Theology of the Church, Amharic Mentor Guide
1 2 0 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ለ. 1 ተሰ. 5፡12-13
4. በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስልመከፋፈል፤ ስለመናፍቅነት፣ እና ከሥነ ምግባር ብልግና ጋር በተያያዘ ምን ለማለት ይቻላል? እነዚህም በጉባኤው ውስጥ በጥንቃቄ እና በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት መስተናገድ አለባቸው።
ሀ. 1 ቆሮ. 5
የተሐድሶው ምልክቶች ቅዱሳት መጻሕፍትን ይይዛሉ፡- ቃሉ በትክክል የሚሰበክበት፣ የቤተክርስቲያን ስነ-ሥርዓት በትክክል የሚፈጸምባት፣ እና ተግሣጽ በትክክል የታዘዘባት እውነተኛ ቤተ ክርስቲያን ትኖራለች።
ለ. 1ኛ ዮሐንስ 2፡19
ሐ. ማቴ. 18
መ. ገላ. 6.1-3
III. ወግ እና እምነትን ወይም የቪንሴንቲያን ህግን በተመለከተ ምልክቶች - “በሁሉም ቦታ, ሁልጊዜ እና በሁሉም የሚታመን” የቪንሴንቲያን ህግ አንዳንድ ትምህርቶች ወይም ልምምድ ከእውነተኛዋ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን “ታላቅ ወግ” ትምህርት ጋር መስማማታቸውን ለማወቅ የምንችልበትን መንገድ ይሰጠናል።
4
ከ 450 ዓ.ም በፊት የሞተው የሌሪን ቅዱስ ቪንሰንት ፣ “የቪንሴንቲያን ቀኖና፣ የካቶሊካዊነት የሶስት ጊዜ ፈተና፡ quod ubique፣ quod semper፣ quod ab omnibus creditum est (ተብሎ በሚጠራው በዚህ መስፈርት ጥሩ ፍቺ አስቀምጧል። (በሁሉም ቦታ, ሁልጊዜ እና በሁሉም የሚታመን)። በዚህ የሶስት ጊዜ የክርስትያኖች ውህደት፣ ጥንታዊነት እና ስምምነት ፈተና፣ ቤተክርስቲያን በእውነተኛ እና በሐሰት ወጎች መካከል መለየት ትችላለች። ~ Thomas C. Oden. Classical Pastoral Care . Vol. 4. Grand Rapids: Baker Books, 1987. p. 243.
ሀ. ደንቡ ለእውነተኛ ትውፊት መሰረቱ “በሁሉም ቦታ የታመነ” መሆኑን ያረጋግጣል።
1. ይህ የክርስትያኖች ውህደት መመዘኛ ነው (ማለትም፣ በሁሉም ቦታ የሚታመን)፡ ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ማንነት ላይ የተመሰረተ አዋጅ በታሪክ የያዘች የእምነት ማህበረሰብ ናት።
2. የክርስትና እምነት በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት እና ጌትነት ፤ ስራ እንዲሁም አካል ላይ የተመሰረተ ነው፥ እናም ይህ መልህቅ ከመጀመሪያ ጀምሮ በሁሉም ክርስቲያኖች ዘንድ ይታመናል።
Made with FlippingBook Ebook Creator