Theology of the Church, Amharic Mentor Guide
/ 5 5
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
መ. የጌታ እራት መወሰድ ያለበት በንስሃ እና በእምነት ነው።
1. የፕሮቴስታንት ተሐድሶ አራማጆች በመጀመሪያ ከካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት እንዲለያዩ ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ ምሥጢረ ቁርባን በእምነት እንደሚወሰድ የእግዚአብሔር ጸጋ ሳይሆን እንደ ምትሃታዊ ተግባር በመታየታቸው ነው።
ገጽ 214 16
2. የጌታ እራት በድርጊቱ ውስጥ በመሳተፍ ብቻ ጸጋ እንዲሰጥ የሚያደርግ ምትሃታዊ ስርዓት አይደለም።
የቀድሞዎቹ የፕሮቴስታንት ተሐድሶ አራማጆች ኤክስ ኦፔሬ ኦፔራቶ በመባል የሚታወቀውን የካቶሊክ አስተምህሮ ተቃውመዋል። (ይህ የላቲን ሐረግ ሲሆን ትርጉሙም “ድርጊቱ በመፈጸሙ እውነታ” ማለት ነው። የተሐድሶ አራማጆች ይህ ሰዎች ቅዱስ ቁርባንን እንደ አስማት እንዲመለከቱ ያደረጋቸው መሆኑን ተቃውመዋል፡ መጠመቅ ወይም የጌታን እራት መውሰድ በራሱ ክርስቲያኖች እንድትሆኑ አድርጓችኋል የሚለውን አስተምህሮ ማለት ነው። ምላሻቸው አንድ ሰው ክርስቲያን ሆኖ እንደ ክርስቲያን የሚያድገው “በእምነት ብቻ” ነው የሚል ነበር። ካቶሊኮች ኤክስ ኦፔራቶን ማስተማራቸውን ቀጥለዋል ነገር ግን ቅዱስ ቁርባንን በእምነት መቀበል የፕሮቴስታንት ሃሳብ ብቻ ሳይሆን ለካቶሊክ አመለካከት አስፈላጊ መሆኑን በመቀበል የአስተምህሯቸው ትኩረት በማድረግ “[ምስጢረ ቁርባን] እምነትን ይቀድማል”፣ “በእምነት ሲከናወን ደግሞ ቁርባን ጸጋን ይሰጣል” ብለዋል። ~ Catechism of the Catholic Church. Liguori, MO: Liguori Publications, 1994. pp. 291-293.
2
ሠ. በጌታ እራት ላይ አራት መሰረታዊ የክርስቲያን አመለካከቶች አሉ (አባሪ 17ን ተመልከት)።
1. ትራንሰብስታንሲዬሽን (Transubstantiation) ኅብስቱና ወይኑ የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም ነው ብሎ ማመን ነው። ይህ በሮማ ካቶሊክ ክርስቲያኖች የተያዘው የጌታ እራት አመለካከት ነው።
ገጽ 214 17
Made with FlippingBook Ebook Creator