Theology of the Church, Amharic Student Workbook
/ 1 2 3
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
6. የቤተክርስቲያንን ሥነ-መለኮታዊ የይገባኛል ጥያቄዎች እውነተኝነት ለመገምገም የቪንሴንቲያን ደንብ መርሆችን በግልፅ አስቀምጡ። ቤተክርስቲያ እምነቷን እና ድርጊቱን በሚመለከት የተለያዩ የሚቃረኑ የይገባኛል ጥያቄዎችን ለመገምገም እንዲህ አይነት ህግ እንዲኖራት ለምን አስፈለገ? 7. የኒቂያው የሐዋርነት መመዘኛ ከቪንሴንቲያን ደንብ ጋር እንዴት ይዛመዳል? ቤተክርስቲያን በታሪክ ለምታምንበት ነገር ፍትሃዊነትን ለማድረግ እነዚህ ሁለት ህጎች ሁል ጊዜ ሊገልፁ እና እርስ በርሳቸው መዛመድ የሚገባቸው ለምንድ ነው? 8. እነዚህን ደንቦች እና መመዘኛዎች በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ስለመተግበሩ በጉባኤዎቻችን ውስጥ እነማን በጣም ሊያሳስባቸው ይገባል? በከተማ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ እንዴት እነሱን በብቃት ልንጠቀምባቸው እንችላለን?
በሥራ ላይ ያለች ቤተክርስቲያን ክፍል 2
ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ
በአለም ላይ የቤተክርስቲያን ስራዎች ባህሪ በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተጠቀሱትን የተለያዩ የቤተክርስቲያን ምስሎች በመመርመር መረዳት ይቻላል። እያንዳንዱ ምስሎች ቤተክርስቲያን በአለም ላይ ያላትን ሚና እና ተልእኮ ለማንፀባረቅ የተለያዩ ፅንሰ ሀሳቦችን ይሰጡናል። ቤተክርስቲያን ከእግዚአብሔር ጋር ያላትን የጠበቀ ግንኙነት በእግዚአብሔር ቤተሰብ፣ በክርስቶስ አካል እና በመንፈስ ቅዱስ ቤተመቅደስ ምስሎች እናያለን። ቤተክርስቲያንን እንደ ክርስቶስ አምባሳደር እንደሆነች በቤተክርስቲያን መነጽር እንደ እግዚአብሔር መንግስት ወኪል እንገነዘባለን። በመጨረሻም፣ ቤተክርስቲያን በበጉ ጦርነት ውስጥ እንደ እግዚአብሔር አሳታፊ ሰራዊት ስትዋጋ እናያለን። የዚህ የቤተክርስቲያን በሥራ ላይ ሁለተኛ ክፍል አላማዎቻችን፡- • በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተጠቀሱትን የተለያዩ የቤተክርስቲያን ምስሎች በመቃኘት በአለም ላይ ባለው የቤተክርስቲያን ስራዎች ባህሪ ላይ ማተኮር። • የቤተክርስቲያንን ስራዎች በእግዚአብሔር ቤት፣ በክርስቶስ አካል እና በመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ መነጽር ለማየት። • የቤተክርስቲያንን ስራዎች በአምባሳደርነት መነጽር፣ እንዲሁም ቤተክርስቲያን እንደ እግዚአብሔር መንግስት ወኪል ለመዳሰስ። • ቤተክርስቲያንን በእግዚአብሔር ሰራዊት መነፅር እንዲሁም የቤተክርስቲያንን ስራ በበጉ ጦርነት ውስጥ እንደ ውጊያ ለመመልከት። እነዚህ ምስሎች የቤተክርስትያንን ማንነት እና በዓለም ውስጥ ኣሁን ላይ ያላትን ስራ እንዴት መረዳት እንዳለብን ትልቅ ግንዛቤ ይሰጡናል።
የሴግመንት 2 ማጠቃለያ
4
Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online