The Kingdom of God, Amharic Student Workbook
/ 9 3
የ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር መ ን ግ ስ ት
ለ. አማኞች፣ በመንግሥቱ ፍጻሜ ምክንያት፣ የእግዚአብሔር መንግሥት በምድር ላይ በኃይል እንደሚመለስ ተስፋ እንደሌላቸው የጠፉ ሰዎች እንደሚያዝኑ ማዘን አያስፈልጋቸውም።
በዚህ ዘመን አማኞች በሥጋ ቢሞቱም፣ ጌታ በራሱ ጊዜና መንገድ፣ ፍጹምና ፍትሐዊ በሆነበት አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር፣ ንጉሥ ሆኖ ለዘላለም እንደሚነግሥ የተነገረውን ትንቢታዊና ሐዋርያዊ ቃል ኪዳን እንደሚፈጽም ተስፋችን ሙሉና እርግጥ ነው።
ሐ. ጳውሎስ ለተሰሎንቄ ሰዎች የኢየሱስን የዳግምምጽዓት እውነቶች አስተምሯቸዋል፣ ከዚያም በእነዚያ ቃላት እርስ በርሳቸው እንዲፅናኑ ይጠቁማል፣ 1 ተሰ. 4.18.
2. በኢየሱስ ክርስቶስ በቅርቡ መገለጥ ምክንያት ምንጊዜም ንቁ፣ በመጠን እና ጥንቁቅ እንድንሆን ለማበረታታት
ሀ. ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲመለከቱት እና ለመገለጡ እንዲዘጋጁ የተናገረው የማያቋርጥ ቃል፣ ሉቃስ 12፡35-40
ለ. ጳውሎስ በሮሜ 13፡11-12 የፍጻሜው ዘመን ፈጥኖ እንደሚመጣ ይጠቁማል፤ በመጠን እና በንቃት እንድንኖር በመጠቆም።
4
ሐ. በተጨማሪም፣ ጳውሎስ የብርሃን ልጆች እንደመሆኖ ለተሰሎንቄ ሰዎች በመጠን ይኑሩ፣ ለመምጣቱም ንቁዎች እንዲሆኑ ሰበከላቸው፣ 1ኛ ተሰ. 5.6-9.
መ. ጴጥሮስ በትንሿ እስያ ስደት ለነበሩት ክርስቲያኖች በመጠን ይኑሩ እና በኢየሱስ መገለጥ በሚመጣው ጸጋ ላይ ሙሉ በሙሉ ተስፋቸውን እንዲያሳርፉ ነገራቸው፣ 1 ጴጥ. 1.13.
ሠ. ጴጥሮስ የነገር ሁሉ ፍጻሜ ቅርብ ስለሆነ በመጠን እና ንቁ የመሆንን አስፈላጊነት በድጋሚ ተናግሯል፣ 1 ጴጥ. 4:7
Made with FlippingBook - Share PDF online