Theology of the Church, Amharic Student Workbook
/ 1 3 3
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
2. በዚህ መንገድ ጥናትን ለማድረግ ማለትም፣ በዘይቤ እና በምሳሌ መነጽር ምን ገደቦች (ካሉ) ሊቀመጡ ይገባል? መንፈስ ቅዱስ በሚያስተምረን መንገድ ስለቤተክርስትያን ማንነት በነዚህ ምሳሌያዊ አነጋገሮች ለመጠቀም ይህንን ዘዴ እንዴት መጠቀም እንችላለን? 3. እንደ እግዚአብሔር ሕዝብ ወይም “ቤተሰብ” በመጽሐፍ ቅዱሳዊው የቤተክርስቲያን ምስል ስለ ቤተክርስቲያን ሥራ ምን እንማራለን? ይህ ቤተክርስቲያን በግንኙነቶቿ በተለይም በአባሎቿ መካከል ምን ማድረግ እንዳለባት እንድንረዳ የሚያግዘን እንዴት ነው? 4. “የክርስቶስ አካል” ምስል የሆነች ቤተክርስቲያን በአለም ውስጥ ምን ማድረግ እንዳለባት እንድንገነዘብ የሚረዳን እንዴት ነው? 5. “የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ?” በሚለው የቤተክርስቲያን ሃሳብ ስለቤተክርስቲያ በአለም ላይ ስላለው ስራ ምን እንማራለን? ይህ ምስል ቤተክርስቲያን በአለም ላይ ስላላት ሚና ሊያስተምረን ምን ይሰራል? 6. ከአምባሳደርነት ሀሳብ ጋር የተያያዙትን የተለያዩ ተግባራትን፣ ኃላፊነቶችን እና ሚናዎችን ይግለጹ? ይህ ሕያው ምስል እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ተወካይ ቤተክርስቲያን በዓለም ላይ ምን ማድረግ እንዳለባት እንድንረዳ የሚረዳን እንዴት ነው? 7. እንደእግዚአብሔርወታደርወይምሠራዊትበቤተክርስቲያኗምስልበኩልስለቤተክርስቲያን የስራ ባህሪ ምን አይነት ግንዛቤዎችን እናገኛለን? ይህ ምስል አባሎቻችንን ለማስታጠቅ፣ ሀብቶቻችንን ለማደራጀት እና ለማሰማራት እና እንቅስቃሴዎቻችንን ከምስሉ ጋር ወጥ በሆነ መልኩ ለማቀድ እንዴት ሊረዳን ይችላል? ይህ ትምህርት የሚያተኩረው የቤተክርስቲያንን ስራ ባህሪ እና ተግባር በተወሰኑ የኒቂያው የሃይማኖት መግለጫ ምልክቶች፣ የተሃድሶ ትምህርት እና የቅዱስ ቪንሰንት አገዛዝን በመረዳት ላይ ነው። እንዲሁም የቤተክርስቲያንን ስራ እና አገልግሎት በተወሰኑ የተመረጡ ምስሎች መነፅር ለመረዳት ፈልገን ነበር ይህም ቤተክርስቲያን ከእያንዳንዱ የስላሴ አባላት፣ ከአለም እና ከዲያብሎስ እና ከጨለማ መንፈሳውያን ሀይሎች ጋር ያለውን ግንኙነት የሚያጎሉ ናቸው። ብዙዎች ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ግንኙነት አለን የሚሉ እንዲሁም ክርስቲያን ወይም የእግዚአብሔር ጉባኤዎች ነን በሚሉበት ዓለም፣ የክርስቲያን መሪዎች እውነተኛ የክርስቲያን ማኅበረሰብ ምን እንደሆነ ተረድተው ይህንንም በሌሎች ደቀ መዛሙርት መካከል መሟገትና መግለጽ መቻል አለባቸው። የቤተክርስቲያንን ስራ በአለም ላይ በትክክል እንድንረዳ እንዴት እንደሚያስችሉን በማሰብ እነዚህን ወሳኝ ጽንሰ-ሀሳቦች በጥንቃቄ አስቡባቸው። ³ የቤተ ክርስቲያንን ተፈጥሮ እና ተግባር ለመረዳት በጣም አስፈላጊ እና ተቀባይነት ካላቸው መመዘኛዎች አንዱ በኒቂያው የሃይማኖት መግለጫ መሠረት “በአንዲት፣ ቅድስት፣ ካቶሊክ እና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን” በሚለው ምልክቶች ውስጥ ይገኛል። እውነተኛይቱ ቤተክርስቲያን አንዲት፤ ለእግዚአብሔር ይዞታ እና ጥቅም የተለየች ሁለንተናዊ እና ዓለም አቀፋዊ፣ እንዲሁም ሐዋርያዊ መነሻ እና ማንነት ያላት ናት።
4
ግንኙነት
የቁልፍ ጽንሰ ሐሳቦች ማጠቃለያ
Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online