Theology of the Church, Amharic Mentor Guide
/ 3 3
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
3. በዘፀአት መዳን ማለት ምን ማለት ነው?
4. በአዲስ ኪዳን መዳን ማለት ምን ማለት ነው?
ሀ. ሮሜ. 8.20-25
ለ. 2 ጴጥ. 3.13
1
ማጠቃለያ
» ድነት ማለት ከክርስቶስ ጋር አንድ በመሆን ኃጢአት ካስከተለው ጥፋትና መለያየት መዳን ማለት ነው ይህም እርሱ ቃል የገባላቸውን መንግሥት ከሚወርሱት ‘የእግዚአብሔር ሕዝብ’ ጋር መቀላቀል ማለት ነው። » ይህ መዳን ሁልጊዜ ኃጢአት ከሚያስከትለው የእግዚአብሔር ፍርድ መዳንን እና ኃጢአት በሰው ሕይወት ውስጥ ከሚያመጣው እስራት ነፃ መውጣትን ያካትታል። » መዳን እና ቤተክርስቲያን በእውነት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው ምክንያቱም መዳን ማለት በትርጉሙ የእግዚአብሔር ህዝብ አካል መሆን ማለት ነው። ግለሰቦች መዳንን ይለማመዳሉ ነገር ግን ማንም በራሱ የዳነ የለም። ከክርስቶስ ጋር አንድ መሆን ሁልጊዜም ከሕዝቡ ጋር አንድ መሆንን ይጨምራል። » ቤተ ክርስቲያን አዲሶቹ የሰው ልጆች በአዲስ ሰማይ እና አዲስ ምድር ውስጥ በእግዚአብሔር አገዛዝ ሥር የሚያመጡት ተጽዕኖ ትልቅ የእግዚአብሔር ታሪክ አካል ነች ይህም በዓለም ላይ የኃጢአትና የሞትን መዘዝ ሙሉ በሙሉ የሚቀይር ነው። » ሰዎች እንዲድኑ ጥሪ ማድረግ በኢየሱስ በማመን እርሱ በሚገዛበት በዚህ አዲስ ዓለም ውስጥ እንዲሳተፉ መጋበዝ ማለት ነው።
Made with FlippingBook Ebook Creator