Theology of the Church, Amharic Mentor Guide
/ 5 9
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ሠ. በእምነት ሊወሰድ እንደሚገባ እና ሙሉ እምነትን በክርስቶስ ሥራ ላይ እንድናደርግ እንደሚረዳን
ረ. ኃጢአት የሚወገድበት እና በእግዚአብሔር ይቅር ባይ ምሕረት ሥር የሚቀመጡበት ጊዜ መሆኑን
2. የጌታ እራት እነዚህ ነገሮች እንዲከሰቱ ምክንያት የሚሆነው እንዴት እንደሆነ ላንስማማ እንችላለን ነገር ግን እነዚያ ልዩነቶች የጌታ እራት በአምልኮ ሕይወታችን ውስጥ ያለውን መሠረታዊ አስፈላጊነት እንድንረሳ ሊያደርጉን አይገባም። ለቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ነው።
2
ማጠቃለያ
» አምልኮ ለእግዚአብሔር ጸጋ የቤተክርስቲያን ምላሽ ነው።
» ድነት ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ቸርነት ብቻ የሚመጣ ሲሆን ከሰራሁት ሥራ የተነሳ ድነቴን አገኘሁ የሚል የሰው ልጅ የለም።
» ጥምቀት እና የጌታ እራት በተለይ የክርስቲያን አምልኮ ጉልህ ክፍሎች ናቸው።
» ቤተክርስቲያን የጌታን እራት እና ጥምቀትን በምትረዳበት መንገድ ትለያያለች። አንዳንዶች እነዚህ ቅዱስ ቁርባን ናቸው ብለው ያምናሉ፣ ይህም የእግዚአብሔር ጸጋ ወደ እኛ የሚመጣበት መንገድ ነው ይላሉ፣ ሌሎች ደግሞ የእግዚአብሔርን ጸጋ የሚያመለክቱ እና የሚመሰክሩ ሥርዓቶች ብቻ ናቸው ብለው ያምናሉ።
እነዚህን እና ሌሎች ቪዲዮው ያነሳቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ አስፈላጊውን ያህል ጊዜ ውሰድ። እነዚህ ጥያቄዎች የተነደፉት በዚህ የመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔር ጸጋ የቤተክርስቲያንን አምልኮ መሰረት አድርጎ ለመገምገም እንዲረዳህ ነው። ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ በምትሰጥበት ጊዜ፣ የእግዚአብሔርን ጸጋ በተመለከተ ቅዱሳት መጻሕፍት ስለሚያስተምሩበት ግልጽ አቋም ለማሳየት ሞክር። የመጽሐፍ ቅዱስ አማኞች የእግዚአብሔር ጸጋ በጌታ እራት እና በጥምቀት አማካኝነት እንዴት ወደ እኛ እንደሚመጣ ስለሚለያዩ እባክህ ከአንተ ጋር የማይስማማ ሃሳብ ያላቸውን በክፍልህ ውስጥ ያሉትን በጥሞና እና በአክብሮት አዳምጥ። መልሶችህ ግልጽ እና አጭር ይሁኑ፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ በቅዱሳት መጻሕፍት አስደግፍ!
መሸጋገሪያ 1
የተማሪው ጥያቄዎች እና ምላሾች
ገጽ 215 19
1. ሶላ ግራቲያ ማለት ምን ማለት ነው እና ለምን አስፈላጊ ሆነ?
Made with FlippingBook Ebook Creator