Theology of the Church, Amharic Mentor Guide
/ 5 7
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
በዚህ ቅዱስ ቁርባን ክርስቶስ በአካል ሳይሆን በመንፈስ ይገኛል... ሕዝቡ ቁርባኑን የሚቀበሉት በእምነት እንጂ በአፋቸው አይደለም፤ ሥጋውና ደሙን እንደ ተጨባጭ አካል አይቀበሉም ነገር ግን ሥጋውን ስለነርሱ እንደተቆረሰ ደሙም ስለነርሱ እንደ ፈሰሰ እንጂ። ስለዚህም ህብረቱ . . . በመንፈስ ቅዱስ ማደር ምክንያት የሚገኝ መንፈሳዊ እና ምስጢራዊ ኅብረት ነው። እንደ ጸጋ መንገድ የዚህ ቅዱስ ቁርባን ውጤታማነት በምልክቶችም ሆነ በአገልግሎት፣ ወይም በአገልጋዩ፣ ወይም በቃሉ ውስጥ አይደለም፣ ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ ተሳትፎ ውስጥ እንጂ። ~ Charles Hodge. Systematic Theology. Abridged edition. Grand Rapids: Baker, 1992. pp. 496-498.
ሀ. ቆላ.3.1
2
ለ. ዮሐንስ 16፡7
ምንም እንኳን አብዛኞቹ የጴንጤቆስጤ ወጎች ሜሞሪያሊስት ቢሆኑም፣ ጴንጤቆስጤአዊው ምሁር ጎርደን ፊ ከካልቪን አስተምህሮ ጋር ያለውን ተመሳሳይ አቁም ሲገልጽ እንዲህ ይላል:- “በእርግጥ፣ አንድ ሰው የመንፈስን በቅዱስ ቁርባን ላይ መገኘትን የጳውሎስ እውነተኛ የህልውና የመረዳት መንገድ አድርጎ መመልከቱ በጣም ስህተት አይሆንም። በ1ኛ ቆሮንቶስ 10.3 4 ላይ ካለው የእስራኤል ‘መንፈሳዊ ምግብ’ እና ‘መንፈሳዊ መጠጥ’ ያላቸው ተመሳሳይነት ቢያንስ የሚናገረው ነገር አለ።
~ Gordon Fee. Paul, the Spirit and the People of God. Peabody, MA: Hendrickson Publishers, 1996. p. 154.
4. የሜሞሪያሊስት (Memorialist) እይታ ዳቦው እና ወይኑ የክርስቶስን ሥጋና ደም ያመለክታሉ ብሎ ያምናል ስለዚህም ጌታ ለእኛ ያደረገልንን እንድናስታውስ ይረዱናል ብሎ ያምናል።
ሀ. የጌታን እራት እንደ ቅዱስ ቁርባን ከሚመለከቱት ከመጀመሪያዎቹ ሶስት እይታዎች በተቃራኒ የሜሞሪያሊስት እይታ የጌታን እራት እንደ ስርዓት ነው የሚያየው።
Made with FlippingBook Ebook Creator