Theology of the Church, Amharic Mentor Guide
6 6 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ትስስር እንዳለው የአይሁድ እምነት። ሆኖም ግን የጥንቶቹ አማኞች ተሰብስበው የተወሰኑ የአምልኮ ሥርዓቶችን ይለማመዱ ነበር። አማኞች ለኅብረት፣ ለመብላት፣ እና የጌታን እራት ለማክበር፣ ቅዱሳት መጻሕፍት ሲነበቡና ሲሰበኩ፣ ለመጸለይና ለእግዚአብሔር የምስጋና መዝሙሮችን ለመዘመር፣ እንዲሁም አዳዲስ አማኞችን ለማጥመቅ እና ፈውስን ለመቀበል ይጸልዩ ነበር። እነዚህ ልምምዶች ከየትኛውም ቦታ ጋር የተሳሰሩ አይደሉም፤ የተፈጸሙትም በክርስቲያናዊ ታሪክ ነው። “ሥርዓተ ቅዳሴ” የሚለው ቃል ጉባኤው በጋራ ሲያመልኩ የሚጠቀሙበት የአገልግሎት የቀን አቆጣጠር ውስጥ ያለ አገልግሎት ነው።
1. ቤተ ክርስቲያን በምትሰበሰብበት ጊዜ እግዚአብሔርን የምናመልከው በእግዚአብሔር ቃል ስብከት ነው።
ሀ. ሥርዓተ ቅዳሴ፣ ወይም የአምልኮ መርሐ ግብር እና የጊዜ ሰሌዳ፣ በታሪክ ውስጥ የእግዚአብሔርን ታላላቅ ሥራዎች እንደገና ያወሳል፤ ይለማመድማል።
2
ለ. ቤተክርስቲያን በቅዳሴዋ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን አንድ፣ እውነተኛ እና ታላቅ ታሪክ ታስታውሳለች፤ ታሰላስላለች።
ሐ. የእግዚአብሔርን ቃል እንደ እግዚአብሔር ታሪክ ስንሰብክና ስናስተምር፣ እግዚአብሔር በሕዝቡ እና በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ስላደረገው ነገር አድናቆታችንን እና አክብሮታችንን በመግለጽ እግዚአብሔርን እንድናመልክ ይመራናል።
2. በጌታ ማዕድ አብረን በመቀመጥ (የጌታ እራት ወይም ቅዱስ ቁርባን ተብሎ ይጠራል) እግዚአብሔርን እናመልካለን። ስለ ቅዱስ ቁርባንን ምስረታ የምናውቅባቸው የአዲስ ኪዳን ምንጮች አራት ናቸው፣ አጫጭር ዘገባዎች በእያንዳንዱ ሲኖፕቲክ ወንጌላት እና በጳውሎስ የመጀመሪያ መልእክት ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ውስጥ ይገኛል (ማቴ. 26.26-29፤ ማር. 14.22-25፤ ሉቃ. 22.14) -20፣ እና 1ቆሮ.11፡23-26)።
ሀ. የጌታ እራት “ቅዱስ ቁርባን” ተብሎም ይጠራል፤ ዩካሪስቲዮሳስ/eucharisteosas ከተሰኘ ከላቲን ቃል የተገኘ ነው (“ለመስጠት ወይም ለማመስገን”)። ይህ ቃል በቀደመችው ቤተክርስቲያን በብዛት ጥቅም ላይ የዋለ ቃል ነበር፤ ለጠቅላላው
Made with FlippingBook Ebook Creator