The Kingdom of God, Amharic Student Workbook
/ 7 9
የ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር መ ን ግ ስ ት
እነዚህ ጥያቄዎች ቤተክርስቲያንን በአለም ላይ የመንግስቱ ህይወት እና ህልውና ወኪል እውነት ለመገምገም እና ለመወያየት እንዲረዷችሁ የተነደፉ ናቸው። እነዚህን እና ሌሎች ቪዲዮው ያነሳቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ አስፈላጊውን ያህል ጊዜ ውሰድ። እባክህ መልሶችህ ግልጽ እና አጭር ይሁኑ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ በቅዱሳት መጻሕፍት አስደግፍ! 1. “ወኪል” የሚለው ቃል ምን ማለት ነው? ቤተክርስቲያን ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ በማምለክ የእግዚአብሔር መንግሥት ወኪል ሆና የምትሠራው እንዴት ነው? 2. ለምንድነው አምልኮ ለቤተክርስቲያን በዓለም ላይ ላለችበት ማንነት እና ሃላፊነት ወሳኝ የሆነው? ቤተክርስቲያን እንደ እግዚአብሔር አምላኪ ሳትሳካ በዓለም ላይ ያላትን ተግባር መወጣት ትችላለች? ለምን? 3. ቤተክርስቲያን በ”ሐዋርያዊ ምስክርነት” የእግዚአብሔር ወኪል እንድትሆን የተጠራችበት ሁለቱ መንገዶች ምንድናቸው? በዓለም ላይ ያለች ቤተክርስቲያን ስለ ክርስቶስ የሐዋርያትን ትምህርት እና አስተምህሮ እንድትጠብቅ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው? 4. ቤተክርስቲያን የሐዋርያዊ ምስክር ጠባቂ ሆና ማገልገል እና ያንን ምስክርነት ለጠፉት በማካፈል መካከል ያለው ግንኙነት ምንድን ነው? ቤተክርስቲያን ሁለቱንም ሳታደርግ የምሥክርነት ጥሪዋን መፈጸም ትችላለች? ለምን? 5. ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚሉት፣ ቤተ ክርስቲያን ለበጎ ሥራ እንድትጠብቅና እንድትቀና ለምን አስፈለገ? በዓለም ላይ መንግሥቱን መግለጥን እና መልካም ሥራን ምን ያገናኛቸዋል? 6. ድሆችን እና የተጨቆኑ ሰዎችን ማገልገል በቤተ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ልዩ ቦታ አለው - ለምን? አንድ ጉባኤ ለድሆች ፍትሕና ርኅራኄ ካላሳየ ይህ ቸልተኛነት ስለ መንግሥቱ ምሥክርነት ለመስጠት ስላለው አቅም ምን ይላል? 7. መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት በመግለጥ ውስጥ ያከናወናቸው ሥራዎች በቤተክርስቲያን ሕይወትና ተግባራት ውስጥ እንደሚቀጥሉ የሚያረጋግጥልን ከምን አንጻር ነው? 8. መንፈስ ቅዱስ ዛሬ በቤተክርስቲያን አገልግሎት የእግዚአብሔርን ቃል አግባብነትና ሃይል በማረጋገጥ ላይ የሚሰራው እንዴት ነው? ወንጌልን ወደ አለም ይዘን ስንሄድ መንፈስ ቅዱስ በክርስቶስ የትንሳኤ ሃይል እንደሚሰራ ማረጋገጫችን ምን መሆን አለበት?
መሸጋግገሪያ 2
የተማሪው ጥያቄዎች እና ምላሾች
3
Made with FlippingBook - Share PDF online