Theology of the Church, Amharic Mentor Guide
5 6 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ሀ. ማቴ. 26.26
ለ. ዮሐንስ 6፡53-60
በእንጀራውና በዓሣው ተአምር እንዲሁም በውኃው ላይ በተመላለሰበት ተአምር ክርስቶስ በቀደመው ቀን አድማጮቹን እያዘጋጀ የነበረው የቅዱስ ቁርባንን ተስፋ ለያዘው ታላቁ ሃሳብ [የዮሐንስ ወንጌል 6] ብቻ ሳይሆን እርሱ ሁሉን ቻይ አምላክ-ሰው፣ ከተፈጥሮ ህግጋት የሚበልጥ እና ነጻ የሆነ ሃይል ያለው፣ ልዕለ ተፈጥሮ የሆነውን የራሱን ስጋና ደም እንደ መብል ማቅረብ የሚችል መሆኑንም አረጋግጧል። ~ Joseph Pohle. “Eucharist.” Readings in Christian Theology. Vol. 3. Millard Erickson, ed. Grand Rapids: Baker, 1973. 2. ኮንሰብስታንሲዬሽን (Consubstantiation) ኅብስቱና ወይኑ ኅብስትና ወይን መሆናቸው እንዳለ ሆኖ የኢየሱስ ሥጋና ደም ይሆናሉ ብሎ ማመን ነው። ይህ በሉተራን አብያተ ክርስቲያናት የተያዘው የጌታ እራት አመለካከት ነው። ይህ አመለካከት የኢየሱስ እውነተኛ ሥጋ እና ደም በጌታ ራት ውስጥ እንዳለ ከላይ የተብራራውን መሠረታዊ ሃሳብ ይቀበላል ነገር ግን እንዴት አብረው እንደሚገኙ የተለየ ማብራሪያ አለው። 3. ሦስተኛው አመለካከት የተሐድሶ (Reformed) እይታ ነው።ፕሬስቢቴሪያን እና የተሐድሶ አብያተ ክርስቲያናት የክርስቶስ ሥጋ እና ደም ለጌታ እራት የተሰጠን በአካል ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እና መገኘት እንደሆነ ያስተምራሉ። ይህ ትውፊት የሚያመለክተው በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 6 ላይ ኢየሱስ ሥጋውን ስለ መብላት እንዳስተማረው፣ ይህንንም እንደ መንፈሳዊ እውነት አጽንዖት መስጠቱን ነው። ዮሐንስ 6፡60-63 ከደቀ መዛሙርቱም ብዙዎች በሰሙ ጊዜ። ይህ የሚያስጨንቅ ንግግር ነው፤ ማን ሊሰማው ይችላል? አሉ። ኢየሱስ ግን ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ እንዳንጐራጐሩ በልቡ አውቆ አላቸው። ይህ ያሰናክላችኋልን? እንግዲህ የሰው ልጅ አስቀድሞ ወደ ነበረበት ሲወጣ ብታዩ እንዴት ይሆናል? ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው።
2
ገጽ 215 18
Made with FlippingBook Ebook Creator