Theology of the Church, Amharic Mentor Guide

/ 3 7

የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት

ጥናቶች

“እስራኤል ከአሁን በኋላ የእግዚአብሔር ሕዝብ አይደለም” በቅርብ ጊዜ በርካታ ሰዎች በሚካፈሉበት የአዋቂዎች የሰንበት ትምህርት ቤት በርካታ አባላት እስራኤል በእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ ስላላት ስፍራ ሞቅ ያለ ውይይት አድርገዋል። አንዳንዶች አይሁዳውያን በኢየሱስ ሞት ውስጥ እጃቸው ስላለበት እግዚአብሔር እንደ ሕዝቡ አድርጎ አይቀበላቸውም ብለው ይከራከሩ ነበር። ሌሎች ደግሞ እግዚአብሔር እስራኤልን እንደ ሕዝቡ አልተወም ነገር ግን በክርስቶስ ስላላመኑ ቀድሞ በእግዚአብሔር ፊት የነበራቸው አይነት ሞገስ እንደሌላቸው ይናገራሉ። ሌላው ቡድን ደግሞ ኢየሱስ በዳግም ምጽአት እስከሚመለስበት ወቅት ድረስ እስራኤላውያን የእግዚአብሔር ሕዝብ ሆነው እንደሚቀጥሉ ያምናሉ። አንድ ሌላ ቡድን ደግሞ ስለ እስራኤል ብዙ መጨነቅ እንደሌለብን በመግለጽ ጥያቄው እንኳን ያን ያህል አስፈላጊ እንዳልሆነ ያምናል፣ ዋናው ጉዳይ መሆን ያለበት ራሱ ክርስቶስ እና በእርሱ በማመን ስለሙገኘው ድነት ነው ብለው ያምናሉ። ይህ መምህር ለእርዳታ ወደ አንተ ቢመጣ ምን ትመክረዋለህ? “ቤተ ክርስቲያን ማን ያስፈልገዋል?” አንድ ጓደኛህ እግዚአብሔርን የሚወድ፣ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያነብ እና በመልካም ሥራ ሕይወት ለመኖር የሚጥር የተሰጠ ክርስቲያን ነኝ ብሎ ያምናል። ነገር ግን ይህ ግለሰብ ወደ ቤተ ክርስቲያን አይሄድም ወይም እራሱን በክርስቶስ አካል ውስጥ አያሳትፍም። ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲመጣ በጋበዝከው ጊዜ ሁሉ “ክርስቲያን ለመሆን የቤተክርስቲያን አባል መሆን ግድ ነው ብዬ አላምንም፣ እንዳውም እኔ በቤተክርስቲያን ሕንፃ ውስጥ ከማደርገው አምልኮ በተሻለ በውጭ በተፈጥሮ እግዚአብሔርን ማምለክ እመርጣለሁ” ይላል። ይህ ሰው ስለ ክርስትና ስላለው አመለካከት ምን ትላለህ? መላውን መጽሐፍ ቅዱስ መስበክ የዚህ ትምህርት ርዕስ “በእግዚአብሔር ጥላ ውስጥ ያለች ቤተ ክርስቲያን” የሚለው ሃሳብ በብሉይ ኪዳኑ የእግዚአብሔር ሕዝብና በቤተ ክርስቲያን መካከል ግንኙነት እንዳለ ይጠቁማል፣ ሐዋርያው ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮንቶስ 10፡1-11 የዳሰሰው ሐሳብ - “ወንድሞች ሆይ፥ ይህን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ። አባቶቻችን ሁሉ ከደመና በታች ነበሩ ሁሉም በባሕር መካከል ተሻገሩ፤ ሁሉም ሙሴን ይተባበሩ ዘንድ በደመናና በባሕር ተጠመቁ፤ ሁሉም ያን መንፈሳዊ መብል በሉ ሁሉም ያን መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤ ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ ዓለት ጠጥተዋልና፥ ያም ዓለት ክርስቶስ ነበረ። እግዚአብሔር ግን ከእነርሱ በሚበዙት ደስ አላለውም፥ በምድረ በዳ ወድቀዋልና። እነዚህም ክፉ ነገር እንደ ተመኙ እኛ ደግሞ እንዳንመኝ ይህ ምሳሌ ሆነልን። ሕዝብም ሊበሉ ሊጠጡም ተቀመጡ ሊዘፍኑም ተነሡ ተብሎ እንደ ተጻፈ ከእነርሱ አንዳንዶቹ እንዳደረጉት ጣዖትን የምታመልኩ አትሁኑ። ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንደ ሴሰኑ በአንድ ቀንም ሁለት እልፍ ከሦስት ሺህ እንደ ወደቁ አንሴስን። ከእነርሱም አንዳንዶቹ ጌታን እንደ ተፈታተኑት በእባቦቹም እንደ ጠፉ ጌታን አንፈታተን። ከእነርሱም አንዳንዶቹ

1

ገጽ 206  17

1

2

3

Made with FlippingBook Ebook Creator