Theology of the Church, Amharic Student Workbook
/ 1 2 7
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ሀ. በእግዚአብሔር አምሳል ለተፈጠረው የሰው ልጅ በቂ እንክብካቤ አለማግኘትን እንዲሁም አካላዊ በሽታ እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን ለማስወገድ ሥራዎችን እንሠራለን።
ለ. በተጨማሪም፣ እኛ አማኞች የተጨቆኑ ሰዎችን የትም ብናገኝ በሰዎች ላይ የሚደርሰውን ስቃይ እና ስፍር ቁጥር የሌላቸውን የዚያ ስቃይ መንስኤዎች እንቃወማለን።
3. የተሰበረውን ወደ ሙሉነት እንጠግን ዘንድ እንደተጠራን እግዚአብሔር ራሱ ሥራችንን እንደሚያውቅ እርግጠኞች ነን። መዝ. 41.1-2.
ሐ. በመጨረሻም የኢየሱስ ክርስቶስ አምባሳደሮች እንደመሆናችን መጠን የመንግሥቱን ፍትሓዊ አገዛዝ ለማሳየት እንቅስቃሴዎችን እናደርጋለን።
1. እግዚአብሔር ሕዝቡን እውነተኛ አምልኮና እውነተኛ መሥዋዕት ያስተምራል። ኢሳ. 1.16-18.
4
2. የኢየሱስ አምባሳደሮች እንደመሆናችን በሰዎች መካከል ባገኘንበት በማንኛውም ደረጃ ኢፍትሃዊነትን ለመቋቋም በንቃት እንሰራለን።
3. በአሜሪካ በከተሞች አካባቢ እና በዓለም ዙሪያ ባሉ ከተሞች ያሉ ሁኔታዎች ጥልቅ የፍትህ መጓደል ምልክቶች ይታዩባቸዋል። መክብብ 4.1.
ሀ. የኢየሱስ የፍትሐዊ አገዛዝ አምባሳደሮች እንደመሆናችን መጠን ሁሉንም ዓይነት ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ ሃይማኖታዊና ግላዊ ጭቆናዎች መቃወም አለብን።
ለ. እኛ ለራሳቸው መቆም ለማይችሉ እንቆማለን እናም እንደ ሰው መብታቸውን ለማስከበር ምንም አይነት ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ እንሆናለን። ምሳ. 31፡8-9።
Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online