Theology of the Church, Amharic Mentor Guide

4 6 /

የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት

ቅዳሴ በጣም አሰልቺ ነው - እግዚአብሔር እንዲደብረን ይፈልጋል? በእራት ሰአት ላይ አንድ የቤተ ክርስቲያን ቤተሰብ ልጆች ስለ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ያላቸውን አመለካከት አስተያየት ሰጥተዋል። እንደ የ13 ዓመቷ ልጅ አስተያየት ከሆነ የቤተክርስቲያኒቱ አገልግሎቶች በጣም መደበኛ፣ በጣም ተመሳሳይና ለእርሷ ምንም ትርጉም የሌላቸው ከባባድ ቋንቋና ተግባራት የሞሉበት ነው። መዝሙሮቹ ለምን የቆዩና እና ሙዚቃው ለምን የቀብር ሙዚቃ እንደሚመስል ትጠይቅ ነበር። በአጠቃላይ ያለው ድባብ የሃዘንና የተስፋ መቁረጥ ይመስላል፣ ለምንድን ነው ቅዳሴ በተወሰኑ ጊዜያት የሚዘመሩት፣ አንዳንዴም ለምን እንደሚቆሙና አንዳንዴም ለምን ማንበብ እንዳለባቸው አታውቅም። ሁሉም ነገር በጣም አሰልቺ እና ያለፈበት ይመስላል። ለምን ቤተ ክርስቲያን አስደሳች ሊሆን እንደማይችል ቤተሰቦቿን ጠየቀቻቸው፣ ለምሳሌ ልክ በቴሌቭዥን ላይ እንዳሉ የጨዋታ ትዕይንቶች፣ ወይም በአትሌቲክስ ዝግጅቶች ላይ እንዳለው አይነት ደስታ። “እግዚአብሔር እንዲደብረን ይፈልጋል?” ብላ ጠየቀች። የ13 ዓመቷን ልጅ በቤተክርስቲያኗ ስላላት የአምልኮ ልምምድ እና እግዚአብሔርን እንዴት በአንድነት ማምለክ እንዳለባት እንድትረዳ እና እንድታስተውል ምን ትመክራታለህ?

3

2

በአምልኮ ላይ ያለች ቤተ ክርስቲያን ክፍል 1

ይዘት

ቄስ ቴሪ ኮርኔት

የእግዚአብሔር ጸጋ ከየትኛውም የሰው ውሳኔ ወይም ጥረት በፊት ይመጣል - ሰዎች ለእርሱ ምላሽ እንዲሰጡ የሚያስችለው ጸጋው ብቻ ነው። በዚህ ጸጋ ምክንያት ነው ቤተክርስቲያኑ እግዚአብሔርን ማምለክ የምትችለው፣ ለዚህም ነው ሁሉም የቤተክርስቲያን አምልኮዎች በተለይም የጌታ እራት እና ጥምቀት የእግዚአብሔር ፀጋ ልምምድ እና ምስክር የሆኑት። የዚህ በአምልኮ ላይ ያለች ቤተክርስትያን የተሰኘው የመጀመሪያው ክፍል አላማችን የሚከተሉትን እንድታደርግ ማስቻል ነው:- • የጸጋን ፍቺ/ትርጓሜ መስጠት • ጸጋንና ምሕረትን መለየት • የፔላጊያን ኑፋቄ ለይተህ መልስ መስጠት • “ቅዱስ ቁርባን” በሚለው ቃል እና “ሥርዓት” በሚለው ቃል መካከል ያለውን ልዩነት መግለጽ • ስለ ጌታ እራት አራቱን ዋና ዋና ክርስቲያናዊ አመለካከቶች መግለጽ እና በአጭሩ ማብራራት

የሴግመንት 1 ማጠቃለያ

Made with FlippingBook Ebook Creator