The Kingdom of God, Amharic Student Workbook
5 8 /
የ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር መ ን ግ ስ ት
* ኢየሱስ በሆነ መንገድ የእግዚአብሔርን መንግሥት ከገለጠ ለምንድን ነው ጥቂት ክርስቲያኖችና አብያተ ክርስቲያናት ብቻ የእግዚአብሔር ልን አገዛዝ ሥልጣንና ኃይል የሚለማመዱት? * በፍጻሜው ዘመን ትንቢት እና አስተምህሮ ላይ ክርስቲያኖች ብዙ አይስማሙም። ይህ የመንግሥቱ ትምህርት በመጨረሻው ዘመን የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርት ለመረዳት የሚረዳው ወይም ይበልጥ አስቸጋሪ የሚያደርገው እንዴት ነው? የድል አድራጊነት ጉዞ አንድ ቅን ክርስቲያን ወንድም፣ የእግዚአብሔር መንግሥት አሁን ናት የሚለውን ትምህርት ከሰማ በኋላ፣ የመንግሥቱ ኃይልና በረከቶች ሁሉ ዛሬ ለእኛ እንደሚገኙ ያመላክታል በሚል ወስዶታል። ወዲያው በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ኢየሱስ በመንግሥቱ ውስጥ ሁሉን እንደሰራልን ያስተምር ጀመር፣ ስለዚህም ከአሁን በኋላ የትኛውንም የዲያብሎስ ጣልቃ ገብነት ወይም መጠላለፍ ልንለማመድ አይገባም ይላል። በተለይም በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ታዳጊ ወጣቶችን ከእንግዲህ ወዲህ መታመም ወይም ገንዘብ ማጣት እንደሌለባቸው ወይም ኃጢአት መስራትና ተስፋ መቁረጥም ተቀባይነት እንደሌላቸው ማስተማር ጀመረ። በዚህ ትምህርት ምክንያት በወጣቶቹም ሆነ በወላጆቻቸው ዘንድ መከፋፈል ተፈጠረ። አንዳንዶቹ ከዚህ ክርስቲያን ወንድም ጎን ሲቆሙ ሌሎች ደግሞ “በዓለም ውስጥ ሳለን መከራ ይደርስብናል” ሲሉ ተከራክረዋል። ሁለቱም ወገኖች ከመጽሐፍ ቅዱስ የየራሳቸውን ነጥብ የሚደግፉላቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎችን ለማቅረብ ሞክረዋል። በዚህ ዓለም ውስጥ ከሥጋ፣ ከዲያብሎስና ከዚህ ክፉ የፈተና ሥርዓት ጋር በመታገል ላይ በክርስቶስ በኩል ድል እንዳለን ሞግተዋል። በመሆኑም ሁለቱም ወገኖች በመጠኑ ግራ በመጋባት፣ መጥተው “የተፈጸመ/ገና” በተባለው መንግሥት ውስጥ ያለውን “የተፈጸመው”ን ትርጉም እንድታብራራ ጠየቁህ እንበል። ይህ ኅብረት የእግዚአብሔርን መንግሥት በተመለከተ “የተፈጸመው” እና “ገና” የተባለውን ትክክለኛ ትርጉም እንዲረዳ እንዴት መርዳት ትችላለህ? ሁሉም ነገር ለበኋላ ነው የዚህን ትምህርት አስተምህሮ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ካሉ አንዳንድ ጓደኞቹ ጋር በማካፈል፣ የአንድ ታዋቂ ሴሚናሪ ተመራቂ ተማሪ ይህ አመለካከት እንዴት ኑፋቄ እንደሆነ መናገር ይጀምራል። ተመራቂው የመንግሥቱ ሕይወትና ሥልጣን ሁሉ ወደ ፊት ዘመን መተላለፉን አጥብቆ በማመን፣ እስራኤል እንዴት የመንግሥቱን ስጦታ እንዳልተቀበለችውና ወደ መንግስቱ የጋበዛትን መሲሕ መግደሏን ያነሳል። የኢየሱስን መንግሥት ስጦታ ባለመቀበል፣ አሁን ያለነው በኢየሱስ የመንግሥቱ ጥሪ ጊዜ እና በዳግም ምጽአቱ ጊዜ መካከል በሚገኝ የቤተክርስቲያን ዘመን ውስጥ ነው ብሏል።። በክርስቶስ ዳግም ምጽአት እስራኤል የእግዚአብሔርን መንግሥት ጥሪ ትቀበላለች፣ የዳዊትም መንግሥት ለወደፊቱ ይዘጋጃል ብሎ ይሟገታል። አሁን፣ ምንም ዓይነት የመንግሥቱ መገለጫ የለም፣ ከመንግሥቱ ጋር የተያያዘው ሁሉ ለኋለኛው ነው። ለዚህ ተማሪ ምን ትላለህ? የእሱ አመለካከት እምነት የሚጣልበት ይመስላል? በዛሬው ክፍለ ጊዜ ከተማርከው አንጻር እንዲህ ያለውን ትርጉም እንዴት ትመልሳለህ?
ጥናቶች
1
2
2
Made with FlippingBook - Share PDF online