምድር ላይ ወደር የለሽ ሽብርና የፍርድ ጊዜ በሚመጣው “በመነጠቅ” ወቅት በሕይወት ያሉ አማኞች በሚነሱት ትንሣኤ እና ክርስቲያኖች የተተረጎሙበት ወቅት ነው። (1) ዓለም በመከራው ጊዜ የእግዚአብሔርን ቁጣና ፍርድ ይቀበላል።
4
(2) ቤተ ክርስትያን ስለ ታማኝነቷ በሰማያት ተፈርዶላት አክሊልን ትቀበላለች።
ለ. ሁለተኛው ደረጃ በነዚህ 7 ዓመታት መጨረሻ ላይ ይከሰታል፣ ክርስቶስ በመከራው ጊዜ ከሞቱት ቅዱሳን ትንሣኤ ጋር ይመጣል።
ሐ. የዚህ አመለካከት ልብ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን ከታላቁ መከራ ለማዳን ያለው ሃሳብ ነው፣ 1ተሰ. 5.10.
2. የድህረ መከራ አራማጆች ክርስቶስ ለህዝቡ የሚመጣው በመከራው መጨረሻ ላይ እንደሆነ ያምናሉ።
ሀ. የክርስቶስን መምጣት ማንኛውንም ዓይነት “መነጠቅ” አይቀበሉም።
Made with FlippingBook - Share PDF online