The Kingdom of God, Amharic Student Workbook

1 1 6 /

የ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር መ ን ግ ስ ት

2. እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እንደ እርሱ እንሆናለን 1ኛ ዮሐ 3፡2።

ለ. የመንግሥቱ ፍጻሜ በኢየሱስ ክርስቶስ እግር ሥር የሚጠፋውና የሚደመሰሰውን ክፋት ሁሉ ያስወግዳል።

1. ፍጥረት ሁሉ ወደ ኤደናዊ ክብሩ ይመለሳል፣ ኢሳ. 11፡1-9።

2. መከራዎች፣ ክፋት፣ ጭንቀት፣ እና ኃጢአት ሁሉ ይወገዳሉ፣ ውጤታቸውም ጭምር ለዘላለም፣ ራዕ. 21፡4።

3. የፈተናና የክፋት ምንጭ እንኳ ለዘላለም ይሻራል፣ ራዕ 20፡10።

ሐ. የመንግሥቱ ፍጻሜ የተዋጁትን፣ ለእግዚአብሔር ብቻ የሆኑትን፣ ለእግዚአብሔር እና ለበጉ አምልኮ እና አገልግሎት የተጠሩትን የጌታ ብቸኛ ርስት ያደርጋቸዋል።

4

1. በአዲሲቷ ኢየሩሳሌም፣ የእግዚአብሔር ከተማ ወደ ሰው ልጆች ወረደ፣ ራዕ. 21.1-4.

2. በራዕ 19፡1-4 ላይ እንደሚታየው ዳግም የተፈጠረችው ምድር በጌታና በበጉ አምልኮ የተሞላች ትሆናለች።

3. የእግዚአብሔር ቅዱሳን ለዘላለም እርሱን እንዲያገለግሉ እንደ በረከታቸው ይቆጥሩታል፣ ራዕ.22፡3።

4. የእግዚአብሔር ሕዝቦች ፍትሕና ሰላም ለዘላለም በሚገዙባት በተዋጀች ምድር፣ በማይሞት አካል ውስጥ ሆነው ለዘላለም እሱን ያገለግላሉ።

መ. የመንግሥቱ ፍጻሜ፣ ሞትን ጨምሮ ጠላቶች ሁሉ በክርስቶስ እግር ሥር ከተደረጉ በኋላ ክርስቶስ መንግሥቱን ለአምላክ ያስተላልፋል፤ እርሱም የአጽናፈ ዓለሙ ሁሉን ቻይ ይሆናል።

Made with FlippingBook - Share PDF online