Theology of the Church, Amharic Student Workbook
1 2 8 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ሐ. በድሆች ወይም አቅመ ደካሞች ላይ የሚደርሰውን መገለል እና መድልዎ ይህም በነፃነት፣ በሙሉነት እና በፍትሃዊነት የመኖር እቅማቸውን የሚሸረሽር ማንኛውንም ነገር በሚመለከት ዝም ኣንልም። ዘዳ. 27.19.
4. በሰዎች መካከል በሁሉም ደረጃዎች ፤ በግለሰቦች፣ በቤተሰብ፣ በባህል እና በሕዝብ መካከል ለትክክለኛ እና ፍትሃዊ ግንኙነቶችን እንሰራለን።
ሀ. ያለ እውነተኛ ጥረት ለፍትህ እና ለጽድቅ ያልተበረዘ አምልኮ እና ምስጋና የለም፣ አሞጽ 5፡23-24።
ለ. እኛ የክርስቶስ አምባሳደሮች ነን። በሁሉም ነገር፣ ለድሆች እና ለተጨቆኑ በስሙ በተጨባጭ በተገለጠ እና ወጥ በሆነ መንገድ ፍትህን ልንፈልግ ይገባል እንዚህም፦ (1) የፍትህ አስተዳደር ለእነሱ በህጋዊ ስርዓታችን፤ አሞጽ 5.10-15
እንደ እግዚአብሔር መንግሥት አምባሳደሮች፣ ቤተክርስቲያን የመንግሥቱን የጽድቅ አገዛዝ በእኛ የነጻነት፣ የሙሉነት እና የፍትህ ሥራ ማሳየት አለባት።
(2) እነርሱን ሊበዘበዙ ባሉ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች፣ ዘሌ. 19.35-36
(3) ሕጎቻችን በጣም ተጋላጭ የሆኑትን ሰዎች ፍላጎት በቀላሉ ችላ በሚሉበት መንገዶች፣ ኢሳ. 10.1-4
4
III. ቤተ ክርስቲያን ያለችው እንደ እግዚአብሔር ሠራዊት ልትዋጋ፤ በበጉ ጦርነት ውስጥ ውጊያ ልታደርግ፣ የእግዚአብሔርን እውነት ልታውጅ እና፣ የዲያብሎስን ሥራ ለማጥፋት እና ክፉን በመልካም ለማሸነፍ ነው። በቀራንዮ መስቀል ላይ የኃጢአታችንን ዋጋ ከፍሎ፣ ኢየሱስ እንደ (ክርስቶስ ቪክቶር) በድል አድራጊነት ተነስቷል፣ እናም በሞቱ የዲያብሎስን እና የጭፍሮቹን ስራ አጥፍቷል። ቆላ. 2.15፣ 2ቆሮ. 2.14. የቤተክርስቲያን ዋነኛ ምስል የእግዚአብሔር ሰራዊት ነው እሱም የሚዋጋው ከሥጋና ከደም ጋር ሳይሆን በከፍታ ቦታዎች ካሉ ከመንፈሳዊ ኃይሎች ጋር ነው (ኤፌ. 6.12-13) ። ኢየሱስ ድልን ቢያደርግም በዳግም ምጽአት ስራውን እስኪጨርስ ድረስ እኛ ደግሞ በዚህ ዘመን መዋጋት አለብን። በዘመናችን መልካሙን የእምነት ገድል እንዴት ነው የምንዋጋው?
ሀ. በመጀመሪያ የእግዚአብሔርን እውነት በክርስቶስ በማወጅ እንደ እግዚአብሔር ወታደሮች እንዋጋለን።
Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online