Theology of the Church, Amharic Mentor Guide
/ 1 2 1
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ለ. በመቀጠል ህጉ መስፈርቱን ያሰፋዋል በዚህም “ሁልጊዜ በሁሉም ቦታ የሚታመን” የሚለውን ይጨምራል።
1. ይህ የጥንታዊነት መመዘኛ ነው (ማለትም፣ ከመጀመሪያው ያለው)፡ ቤተክርስቲያን ከሐዋርያት ትውልድ ጀምሮ በኢየሱስ ላይ የተመሰረተውን ይህን የኑዛዜ እውነት አስኳል ይዛለች።
2. አስፈላጊው ማእከላዊ ሃሳብ ከመጀመሪያው ጀምሮ ሁል ጊዜ የተመሰከረ ነው፡ በክርስቶስ ያለው የእግዚአብሔር ማዳን ሁሉም የክርስትና እምነት እና ልምምድ የታነጹበት መሰረት ነው።
ሐ. በመጨረሻም፣ ደንቡ መርሆቹን “በሁሉም ቦታ፣ ሁልጊዜ እና በሁሉም ዘንድ የታመነውን” በማለት ያጠቃልላል።
1. ይህ የስምምነት መለኪያ ነው፡ ሁሉም የቤተክርስቲያኑ ቅርንጫፎች ከዚህ የእውነትን አዋጅ ጋር ተያይዘዋል።
4
2. አስፈላጊው ማእከላዊ ሃሳብ ሁል ጊዜ በሁሉም ዘንድ የተመሰከረ ነው፦ መናፍቅነት፣ በትርጉም፣ “ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ለዘለዓለም የተሰጠ” የሚለውን ትርጉም የሚያድስ ወይም የሚቀይር ነው፣ ይሁዳ 3.
በዚህ አስደናቂ ቀላል መግለጫ የክርስትና እምነትን በተመለከተ እውነተኛውን ትምህርት ከሐሰተኛው ትምህርት የምንለይበት የተወሰነ እና አስተማማኝ መመሪያ አለን። “በሁሉም ቦታ፣ ሁል ጊዜ እና በሁሉም ዘንድ የታመነው” የመሆን ፈተናን ማለፍ ከቻለ አንድ ትምህርት ስልጣን ያለው እና በቤተክርስቲያን ላይ አስገዳጅ እንደሆነ ልንቆጥረው እንችላለን።
Made with FlippingBook Ebook Creator