Theology of the Church, Amharic Mentor Guide
3 6 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
* አንድ የቤተ ክርስቲያን መሪ ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር ሕዝቦች መካከል ራሱን ለማክበር በእግዚአብሔር የላቀ ዓላማ ጥላ ስር እንደምትገኝ መረዳቱ እና ማስረዳት መቻሉ ለምን ጠቃሚ ይሆናል? አንተ ያለህበት አጥቢያ ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ለዘላለም የሚኖርን አዲስ የሰው ዘር ለመፍጠር ካለው ፍላጎት ጋር ያለው ዝምድና ምንድን ነው? * እግዚአብሔር ዓለምን ሁሉ ለመቤዠት ባለው ዓላማ ውስጥ አሕዛብን ለማካትት ስላለው ሐሳብ አንዳንድ ተግባራዊ አንድምታዎች ምንድን ናቸው? እግዚአብሔር በአካባቢህ ያሉ አጥቢያ አብያተክርስቲያናት ግልጽ እና ከጭፍን ጥላቻና ከአድልዎ ነፃ እንዲሆኑ ስላለው ዓላማ ምን ይላል? * በክርስቶስ የሚያምኑት ሁሉ ሕዝቡ ከሆኑ፣ ከሁሉም ታናሽ የሆነችውንና ኢየሱስ የሚመለክባትና የሚከበርባትን ትንሿን የአማኞች ስብስብ የሆነችውን ቤተክርስቲያን እንኳን እንዴት ልንመለከት ይገባናል? ትናንሽ የሆኑት የከተማ አብያተ ክርስቲያናት እግዚአብሔር የራሱ የተለየ ሕዝብ አድርጎ ለራሱ እንደሚያስነሣው ቃል የገባለትን ሕዝብ (ላኦስ) አካል ነን ብለው እንዴት ሊናገሩ ይችላሉ? * በእግዚአብሔር ሕዝቦች መካከል ያሉ አንዳንድ ቡድኖች ከሌሎቹ የበለጠ ክብደትና ክብር የተሸከሙ የሚመስሉት ለምንድን ነው? በክርስቲያን ቡድኖች መካከል ያለው ይህ የተለመደ ዝንባሌ እግዚአብሔር ከምድር አህዛብ ሁሉ ለራሱ የሚሆንን ሕዝብ ለማውጣት እየሠራ ያለውን ሐሳብ የሚቃረነው እንዴት ነው? * በአንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለ መሪ እግዚአብሔር ለብዙ ዘመናት ሕዝቡን በአንድነት ለመሰብሰብ ሲሠራ እንደነበረ መገንዘቡ አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድነው? ጠላት ለአንድ ተስፋ ለቆረጠመሪ ቤተክርስቲያንን ለመገንባት የሚያደርገው ጥረት መቼም እንደማይሳካለት ምን አይነት ውሸት ሊነግረው ይችላል? * ለአንድ የከተማ አገልጋይ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሥነ ምግባር ጥሰት፣ ከጣዖት አምልኮ እና ከኃጢአት ጋር ለተያያዙት ለአህዛብም ቢሆን ቤተክርስቲያንን ለሁሉም ሰው ማድረግ የእግዚአብሔር ጥልቅ ፍላጎት መሆኑን መረዳቱ ለምን አስፈላጊ ሊሆን ይችላል? ይህ ዛሬም ለዚህ ማህረሰብ ውጭ ስላሉት ሰዎች ምን ሊጠቁም ይችላል? * ለአንድ የተሰጠ ክርስቲያን ሠራተኛ እግዚአብሔር ሕዝቡን በአንድ ላይ የማሰባሰብ ዓላማ እንዳለው ማረጋገጥ ለምን አስፈላጊ ይሆናል? ለክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ለማድረግ ከዚህ ያነሰ መሥራት አለብን ማለት ነው?
1
Made with FlippingBook Ebook Creator