Theology of the Church, Amharic Student Workbook

1 2 4 /

የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት

ቪድዮ ሴግመንት 2 ዝርዝር

I. የቤተክርስቲያን ዋና ስራ የእግዚአብሔርን ስራ ማስረጃ በማህበረሰብ ህይወቷ ውስጥ መስጠት ነው፡- የቤተክርስቲያን የመጀመሪያ ስራዋ የእግዚአብሔርን መልካምነት በህይወቷ እና በግንኙነቷ ማወጅ ነው። የቤተክርስቲያን ዋና ስራ አንድ ነገር መሆን እንጂ አንድን ነገር ማድረግ አይደለም፤ ቤተክርስቲያን እንደ እግዚአብሔር ሰዎች በመጀመሪያ እሷን የፈጠራት የእርሱን ክብር የሚያንፀባርቅ የህይወት ጥራት ለማሳየት ተጠርታለች። አዲስ ኪዳን ብዙ የቤተክርስቲያን ምስሎችን ይሰጠናል እነዚህም ሁሉ እግዚአብሔርን እንደ ህዝቡ ለማክበር ልንሰራው የሚገባንን ስራ ምንነት ማስተዋልን ይሰጡናል።

ሀ. ስንመጀምር እንደ እግዚአብሔር ቤት፣ እንደ ወንድሞች እና እህቶች በአንድነት መኖር እንዲሁም እንደ እግዚአብሔር ውድ ቤተሰብ መኖር አለብን።

ጳውሎስ በቲቶ 2፡14 ላይ እንደገለጸው፣ ኢየሱስ “ከዓመፅ ሁሉ ሊቤዠን ለመልካምም ሥራ የሚቀናውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ” ሲል ለሕዝቡ፣ ለቤተክርስቲያን ሲል ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ሰጠ። አዎን፣ በኤፌሶን 2፡10 መሠረት ለተፈጠርንለት መልካም ሥራ ልንቀና ይገባናል። እና ጴጥሮስ በ1ኛ ጴጥሮስ 2 ላይ በግልፅ እንዳስቀመጠው ከእነዚህ ስራዎች በስተጀርባ ያለው ዋነኛ ምክንያት የእግዚአብሔርን በጎነት እና ባህሪ ማሳየት ነው። በዓለም ላይ የእሱን የላቀ ባህሪ እናውጅ ዘንድ እኛ የእርሱ ርስት ነን። “እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ” (1ኛ ጴጥሮስ 2፡9)

1. ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔር ልጆች፣ የእግዚአብሔር ቤተሰብ እና የቤተሰቡ አባላት መሆናችንን ያውጃል፣ ኤፌ. 4.1-3.

2. የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ምሥራች በመመስከር ለአብሮነትና እና ለመተባበር የሚረዱ ሥራዎችን መሥራት አለብን፣ ፊል. 1፡27-28።

4

ለ. በመቀጠል በአለም ውስጥ ያለ የክርስቶስ አካል እንደመሆናችን፣ እርስ በእርሳችን እና በጎረቤቶቻችን መካከል በሚኖረን ግንኙነት የኢየሱስን ህይወት መምሰል አለብን።

1. የኢየሱስን ሥራ በዓለም ውስጥ መወከል እና ማበርከት የእያንዳንዱ ክርስቲያን እና እያንዳንዱ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን መብትና ኃላፊነት ነው፣ ሮሜ. 12.4-6.

2. ጳውሎስ ለመጠራታችን አንድ አካል አንድ እምነት እና አንድ ተስፋ ብቻ እንዳለ ያረጋግጥልናል። ስለዚህም ከዚህ አንድነት አንፃር ወጋችን ወይም እንቅስቃሴያችን ከሌሎች ይልቅ በእግዚአብሔር ዘንድ አስፈላጊ ነው ብሎ ከማሰብ የራስ ወዳድነት ዝንባሌ ሁሉ ንስሐ መግባት አለብን። የሌሎች አማኞችን አስተዋጽዖ ችላ ማለት ወይም ወደጎን መተው ኢ-ስነ-ምግባራዊነት ነው እናም በአለም ላይ ያለውን የእግዚአብሔርን አላማ ለመፈጸም ራሳችንን ከእነሱ ጋር ለመስማማት መፈለግ አለብን። ኤፌ. 4.1-6.

Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online