Theology of the Church, Amharic Mentor Guide
3 4 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
የሚከተሉት ጥያቄዎች የተነደፉት በሁለተኛው የቪዲዮ ክፍል ውስጥ የሚገኘውን የመዳንን ትርጉም እንዲከልሱ ለመርዳት ነው። ለጥያቄዎቹ መልስ ስትሰጥ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ “መዳን” ሲናገር ምን ማለት እንደሆነ ግልጽ በሚያደርጉ ሐሳቦች ላይ አተኩር። አስታውስ እነዚህ ጥያቄዎች ኢየሱስ እንዴት ድነትን እንዳከናወነ ወይም ሰዎች እንዴት እንደዳኑ ለመግለጽ እየሞከሩ እንዳልሆነ (እነዚህ ሃሳቦች በሌሎች የካፕስቶን ሞጁሎች ውስጥ ይብራራሉ) ይልቁንም መዳን ምን እንደሆነ ግልጽ እንዲሆንልን ይረዱናል። መልሶችህ ግልጽ እና አጭር ይሁኑ፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ በቅዱሳት መጻሕፍት አስደግፍ! 1. የሰው ልጆች መዳን ያለባቸው ሦስቱ የኃጢአት ውጤቶች ምንድን ናቸው? 2. በሉቃስ 15 ላይ ኢየሱስ ስለጠፉ ነገሮች የተናገራቸው ምሳሌዎች ስለ ድነት ምን ያስተምሩናል? 3. የመዳን ቁልፉ ‘ከክርስቶስ ጋር ኅብረት’ የሆነው ለምንድን ነው? 4. መዳን ሁል ጊዜ በቤተክርስቲያን ውስጥ መካተትን እንደሚጨምር መረዳት ለምን አስፈለገ? 5. ለምንድነው አንድ ክርስቲያን አማኝ “ድኛለሁ” እና “እድናለሁ” የሚለው እናስ እንዴት ነው ሁለቱም አባባሎች እኩል እውነት መሆናቸውን የሚያውቀው? ይህ ትምህርት የሚያተኩረው እግዚአብሔር ለዘላለም የእርሱ የሆኑትን ሕዝቦች ከምድር ላይ ለመቤዠት ባዘጋጀው ሉዓላዊ ንድፍ ላይ ነው። ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔር ለአብርሃም በገባው ቃል ኪዳን፣ አሁን ስለ አሕዛብ በተገለጠው ምሥጢር፣ እና በእስራኤል ሕዝብ ምሳሌ ትታያለች። እግዚአብሔር ህዝቡን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ከራሱ ጋር አንድ አድርጎ ለራሱ ክብር ሲል አዳነ። በግል መዳን ማለት በእምነት ከክርስቶስ ጋር እና በእርሱም ከተዋጀው ማህበረሰቡ ጋር አንድ መሆን ማለት ነው። ³ የእግዚአብሔር ከፍ ያለው ዓላማ፣ የመጨረሻ ሐሳቡ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት አማካኝነት በፍጥረቱ እና በሕዝቡ በኩል ለራሱ ክብር እና ሞገስን ማምጣት ነው። ሁሉ በእርሱ ፈቃድና ለክብሩ ሆነዋል። ³ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በእግዚአብሔር የላቀ ዓላማ ውስጥ ተጠልላለች። እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ ለራሱ ክብርን ለማምጣት ከአህዛብ መካከል ለዘላለም የእርሱ የሆኑትን ሕዝቦች በመቤዠት ወስኗል። ይህንንም ከአብርሃም ጋር በገባው ቃል ኪዳን ፈጽሟል። ³ ቤተክርስቲያን አህዛብ በክርስቶስ ኢየሱስ በሚካተቱበት ታላቁ ምስጢር መገለጥ ጥላ ውስጥ ነበረች። እግዚአብሔር በልጁ በማመን አሕዛብን ለማዳን በእርሱ ቤተሰብ ውስጥ ለዘላለም እንዲካተቱ በሐዋርያት እና በነቢያት በኩል ለዚህ ትውልድ እና ለአለቆችና ለሥልጣናት አሳውቋል።
መሸጋገሪያ 2
የተማሪው ጥያቄዎች እና ምላሾች
1
ግንኙነት
የቁልፍ ፅንሰ ሀሳቦች ማጠቃለያ
ገጽ 205 15
Made with FlippingBook Ebook Creator