Theology of the Church, Amharic Mentor Guide
4 8 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
መ. ያለን ሁሉ ሶላ ግራቲያ ነው፣ ሁሉም በጸጋ ብቻ ስንል ምን ማለታችን ነው?
1. በመጀመሪያ ደረጃ እስካሁን ድረስ የኖረው የሰው ልጅ ሁሉ በኃጢአት ቀንበር ተይዞ እና በፍጹም ተስፋ ቢስ ሁኔታ ነው ወደ ዓለም የመጣው ማለታችን ነው፣ ሮሜ. 3.10-12. የፔላጂያን ስህተት ወይም ኑፋቄ፣ አንድ ሰው ከኃጢአተኛ ተፈጥሮ ጋር እንዳልተወለደ እና ሰው በራሱ ፈቃድ ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔርን መፈለግ እና ማመን ይችላል የሚል እምነት ነው። ቤተክርስቲያንም የፔላጂያንን ስህተት አልተቀበለችም ስለዚህም አንድ ሰው ወደ እግዚአብሔር ሊመጣ የሚችለው የእግዚአብሔር ጸጋ አስቀድሞ በእርሱ ውስጥ ስለሚሠራ ብቻ እንደሆነ ከቅዱሳት መጻሕፍት ታስተምራለች። የሰው ጸሎት እንዲሰማ የእግዚአብሔር ጸጋ ነው ይህን የሚያደርገው እያለ ነገር ግን ወደ እግዚአብሔር እንድንጸልይ የሚያደርገን በራሱ ጸጋ አይደለም የሚል ሰው ካለ ነቢዩ ኢሳይያስን ወይም ሐዋርያው ዮሐንስን ይቃረናል። “ባልፈለጉኝ መሃል ተገኘሁ፣ ላልለመኑኝም ራሴን አሳየኋቸው።”... የቀደመው ሰው ኃጢአት ነጻ ፈቃድን ስለጎዳ ከዚያ በኋላ ማንም ሰው የመለኮታዊ ምሕረት ጸጋ ከእርሱ ፊት ካልቀደመው በቀር እግዚአብሔርን እንደሚገባው መውደድ ወይም በእግዚአብሔር ማመን ወይም ለእግዚአብሔር ሲል መልካምን ማድረግ አይችልም።
ገጽ 212 7
2
~ The Council of Orange (529 A.D).
2. በሁለተኛ ደረጃ፣ መዳን የሚገኘው በእምነት ብቻ ስለሆነ በማንም ፈጽሞ ሊገኝ አይችልም ማለታችን ነው። መዳንን እንደ ነጻ ስጦታ ብቻ መቀበል ይቻላል፣ ለመልካም ስራዎቻችን ተገብቶን የምናገኘው አይደለም። መዳን ሙሉ በሙሉ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ነው።
ገጽ 212 8
ሀ. ኤፌ. 2.8-9
ለ. የሐዋ ሥራ 20፡24
Made with FlippingBook Ebook Creator