The Kingdom of God, Amharic Student Workbook
የእግዚአብሔር መንግሥት የናዝሬቱ ኢየሱስ ከሰበካቸውና ካስተማራቸው ትምህርቶች ሁሉ፣ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ርዕሰ ጉዳይ ያስተማረውን ያህል ጉልህና አከራካሪ ጉዳይ የለም። ወግ አጥባቂዎቹም ሆኑ ሊበራል ሊቃውንት የኢየሱስ ተወዳጅ ርዕሰ ጉዳይና በብዛትም የሰበከው እና ያስተማረው ስለ እግዚአብሔር መንግሥት እንደሆነ ይስማማሉ። ይህ የድነት መልእክቱ፣ ማስተር ፕላኑ እና የሥነ-መለኮቱ ልብ ነበር። በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ዘመናዊቷ ቤተክርስቲያን ኢየሱስ በትንቢታዊ እና በመሲሐዊ አገልግሎቱ ውስጥ በጣም አስፈላጊ ነው ብሎ ለሚጠራው ነገር ብዙም ትኩረት የሰጠች አይመስልም። እንግዲህ ተስፋችን ልብህ በመንግሥቱ ታሪክ - በንጉሡ እና በመንግሥቱ - እንደሚያዝና በግል ደቀ መዝሙርነት እና አገልግሎት ህይወትህ ውስጥ ያለውን ጠቀሜታ እንደምትመለከት ነው። በአራት ትምህርቶች፣ ይህ ሞጁል የእግዚአብሔር ፍፁም ሉዓላዊነት እና ጌትነት እንዴት በዲያብሎስና በመጀመሪያዎቹ ሰዎች እንደተጣሰ እና በኢየሱስ ክርስቶስ እና በሥጋ መገለጡ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥረታ አስመልክቶ በወፍ በረር እይታን ይሰጣል። አሁን ጌታችን ኢየሱስ ሞቶ፣ ተነሥቷል፣ ወደ ሰማይም አርጓል፣ የእግዚአብሔር መንግሥት በቤተክርስቲያን በዓለም ሁሉ እየተሰበከ ነው። የእግዚአብሔር መንግሥት በቅርቡ በኢየሱስ ዳግም ምጽዓት ይጠናቀቃል፣ ሞት፣ በሽታ እና ክፋት ሁሉ የሚወገዱበት፣ ሰማይና ምድር የሚታደሱበት፣ እና እግዚአብሔር ሁሉን የሚገዛበት ይሆናል።
ቄስ ዶ/ር ዶን ዴቪስ ፣ (ፒኤችዲ፥ አዮዋ ዩኒቨርሲቲ) የዎርልድ ኢምፓክት አገልግሎት አካል የሆነው የኧርባን ሚኒስትሪ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ናቸው። እንዲሁም የዎርልድ ኢምፓክት ከፍተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ያገለግላሉ።
TUMI በዓለም ዙሪያ ቤተክርስቲያን የመትከል እንቅስቃሴዎችን በማመቻቸት መንግሥቱን በከተማ ድሆች መካከል ለማስፋፋት መሪዎችን በማስታጠቅ የሚያገለግል አገልግሎት ነው።
ዎርልድ ኢምፓክት የአሜሪካን የከተማ ድሆችን በወንጌል በማስታጠቅ ፣ በማስታጠቅ እና በማጎልበት የቤተክርስቲያን ተከላ እንቅስቃሴዎችን ለማመቻቸት የቆረጠ የክርስቲያን የሚሽን ተቋም ነው። የእኛ ራዕይ አብያተ ክርስቲያናትን የሚተክሉ እና አገር በቀል የቤተክርስቲያን ተከላ እንቅስቃሴዎችን የሚጀምሩ የከተማ መሪዎችን መመልመል ፣ ማስታጠቅ እና ማሰማራት ነው።
መሪዎችን ማስታጠቅ የማስታጠቅ እንቅስቃሴዎች
THE URBAN MINISTRY INSTITUTE • A MINISTRY OF WORLD IMPACT, INC.
Made with FlippingBook - Share PDF online